Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Za-Ilmaknun
Member
Posts: 4487
Joined: 15 Jun 2018, 17:40

የአብይ መንግስት የአማራን ህዝብ እንዲወጋ ያሰማራውን ሰራዊት እየሰበሰበ ነው። የሪፓብሊካን ዘብ በምትኩ ለወረራው እንዲሰማራ ይጠበቃል፥

Post by Za-Ilmaknun » 03 May 2023, 13:51



ሰራዊቱ የተላከበትን አማራን የመፍጀት ተልእኮ ለመፈፀም ፈቃደኛ አልሆነም። የአራት ኪሎው የ ኦህዴድ መንግስት ታማኝ ያላቸውን የሪፓብሊካን ዘብ ወደ አማራ ክልል እያሰማራ ነው። እስካሁን ባለው ውሎ ፥ የአማራው ህዝብ እንቅስቃሴውን በከፍተኛ ጥንቃቄ እያከናወነ ሲሆን ፥ የመከላከያው የበታች አዋጊዎችና ተዋጊው ሃይል ፥ ወደ ህዝብ አንተኩስም በማለት መሳሪያውን እየዘቀዘቀ ይገኛል።

Horus
Senior Member+
Posts: 42773
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የአብይ መንግስት የአማራን ህዝብ እንዲወጋ ያሰማራውን ሰራዊት እየሰበሰበ ነው። የሪፓብሊካን ዘብ በምትኩ ለወረራው እንዲሰማራ ይጠበቃል፥

Post by Horus » 03 May 2023, 14:01

Za-Ilmaknun wrote:
03 May 2023, 13:51


ሰራዊቱ የተላከበትን አማራን የመፍጀት ተልእኮ ለመፈፀም ፈቃደኛ አልሆነም። የአራት ኪሎው የ ኦህዴድ መንግስት ታማኝ ያላቸውን የሪፓብሊካን ዘብ ወደ አማራ ክልል እያሰማራ ነው። እስካሁን ባለው ውሎ ፥ የአማራው ህዝብ እንቅስቃሴውን በከፍተኛ ጥንቃቄ እያከናወነ ሲሆን ፥ የመከላከያው የበታች አዋጊዎችና ተዋጊው ሃይል ፥ ወደ ህዝብ አንተኩስም በማለት መሳሪያውን እየዘቀዘቀ ይገኛል።
ይህ ክስተት አይቀሬ ነው ብዬ ነበር ትላንት !!!

"የፖለቲካ ሳይንስ ስለ 3ኛ አለም አገሮች ሚሊታሪ ያለው ትንበያ ተራ በተራ በአቢይ አህመድ ሰራዊት ውስጥ እየተከሰተ ነው ። ምን ማለቴ ነው?

አንደኛ በኢትዮጵያ ውስጥ በቢይ አህመድ ወረሙማ አገዛዝ ላይ አገር አቀፍ፣ እምቢተኘት፣ አመጽና የሽምቅ ዉጊያ እዚም እዛም እየፈነዳ አቢይ የእለት ተለት ህልውናው በጦርና ፖሊስ አመጽ ላይ እስከ ቆመ ድረስ አለምንም ጥርጥር መካከያም ፖሊስም፣ ስለላውም ሌላውም ልክ እንደ ሲቪሉ ማህበረ ሰብ እየተከፋፈለ ይመጣል። ይህ ዝም ብሎ በምኞት የሚወረወር አስተያየት አይደለም ፤ ሳይንስ ነው ። አይደለም ተራ ወታደሮች የጦር መኮንኖች እንደየ ብሄርና ፖለቲካ እምነታቸው ይከፋፈላሉ ። በተለይ የሚሊታሪ፣ ፖለቲካ፣ ኢኮኖሚና ስለልዋን የያዙት ያንድ ጎሳ ወረሞ ተረኞች ስለሆኑ!

ሁለተኛው እጅግ አይቀሬና አደገኛው ነገር ይህ ነው ። የሚሊታሪው ክፍል በውስጥ ክልልፍ ሲታመስ አቢይ በመደበኛው ሚሊታሪ ላይ ያለው እምነት ወይም አመኔታ ይጠፋና ዙፋኑን የሚጠብቀው በፕሪቶሪያን ዘብ ወይም ባለቀይ ቆቦች ላይ ብቻ ይሆናል። ይህ ባለቀይ ቦብ ከሞላ ጎደል የወረሞች ስብስብ ነው ። ስለሆነ አቢይ የሌላ ጎሳ ወታደሮችና መኮንኖች አግልሎ፣ አስሮ እና መረሸን ሲጀምር ቀጥታ ዉጊያ በወረሞና ያልሆኑ ወታደሮች መሃል ይፈነዳል ።

አንድ ቀን በመደበኛው ጦርና በቀይ ቆቦች መሃል ዉጊያ ቢፈነዳ እንዳትገረሙ !! አንዱ የፖለቲካ ሳይንስ ሕግ ስለሆነ!!

ስለዚህ ዛሬ እየወጣ ያለው የሰራዊት ወደ ኤርትራ መሸፈት፣ የደቡብ ተወላጅ ወታደሮች መረሸን ፣ ያማራ ተወላጆች ዱር መግባት ሁሉም በታሪክ ሺ ግዜ የተከሰቱ የአብዮትና አመጽ ወቅት ሃቆች ናቸው !!!

አበው እንዲሉ ! ሞት ቢዘገይ የቀረ ይመስላታል !!"

