Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
-
Meleket
- Member+
- Posts: 5070
- Joined: 16 Feb 2018, 05:08
Post
by Meleket » 12 May 2023, 07:01
ድምጻዊቷና ዘማሪቷ ተወዳጇ ሂሩት በቀለ፡ ብዙዎችን በጥበብ ስራዎችሽ በማዝናናት እንዲሁም በዝማሬሽ በርካቶችን ለኣምልኮ በማነቃቃት ጉልህ ድርሻ ኣበርክተሻልና፡ ሁሌም በጥበብ ኣፍቃሪዎች ልብ ውስጥ ነግሠሽ ትኖሪያለሽ! ያመለክሽው ኣምላኽ በቀኙ ይቀበልሽ!
አንጋፋዋ ድምጻዊት ሂሩት በቀለ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየች
Konjit Sitotaw

በኢትዮጵያ የሙዚቃ ኢንዱስትሪ ውስጥ የራሷን አሻራ ያስቀመጠችው አንጋፋዋ ድምጿዊት ሂሩት በቀለ ከዚህ ዓለም በሞት መለየቷ ተሰምቷል።
ድምጻዊት ሂሩት ከ1950 መጀመሪያ እስከ 1980ዎቹ መጨረሻ ድረስ፤ ሕይወት እንደሸክላን ጨምሮ በርካታ ድንቅ የሙዚቃ ሥራዎችን ለአድናቂዎቿ ያበረከተች ሲሆን፤ ባደረባት ሕመም ምክንያት በአገር ውስጥና በውጭ በሕክምና ስትረዳ ቆይታ በ80 ዓመቷ ካሳንችስ አካባቢ በሚገኘው መኖሪያ ቤቷ ዛሬ ግንቦት 04/2015 ከዚህ ዓለም በሞት መለየቷ ታውቋል፡፡
ሂሩት በቀለ ከክቡር ዘበኛ የሙዚቃ ክፍል ጀምሮ በብዙ መድረኮች ላይ ከመጫወት ባለፈ፤ የራሷን የሙዚቃ ካሴቶች በማሳተም ሥራዎቿን ለህዝብ ያደረሰች ሲሆን፤ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በዘማሪነት ሥራዎችን ስትስራ እንደነበር ይታወሳል፡፡
ሂሩት በቀለ የ7 ልጆች እናት፣ የ10 ልጆች አያት እና የ7 ልጆች ቅድመ አያት ነበረች።
https://mereja.com/amharic/v2/822264
ለቤተሰቦቿ ለአድናቂዎቿና ለመላው ጥበብ አፍቃሪ ኢትዮጵያዊና ኤርትራዊ ማኅበረሰብ በሙሉ መጽናናቱን ተመኝተናል፡ እኛ ኤርትራውያን የመሃልና የመስመር ዳኞች።
-
kerenite
- Member
- Posts: 4680
- Joined: 16 Nov 2013, 13:15
Post
by kerenite » 12 May 2023, 12:06
Meleket wrote: ↑12 May 2023, 07:01

This is sad news RIP Hirut. Sadly there is an end for everything.
I extend my heartfelt condolences to her family and to her loved ones.
My favorite songs of Hirut:
1. Tara ina gidgida bewerQ bisera genzeb teQolulo bimesil terara...hiwet indeshekala...(this song was loved by the late famous sudanse singer abdulaziz mubarak and he sang it)
2. Sew biagengim biyaTam maseb metekezu ayQerim..
3. Ayn yetefeterew hulun lemayet naw..hulun lemayet naw...
4. Teyi iniredada yene ida bichayen ine indalugeda.. (she sang it together with shambel Mesfin)
RIP Hirut! You are a legend, you have left a legacy and you will never be forgotten.
-
Horus
- Senior Member+
- Posts: 42777
- Joined: 19 Oct 2013, 19:34
Post
by Horus » 12 May 2023, 13:22
ሂሩት ሰላም ሁኝ !! ዛሬ በጣም የሚያዝን ቴዲ አፍሮ ይመስለኛል! ለሂሩት ሲያለቅስ ላባቱም የሚያለቅስ ይመስለኛ ። አባቱና ካሳሁንና ሂሩት በጣም ቅርብ (ምናልባትም ፍቅረኞች) ከመሆናቸው የተነሳ ቴዲ በህጻንነቴ የዘፋኞች መልበሻ ክፍል ውስጥ በሂሩት እግር ስር እቀመጥ፣ እደበቅ ነበር ብሎናል!!! ይህ የህጻንነት ትዝታው ቴዲን ያስለቅሰዋል ብዬ አምናልሁ !! ሌላ የምታዝነዋ ሂሩትን ኮፒ ያደረገቸው አበባ ደሳለኝ ነች ።
-
kerenite
- Member
- Posts: 4680
- Joined: 16 Nov 2013, 13:15
Post
by kerenite » 12 May 2023, 14:52
I wonder why ethios are mum. I believe Hirut was an idol of her generation. Regardless however, you should extend condolences to her family.
