እናሳ በዚህ አገር አቀፍ አይቀሬ ትግል፣ ፍልሚያ፣ ጦርነት ወዳጅ ማነው? ጠላት ማነው? ይህ ትግል በማና በማን መሃል ነው? እነዚህ ጥያቄዎች አለመመለስ፣ ለመመለስ አለመፈልግ፣ ከመፈለግ መደበቅ ኋላ ላይ ያስከፍላል!
በሬ ካራጁ ስለሚውል ማለት ነው !
መልሱ አንድ መስመር ነው ። በኢትዮጵያ ያለው ዋና መሰረታዊ ቅራኔ በኢትዮጵያ ሕዝብና በብልጽግና ፓርቲ መሃል ነው ። የኢትዮጵያ ሕዝብ ዋና ጠላት የብልጽግና ፓርቲ ነው ። በዚህ ዋና ኡኒቨርሳል ቅራኔ ስር እልፍ አይነት ሌሎች መለስተኛ ቅራኔዎች አሉ ። ካስፈለገ በጎስ ፖለቲካና በዜጋ መሃል እንበለው፣ በአምባ ገነነትና በዴሞክራሲ መሃል እንበለው፣ የሁሉም መቁጠሪያ ቅራኔና ትግል ያለው በኢትዮጵያ ጠላት የብልጽግና ፓርቲ አገዛዝና በኢትዮጵያ ሕዝብ መሃል ነው ።
ነገ ታሪክ የሚያረጋግጠው ይህን ሃቅ ነው ።