Za-Ilmaknun
Member
Posts: 4487
Joined: 15 Jun 2018, 17:40

Re: የአብይ መንግስት የአማራን ህዝብ እንዲወጋ ያሰማራውን ሰራዊት እየሰበሰበ ነው። የሪፓብሊካን ዘብ በምትኩ ለወረራው እንዲሰማራ ይጠበቃል፥

Post by Za-Ilmaknun » 03 May 2023, 18:02

ሰበር ዜና
ሸዋሮቢት ነፃነቷን አወጀች

ሸዋ ሮቢት ከተማ ከትናንት ከሰዓት ጀምሮ በህዝባዊ ኃይሉ ቁጥጥር ሰር ገባች
ላለፉት ሶስት ቀናት ከኦህዴድ ሠራዊት ጋር ከፍተኛ ትንቅንቅ ሲያደርግ የነበረው የሸዋ ህዝብ እና በመከተዉ የሚመራዉ የአማራ ፋኖ አንድነት በሸዋ አካባቢውን በመቆጣጠር ከትናንት ከሰዕት ጀምሮ ህዝቡ ራሱን ማስተዳደር ጀምሯል።
የከተማ አስተዳደሩ፣የብልፅግና ፅ/ቤት እና የፀጥታ ተቋማት በሙሉ በህዝብ ቁጥጥር ስር ዉለዋል።

የሸዋ ህዝብ ከተማዉ በህዝባዊ ሠራዊቱ ቁጥጥር ስር እንድትወድቅ ስንቅ በማቀበል፣መንገድ በመዝጋት፣ህዝቡን ሊጨፈጭፍ የገባውን ሠራዊት በመመከት ከፍተኛ አስተዋፅኦ አበርክተዋል።
ህዝቡ ከጨፍጫፊው የብልፅግና አገዛዝ ወጥቶ እራሱን ማስተዳደር ለዓመታት ሲፈልገው እና ሲመኘው የነበረ መሆኑን በሀሴት ገልጿል።

@ወግደረስ ጤናው

የሸዋሮቢት ከተማ ህዝብ እና የአማራ ፋኖ አንድነት በሸዋ አካባቢውን ተቆጣጥሮ ማስተዳደሩን መጀመሩን ተከትሎ ብስጭት ውስጥ የወደቀው ኦህዴድ ብልፅግና ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሠራዊት ወደ ከተማዋ እንዲላክ ትዕዛዝ ሰጥቷል።
ከደብረብርሃን መስመር ተነስቶ "ቀይት፤ጉዶ በረት" የሚባሉ አካባቢዎች ለይ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የኦህዴድ ሠራዊት ወደ ሽዋ ሮቢት ከተማ ለመግባት ሲርመሰመስ ተስተውሏል።

የዓለም አቀፉን ማህበረሰብ ጨምሮ ሁሉም የአገር ውስጥ እና የውጭ የሲቪክ ተቋማት እንዲሁም ሚዲያዎች የኦህዴድ ሠራዊት አካባቢውን ከቦ በሶስት ቀናት ውስጥ ካደረሰው የንፁሃን ጭፍጨፋ በባሰ መልኩ ሊፈፅም ከፍተኛ ዝግጅት እያደረገ መሆኑን እንድታውቁልን ጥሪ እናቀርባለን ሲል ህዝባዊ ኃይሉ አስተዋቋል።

"ከዚህ በኋላ የሸዋን ህዝብ የኦህዴድ ሠራዊትም ይሁን የኦህዴድ ብልፅግና መዋቅር በጉልበት ሊገዛ አይችልም፤በቃን፤ነፃነታችንን በክንዳችን አስመልሰናል፤ በኦህዴድ ብልፅግና መዋቅር መገደል፣መፈናቀል፣መራብ እና መጨቆን በቅቶናል፤ሁሉም የአማራ ህዝብ የራሱን ህዝባዊ አስተዳደራዊ መዋቅር ልክ እንደ ሸዋ ህዝብ ይፈጠር"ሲሉ ለተቀረው የአማራ ክፍል አስቸኳይ ጥሪ አቅርበዋል።

በስተመጨረሻ ለኦህዴድ ሠራዊት አባላት የአማራ ፋኖ አንድነት በሸዋ እና የሸዋ ህዝብ እንዲህ ሲል ጥሪ አቅርቧል"...ለወንድም የአማራ እና የደቡብ ተወላጅ የሠራዊቱ አባላት እንዲሁም ለሚመለከተው የሠራዊቱ አባላት በሙሉ ትናንት በነበረ የዕርስ በርስ ጦርነት ከ1.2 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ረግፈዋል፤ከነዚህ መካከል በመቶሽዎች የሚቆጠረው ምስኪኑ የመከላከያ ሠራዊት አባላት ነው።

በየጥሻው ያለቀው ሠራዊት ደም እንኳን ሳይደርቅ፣ሲያጋድሉ የነበሩ አካላት ውስኪያቸውን መራጨት ጀምረዋል፤ዛሬም ምስኪኑ የሠራዊት አባላት ለዐብይ አህመድ ሥልጣን መቆየት ብቻ ሲባል ከተደገሰለት ዳግም ዕልቂት እራሱን ሊጠብቅ ይገባል።በህዝብ ላይ አልተኩስም በማለት ህዝባዊነቱን ሊያስመሰክር ይገባል።እየከዳ ቢወጣ ልንቀበለው ዝግጅት ጨርሰናል"ብሏል።

Post Reply