Don't you feel ashamed when an eritrean reports her death and only one eritrean shows his sympathy to her?
Where is your RIP blabber. No wonder dictator issayas is worried about you.
-
Meleket
- Member+
- Posts: 5070
- Joined: 16 Feb 2018, 05:08
Post
by Meleket » 13 May 2023, 02:55
ድምጸ መረዋዋ አንጋፋ ድምጻዊት ኂሩት በቀለ አረፈች
"የኪነት ቡድኑ ካራማራ ድረስ ሄዶ ስራዎቹን ሲያቀርብ ጥይት ሲያፏጭ ሙዚቀኖቹ ጥይት ይመታናል ብለው ቁጭ ብለው ሲጫወቱ እሷ ግን ቆማ ``ሺ ገድሎ ከድንበሩ ላይ፤ አልፏል ያ ጀግና ተጋዳይ`` እያለች እንባዋን እያፈሰሰች ነበር የዘፈነችው፤ ይህ እራሴ ያየሁት ው።"
ድምጻዊት ኂሩት በቀለ ከዚህ ዓለም ድካም በአጸደ ሥጋ ተለየች
ድምጸ መረዋዋ አንጋፋ ድምጻዊት ኂሩት በቀለ ከዚህ ዓለም ድካም በአጸደ ሥጋ ዛሬ ተለየች። ድማጻዊት ኂሩት በቀለ በፖሊስ የሙዚቃና ትያትር ክፍል ለ35 ዓመታት ያገለገለች ሲሆን ከ200 በላይ ዘፈኖችን ማበርከቷን ለማወቅ ተችሏል።
ይህ ፍቅርን፣ ኢትዮጵያዊነትን እና ጀግንነትን ያደመቀ፤ ያሞካሸ ልሳን ላይመለስ ተዘጋ፤ ድምጸ መረዋዋ አንጋፋ ድምጻዊት ኂሩት በቀለ። ድምጻዊት ኂሩት በቀለ ከ1953 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 1980ዎቹ አካባቢ ከ200 በላይ ዘፈኖችን ያበረከተች አንጋፋ ድምጻዊ እንደነበረች በእሷ ሥራዎች ላይ ከፍተኛ አሻራ ያኖሩት አንጋፋው አርቲስት ተስፋዬ አበበ ለዶቼ ቬለ /DW/ ተናግረዋል።
" በፖሊስ ሰራዊት የሙዚቃ ክፍል ከ1953 ዓመተምህረት ጀምሮ ከ30 ታት በላይ አገልግላለች። በዚህ ጊዜ ውስጥ የዘፈነችው የፍቅር ዘፈኖች በጣም ጥቂቶች ነበሩ አብዛኛውቹ ስለ ኢትዮጵያ እና ስለኢትዮጵያ ጀግኖች ነው የዘፈነችው።"
በፖሊስ የቲያትርና የሙዚቃ ክፍል ባልደረባ ሆና በሠራችባቸው ጊዚያት ሠራዊቱን ግንባር ድረስ በመሄድ አጀግናለች፤ ስለሐገር መስዋዕትነት ክብርና መዓርግ በጥበባዊ አንደበቷ አቀንቅናለች። አንዳንዴም መድረክ ላይ እየዘፈነች ጥይት በጆሮዋ እያፏጨ ሲያልፍ እንኳን በተመስጦ እንባዋ እየወረደ ጭምር ሠራዊቱን ታጀግን እንደነበረ አርቲስት ተስፋዬ አበበ ያዩትን በእማኝነት ያስታውሳሉ።
"የኪነት ቡድኑ ካራማራ ድረስ ሄዶ ስራዎቹን ሲያቀርብ ጥይት ሲያፏጭ ሙዚቀኖቹ ጥይት ይመታናል ብለው ቁጭ ብለው ሲጫወቱ እሷ ግን ቆማ ``ሺ ገድሎ ከድንበሩ ላይ፤ አልፏል ያ ጀግና ተጋዳይ`` እያለች እንባዋን እያፈሰሰች ነበር የዘፈነችው፤ ይህ እራሴ ያየሁት ው።"
