ሞት አይቀሬ ነዉ፣ አማሞታችን ይለያል እንጂ፡
በጣም ጥቅቶቻችን የክብር ሞት እንሞታለን፣ አቅባበራችን ያማራ ይሆናል፣ ከየት እንደ መጣን ና ወዴት እንደምንሄድ አስቀድመን እናዉቃለን፣ የበቀልኩት እዚህ ነዉ፣ መሞታዬም እዚህ ነዉ ብለን ለይተን እናዉቃለን፣ ለዘሂም መብታችን እንፋለማለን፡ መነሻቺንን ና መድረሻቺንን ለይተን እናዉቃለን። የክብር ሞት ለመሞት እንበቃለን፣ ታርካቺን ህዋዉ ሆኖ ይቀጥላል። የአቶ ግርማ የሽጥላ ሞት ይህን ይመስላል።
አብዛኞቻችን ደግሞ ከዬት እንደወጣን እንኳ በወል አንገነዘብም፣ መጨራሻቺን ዬት እንደምሆን በወል ኣናዉቅም። የከንቱ ሞት እንሞታለን። ታርካቺን አጭር ናት። ዬት ወድቀን እንደምንቀር እንኳ መገመት እንችልም። ሁለት ሞት መሆኑ ነዉ። ከወገን ተነጥለናል፣ ምንጫቺንን ረስተናል። የአገር ጥቅም አይገባንም፣ ከጠላት ጎራ ተሰልፈን አገርን የምጎዳ እርምጃዎችን እንደግፋለን፣ መንግስትን ና አገርን ለይተን ማየት ተስኖናል። የራሳቺንን መጨረሻ እንኳ መተየብ ተስኖናል። ሞታቺን የአይጥ ሞት ሆኖ ይቀራል። እንደዚህ አይነት ሞት ከምሞቱት ዉስጥ በቀርቡ ኢትዮጵያ ላይ መዕቅብ እንድጣል ለማስቻል ስንኮራተቱ የነበሩት የኢትዮጵያ እርግማን የሆኑ ትዉልድ ኢትዮጵያኖች ይገኙበታል። ሌላ ነገር ባይሆን መዕቀብ መንግስት ስራ ላይ ያሉትን ሳይሆን፡ ተራዉን ሕዝብ የምጎዳ የጠላትነት መሳሪያ መሆኑ እየታወቀ መሆኑ ነዉ።
መዕቀብ እንደ ኢትዮጵያ የሉት የደሃ አገሮች ላይ ተጣለ ማለት መድሃኒት መግዣ ጠፋ ማለት ነዉ፣ ሕይወት ተቀጠፋ ማለት ነዉ። የትምህርት ቁሳቁስ መግዣ ጠፋ ማለት ነዉ፣ የባዕድን ዳቦ እየጎመዱ ለወገን እልቅት የምሟገቱ ከንቱዎች፣ ከንቱ ሆኖ ይቀራሉ።
-
DefendTheTruth
- Senior Member
- Posts: 13240
- Joined: 08 Mar 2014, 16:32