Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
-
Horus
- Senior Member+
- Posts: 42789
- Joined: 19 Oct 2013, 19:34
Post
by Horus » 18 Apr 2023, 22:24
አብዮታዊ ሁኔታ (Revolutionary Situation) ምን ማለት ነው? አብዮታዊ ሁኔታ ተፈጠረ ማለት መንግስት መግዛት አቅቶታል ፤ ሕዝብ አልገዛም ብሏል ማለት ነው ። መንግስት መግዛት የማይችልበት ብዙ ምክኛቶች ቢኖሩም ዋናው የሕዝብ እምቢተኝነት ነው ። ሕዝብ አልገዛም የሚልበት ብዙ ምክኛቶች ቢኖሩማ በኢኮኖሚ ውድቀትና በመንግስት ጭቆና ብዛት ሕዝብ በቃኝ ሲል ነው ።
ይህው ዛሬ ትግሬ ቀውስ ውስጥ ነው!
አማራ አልገዛም ብሏል!
አዲስ አበባ ሊፈነዳ ደርሷል!
መንግስት ጅምላ አፈሳማ እንግልት አስፍኗል
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተማሪ ንቅናቄ ሊጀርም ጫፍ ደርሷል!
ጉራጌ አልገዛም ብሏል!
ሃዲያ መንገድ ዘግቶ እያማጸ ነው!
የወላይታ ሕዝብ ልክ እንደ ጉራጌ በገፍ እየታሰረ ነው!
ሸኔ አማራን ብቻ ሳይሆን አፋርን መውጋት ጀምሯል!
የሱማሌና ኦሮሞ ዉጊያ
የኦሮሞና ሲዳማ ዉጊያ
የሱማሌና አፋር ...
ሁሉም ሁሉም የሚያሳዩን ቀስት አገር አቀፍ አብዮታዊ ሁኔታ !!!!
ሞት ቢዘገይ የቀረ ይመስላታል !!
-
Union
Post
by Union » 18 Apr 2023, 22:35
ኢትዮጵያ ልትፈርስ ነው። ኢትዮጵያዊያንን ነጮቹ ብዙ እንቨስት አድርገው እርስ በእርሳቸው ሊያጨፋጨፉአቸው ነው። በቃ አለቀላቸው። ተበታትነዋል። ምናምን ምናምን ሲሉ እንዳልነበረ። እሳቱ ወደ እራሳቸው ዞረባቸው። ይኸው ኡ ኡ ኡ ኡ ኡ እያሉ ነው። ገና መጀመሩ ነው።
አፋር አስጠንቅቋል፣ ሱማሌም እንደዛው። ጉራጌ ከሸፈተ ቆየ፣ ደቡብ ደግሞ የጉራጌን እንቅስቃሴ የመከተል አዝማሚያ አላቸው። ሁሉም እየገባ ነው!!
ጥንታዊው የኢትዮጵያዊያኖች አምላክ እየመጣ ነው!!!
-
Horus
- Senior Member+
- Posts: 42789
- Joined: 19 Oct 2013, 19:34
Post
by Horus » 19 Apr 2023, 00:13
union,
The Dictator's Handbook ብታነብ ብትክክል ይህን ነው የሚለው፤ ማለትም ዲክታተሩ ቁልፍ ደጋፊው (3ኛው ምሰሶ) ፋይናንስ የሚያደርግበት (ደሞዝ፣ ጉቦ፣ ስጦታ፣ ቤ፣ መኪና፣ ሽልማት ወዘተ) ገንዘብ ስካለው ድረስ በአመጽ፣ በፖሊስ ኃይል ስልጣን ላይ ይቆያል ። ይህ ደጋፊው ቡድን መክዳትና መፍረከለክ ወደ ሌላ መሪና መፍትሄ መመልከት የሚጀምረው ያ ደሞዙና ጥቅማ ጥቅሙ ሲቀረበት ወይም የመቅረት አደጋ ሲያንዣብብ ነው ይላል ።
ሃዲያ መንገድ የዘጉት (ትልቁ ከአርባ ምንጭ ጋራ የሚያገናኘው) እራሳቸው ብልጽግናዎች ናቸው ፣ የደቡብ መንግስት ሰራተኛ ማለት የደቡብ ብልጽኛ ማለት ነው ። የጉራጌ ብልጽግናዎች ክልል በመጠየቅ ኮማንድ ፖስት ተትሎባቸው እስር ቤት ናቸው (ወይም ፍርድ ቤት እየተመላለሱ ነው) ። የወላይታ ብልጽግናዎች መርጫ አሻጥራችኋል በሚል እየታሰሩ ነው ። (የወላይታ ክለስተር ምርጫ መዘረዙን ታስታውሳለህ) ። ጋሞ ድሮም ካቢይ ጋር ችግር ያለው ሕዝብ ነው ። በአንድ ቃል ደቡብ የሚባለው ነገር የለም፣ ደሞዝ መክፈል አይችልም፤ ቢሮክራሲው እየፈረሰ ነው ።
ይህ ማለት ሁለቱ ግዙፍ ክልሎች አማራና ደቡብ እንደ መንግስት እየፈረሱ ነው ። የትግሬ ነገር ይታወቃል ። አፋር በቅርብ የንጉስ አሊ ሚራህን አልጋ ወራሽ አንግሷል ። አፋር ልክ እንደ ድሮ ራሱን የቻለ አይነኬ ሕዝብ ነው ። ለዚህ ነው አሁን ሺመልስ የሸዋ ሸኔ እየላከ የሚለክፋቸው!!! አላርፍ ካለ ደሞ ፈሱን ያዳምጡለታል ። አፋር ስይነኩት ሰው አይነካም! ደሞ ከነኩት ምን እንደ ሚያደርግ እናውቃለን !
ስለዚህ የአቢይ አህመድ 'ብሄራዊ' ጦር ይከፋፈላል ። ለዚህ የሚረዳው በትንሹ የሱዳን ጉዳይ ነው ። አሁን ምን አለ በል፣ ግብጽ ልትወጋን ነው ብሄራዊ ስሜት ለመቀስቀስ ሲሞክር ታየዋለህ በቅርብ ቀናት !
ዶሜስቲካሊ መንግስት ፈርሷል፣ እየፈረሰ ነው !