ጽምጻዊት ኂሩት በቀለ በፖሊስ ሠራዊት የሙዚቃና የቲያትር ክፍል ለ35 ዓመታት አገልግላለች። ኂሩት በአብዛኛው የአገር ፍቅርን ከሚቀሰቅሱ ዘፈኖቿ መካከል «ኢትዮጵያ» ፤ ስለሕይወት ካዜመቻቸው ደግሞ «ሕይወት እንደ ሸክላ» ፣ የሚለውና ሌሎች ጆሮገብ የሙዚቃ ሥራዎቿ አሁንም ድረስ ተወዳጅነትን ያልተለያቸው ድንቅ ሥራዎቿ ናቸው። ኂሩት በቀለ ወደ 40 የሚጠጉ የሙዚቃ ሸክላዎችንና 14 ካሴቶችን ታትመውላታል። ድምጻዊት ኂሩት በቀለ በግል ሕይወቷም ርህሩህና ለሰው ሟች እንደነበረች አንጋፋው አርቲስት ተሰፋዬ አበበ ነግረውናል።
ድምጻዊት ኂሩት በቀለ የመንግሥት የመገናኛ ብዙሃን እንደዘገቡት ከዚህ ዓለም ድካም ያረፈችው በ83 ዓመቷ ሲሆን የ7 ልጆች እናት፤ እና ቅድመ አያትም ነበረች። ባደረባት ህመም በአገር ውስጥና በውጭ ስትታከም ከቆየች ቦኋላ በዛሬው ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት መለየቷን ታውቋል።
ዶይቼቬለ በድምጻዊት ኂሩት በቀለ ሕልፈተ ሕይወት የተሰማውን ሐዘን እየገለጸ ለቤተሰቦቿና አድናቂዎቿ መጽናናትን ይመኛል።
https://www.dw.com/am/%E1%8B%B5%E1%88%9 ... -11646-xml
ከዚህ የበለጠ ደስ ዬሚልና የሚያጽናና ምስክርነት ሊኖር ኣይችልም "ድምጻዊት ኂሩት በቀለ በግል ሕይወቷም ርህሩህና ለሰው ሟች ነበረች" ብለውናል ኣንጋፋዎቹ አስቲስቶች። ሂሩት ስግብግብ ኣልነበረችም ሂሩት ገዳይ ኣልነበረችም ሂሩት ድምጻዊቷም ዘማሪዋም በግል ሕይወቷ ርህሩርና ለሰው ሟች ነበረች! . . .
ለጨዋዎቹ ለ Horus እና ለ kerenite ክብራችንን ለመግለጽ እንወዳለን። ሁለቱም እውነተኛ ጥበብ ኣፍቃሪዎች መሆናቸውን ጽሑፋቸው አሳይቶናል። Horus እባክህ ቴዲንም አበባ ደሳለኝንም በርቱ አዳዲስ ዜማዎችንም ኣቅርቡልን በልልን። ሁለቱም የምርጦች ምርጥ መሆናቸውን እኛ ኤርትራውያን የመሃልና የመስመር ዳኞችም እንመሰክርላቸዋለን። እኛ ኤርትራውያንም አበባ ሃይለ ዬምትባል አንዲት ምርጥ የጥበብ ሰው ኣለችን፡ ዜማዎቿ እጅግ መሳጮች ከመሆናቸው የተነሳ ልብ ውስጥ ዬሚገቡና መንፈስን ዬሚያድሱ ናቸው፡ ልክ እንደ ድምጻዊት አበባ ደሳለኝ።
ወዳጃችን kerenite የሂሩትን ዜማዎች ጥሩ ኣድርገህ ያጣጣምክ እንደ ወዳጃችን Horus መፍቀሬ-ጥበብና ጨዋ ሰው ነህና ላንተም ልባዊ ኣክብሮታችንን ልንገልጽልህ እንወዳለን፡ እኛ ኤርትራውያን የመሃልና የመስመር ዳኞች፡ በኤርትራዊ ጭዋነት ኩራትና ትህትና ጭምር።