Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Abere
Senior Member
Posts: 15429
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

መለስ ዜናዊ <በብርጭቆ ውሃ ስጡት ብርጭቆውን ሰብሮ ውሃውንም ይደፋዋ> --- < በዱርዬ የፈረሰች አገር በሚልበ ዐብይ አህመድ በታሪክ ያታወሳል> ጌታቸው ረዳ። ከውስጥ አዋቂ ወያኔዎች

Post by Abere » 24 Apr 2023, 09:50

መለስ ዜናዊ <በብርጭቆ ውሃ ስጡት ብርጭቆውን ሰብሮ ውሃውንም ይደፋዋ> --- < በዱርዬ የፈረሰች አገር በሚልበ ዐብይ አህመድ በታሪክ ያታወሳል> ጌታቸው ረዳ። ከውስጥ አዋቂ ወያኔዎች
መለስ ዜናው ሲበዛ መሰሪ፤ ቡዳ እና ምስጢር አዋቂ ነው። ተንኮልን እንደ ኳስ ጢባ ጢቦሽ ነበር የሚጫዎትባት። ያን ችሎታውን ለበጎ ነገር ቢያውለው አገር የት እናን የት ደርሳ በነበር፤ ኢትዮጵያዊ የዜግነት ፍቅር የትናየት በናረ ነበር። ለክፉ ስላዋለው ግን የሰፈር እና የመንደር ፓለቲካ ሁኖ ቀረ እንጅ። ታዲያ አንድ እውነት ተናግሯል ለኦሮሙማ ስልጣን የሰጠ ሰው ለህጻን ልጅ በውድ በተገዛ ብርጭቆ ውሃ መስጠት ነው በማለት። ይህ ታሪካዊ አገላለጽ በ5 አመታ ውስጥ ሙሉ በሙሉ ተረጋግጧል።

በተመሳሳይ እንድሁ በዐብይ አህመድ ነብይነት ፍቅር የተነደፉ እና በሆዳም ውታፍ ነቃይነት የንዋይ ቦርጭ ለማውጣት ለባዘኑት ደግሞ የወያኔው ቃል አቀባይ የአሆኑ መሪ ጌታቸው ረዳ በሰፊ ቃለመጠዬቅ ላይ ስለ አብይ አህመድ ይህን ተመሳሳይ ተናግሮ ነበር። በታሪክ በዱርዬ የፈረሰች አገር ብትኖር ኢትዮጵያ ብቻ ናት ብሎ ነበር። አብይ አህመድ በታሪክ መታወስ የሚችል ሰው አይደለም -ታሪክም ከመሰለው የታሪክ ድርሳን ሁሉ ይገድፉታል አይጽፉትም። ኢትዮጵያ በዱርየ የፈርሰች አገር ትባላለች። ስንቶች የደከሙባት አገር በዱርየ ፈረሰች ይባላል።አሁን ኢትዮጵያ በአስተዳደር እና ፓለቲካ ፈርሳለች ፈራርሳለች ያለችው በባህል ድር ትሥስር ብቻ ነው። ኢኮኖሚ ፈራርሷል (ትቢያ ሁኗል)፤ ስነ-መንግስት ፈራርሷል የመንደ ዱርየ ሰፍኗል (ቤት በመንጋ ያፈርሳል፤በመንጋ ይገድላል፤በመንጋ ሴቶችን ይደፍራል፤ በመንጋ ገንዘብ/ሃብት ይዘርፋል)፤ ማንም የውጭ መንግስታት እንደ ፈለጋቸው ገብተው የፓለቲካ ድርያ ዕውቅና ከሌለው( ህዝብ ከተፋው) ሽፍታ/ዱርየ ጋር ውል ይፈጽማሉ፤ አስገድደው የልዑላዊ ግዛት ይደፍራሉ፤ይነጥቃሉ ፤ የአገር ወታደር የሚባለው ህይወት ከነፍሳት ያነሰ ዋጋ ያጣ ዝም ብሎ ለአገር በማይጠቅም ሁኔታ በየጢሻው እንደ ተባይ ይደፈጠጣል- መኖር እና መሞቱ ቤተሰብ ዘመድ አያውቅ ---- የፈራረሰች አገር። በዱርዬ የፈረሰች አገር ።

Axumezana
Senior Member
Posts: 19172
Joined: 27 Jan 2020, 23:15

Re: መለስ ዜናዊ <በብርጭቆ ውሃ ስጡት ብርጭቆውን ሰብሮ ውሃውንም ይደፋዋ> --- < በዱርዬ የፈረሰች አገር በሚልበ ዐብይ አህመድ በታሪክ ያታወሳል> ጌታቸው ረዳ። ከውስጥ አዋቂ ወያኔዎ

Post by Axumezana » 24 Apr 2023, 11:00

አለቃ፥ አበረ፥ ያለፈው፥ ለትምህርት፥ ቢጠቅምም፥ ትኩረታችን፥ ግን፥ ቀጣይዎ፥ ኢትዮጵያ፥ ምን፥ ትሁን፥ መሆን፥ አለበት፥። መለስ፥ አለ፥ ያልከው፥ ግን፥ዘረኛ፥ አባባል፥ ስለሆነ፥ ማለቱን፥ በማስረጃ፥ አስደግፍ፥ መለስ፥ ህዝብን፥የሚያከብር፥ሰው፥ ነበር፥ አማራ፥ እንደዚህ፥ ነው፥ ኦሮሞ፥እንደዚህ፥ ይላል፥ የሚል፥ ግምት፥ የለኝም። ከከፍታህ፥ እንዳትወርድ፥ መጠንቀቅ፥ ጥሩ፥ ነው።

Abere
Senior Member
Posts: 15429
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: መለስ ዜናዊ <በብርጭቆ ውሃ ስጡት ብርጭቆውን ሰብሮ ውሃውንም ይደፋዋ> --- < በዱርዬ የፈረሰች አገር በሚልበ ዐብይ አህመድ በታሪክ ያታወሳል> ጌታቸው ረዳ። ከውስጥ አዋቂ ወያኔዎ

Post by Abere » 24 Apr 2023, 11:48

አክሱምዒዛና

እነኝህ 2ቱን መለስ ዜናዊ አስገንዝቦ ነበር፤

1ኛ) ኦህዴድ ሲፋቅ ኦነግ ነው። ይህ ማለት ኦህዴድ ውስጡ ሊጥ የሆነ የኦነግ ዳቦ ነው።

2ኛ) እንደ ጦጣ እየሸመጠጠ በጫካ ዘመን መኖር የሚፈልግ ይላል። የዘመናችን ኬኛ ሌሎች ያፈሩትን የእኔ እያለ በሰው ጉልበት በተፈራ ላይ ቁጢጥ የሚለውን ተረኛ ኦሮሙማ ለመግለጽ በተለይ ደግሞ በወለጋ እና በባሌ የሚገኘውን ያልሰለጠነ ዘረኛ ኦሮሙማ ለመግለጽ። ኦሮሙማ ወያኔ አንድም በብልጠት ሁለትም በስህተት የፈጠርኩት ነው ብላ ታምናለች። ይህ ደግሞ ትክክል ነው ።

ሌላም አንድ የምርቃት ላድረግ እስኪ። ይኸውም ቀደም ብየ እንዳልኩት መለስ የመጨረሻ ብልጥ እና መሰሪ ቡዳ ነው። የፈጠረው ኢህአድግ የአገልግሎት ዘመኑን ማጠናቀቁን እና የጎሳ ፓለቲካ የደከማ የአቀበት የጋማ ከብት መሆኑን አበክሮ ስለተገነዘነበ አንድ መላ መትቶ ነበር። ይህም አንድ አገራዊ የፓለቲካ ፓርቲ የሁሉንም ክልል ህዝብ የሚያሳትፍ የሚል። የኢህአድግ የጎመን ምንቸት ውጣ ሊያስብል። ይችን ምስጢር ያወቀው ዱርዬው አብይ አህመድ ስልጣን በማጭበርበር ከያዘ በኋላ ለኦሮሞ ብቻ የሚሰራ ብልጽግና የሚሰኝ የጥፋት ሳጥናኤል (prosperity party) በኢትዮጵያ ህዝብ የሚቀኝ ሳይሆን በጴንጤ እና በኦሮሙማ ስም ፈጠረ። በርካቶች መሬት ላይ ተነጥፈው ተቀበሉት። የማደናገር እና የማሳመን (confuse and convince) የጥፋት ወንጌል ተሰበከ። ሳይቆይም የጥፋት ዶፍ አወረደ። ይህን ሁላችን አይተናል አሁንም ዶፉ እየወረደ ነው - ዱርዬው እስካለ ድረስ የግፍ ዝናብ ይወርዳል።

Axumezana
Senior Member
Posts: 19172
Joined: 27 Jan 2020, 23:15

Re: መለስ ዜናዊ <በብርጭቆ ውሃ ስጡት ብርጭቆውን ሰብሮ ውሃውንም ይደፋዋ> --- < በዱርዬ የፈረሰች አገር በሚልበ ዐብይ አህመድ በታሪክ ያታወሳል> ጌታቸው ረዳ። ከውስጥ አዋቂ ወያኔዎ

Post by Axumezana » 24 Apr 2023, 16:15

ዋናው፥ ጉዳይ፥ ኢትዮጵያን፥ከችግር ፥ እንዴት፥ እናውጣት? መተቸትና፥ እጅ፤ መቀሰር፥ ቀላል፥ ነው።

Abere
Senior Member
Posts: 15429
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: መለስ ዜናዊ <በብርጭቆ ውሃ ስጡት ብርጭቆውን ሰብሮ ውሃውንም ይደፋዋ> --- < በዱርዬ የፈረሰች አገር በሚልበ ዐብይ አህመድ በታሪክ ያታወሳል> ጌታቸው ረዳ። ከውስጥ አዋቂ ወያኔዎ

Post by Abere » 24 Apr 2023, 16:52

መፍትሄው እኮ ግልጽ ነው። የችግሩ ዋና አካል የሆኑት ኦሮሙማ እና ትህነግን በቃችሁ ከ50 አመታት በላይ የስቃይ ዶፍ አዘነባችሁ ማለት ነው። የችግሩን ርዕሰ አካላት ተሸክሞ መጓዝ አይቻልም። በመጨረሻ የሚሆነውም ይህ እወነት ነው። የችግሩ የወጥ ወይም የማዕድ ቤቶች ስራ እናጣለን በሚል ፍራቻ እንጅ መፍትሄው እኮ ቀላል ነው። አገር እና ህዝብ ያወቀው ነው።

Axumezana
Senior Member
Posts: 19172
Joined: 27 Jan 2020, 23:15

Re: መለስ ዜናዊ <በብርጭቆ ውሃ ስጡት ብርጭቆውን ሰብሮ ውሃውንም ይደፋዋ> --- < በዱርዬ የፈረሰች አገር በሚልበ ዐብይ አህመድ በታሪክ ያታወሳል> ጌታቸው ረዳ። ከውስጥ አዋቂ ወያኔዎ

Post by Axumezana » 24 Apr 2023, 16:58

መርዶ፥ እንዳይሆንብህ፥ እንጂ፥ ቁጥር፥ ሁለት፥ ኢህዲግ፥ ብያንስ፥ ለሚቀጥሉት፥ 20፥ አመታት፥ መንበሩን፥ ይዞ፥ ይቆያል።

Abere
Senior Member
Posts: 15429
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: መለስ ዜናዊ <በብርጭቆ ውሃ ስጡት ብርጭቆውን ሰብሮ ውሃውንም ይደፋዋ> --- < በዱርዬ የፈረሰች አገር በሚልበ ዐብይ አህመድ በታሪክ ያታወሳል> ጌታቸው ረዳ። ከውስጥ አዋቂ ወያኔዎ

Post by Abere » 24 Apr 2023, 17:08

የወደቀ የሽብር መንግስት ነው የምታወራኝ። ሞቷል - ኢኮኖሚ የለ፤ህግ የለ፤ ስራ ዕድል የለ፤ ወዘተ። አሜሪካ ወይም የአለም ባንክ ደመወዝ ብትከፍለን እያሉ የሚጠባበቁ ደዌ ናቸው አሁን - ኦሮሙማ እና ትህነግ። እግር እጃቸው ሙቶ ጅቡ ሆዳቸው ቀርቶ የሚለፈልፉ። ኢትዮጵያ አሁን መንግስት ዐልባ አገር ናት። አንዳች መስፈርት የሚያሟላ መንግስት የለም። በናፍቆት ጎዳና ጭልጥ ብለህ ከ5 አመታት በፊት ወደ ነበረው የሄድክ ይመስላል። ከሰመመንህ ንቃ! :mrgreen:

Post Reply