Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Meleket
Member+
Posts: 5070
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Zmeselo ይህ ኤርትራን የተመለከተ ዜና ምን ያህል እውነት ነው? እባክህ ንገረን!

Post by Meleket » 12 Apr 2023, 09:18

Zmeselo ይህ ኤርትራን የተመለከተ ዜና ምን ያህል እውነት ነው? እባክህ ንገረን!

እርግጥ "በኤርትራ ዘመናዊ የሆነ የውስጥ አካላትን የሚያሳይ መሳሪያ (ኤምአርአይ)" ዬለምን? ታዲያ ለዚያ ነውን ዕድሉን ያገኙት በርካታ ኤርትራውያን ለህክምና ከኤርትራ ውጭ ሲጓዙ ዬሚታዩት?

ለምንድን ነው ሃገረ ኤርትራ ቢያንስ ቢያንስ በ6ቱ ዞባዎቿ ኣንድ ኣንድ (ኤምአርአይ) ለመትከል ያልበቃችው? እውን ይሄን ማድረግ ለአንዲት ሃገር ከባድ ነገር ነውን? ዘሜ Zmeselo እስቲ እውነተኛ መረጃ በማቅረብ እውነቱን ንገረን፡ ምክንያቱም የዚህን ዜና ጤነኝነት ተጠራጥረናል፡ እኛ ኤርትራዉያን የመሃልና የመስመር ዳኞች
:mrgreen:
በኤርትራ ጭንቅላታቸው ተጣብቆ የተወለዱት ህጻናት ከአገር ውጭ መታከም አለባቸው ተባለ


ዶ/ር ዘሚካኤል ተጣብቀው ከተወለዱት መንታዎች ጋር

ኤርትራ ውስጥ ጭንቅላታቸው ተጣብቆ የተወለዱትን ጨቅላዎች በቀዶ ሕክምና ለማላቀቅ ከአገር ውጭ ሄደው መታከም አለባቸው ተባለ።

ከሁለት ወራት በፊት በከረን ሆስፒታል ተጣብቀው የተወለዱት ጨቅላዎች በመዲናዋ አሥመራ በሚገኘው ኦሮታ ሆስፒታል ክትትል እየደረገላቸው ይገኛሉ።

በሆስፒታሉ የሕጻናት ሕክምና ክፍል ኃላፊ ዶ/ር ዘሚካኤል ዕቁብ ጨቅላዎቹ የቅርብ ክትትል እያደረገ ቢገኝም ጭንቅላታቸውን ለማላቀቅ ቀዶ ሕክምናው ከኤርትራ ውጭ መደረግ አለበት ሲሉ ለቢቢሲ ትግርኛ ገልጸዋል።


ዶ/ር ዘሚካኤል ለመንትያዎቹ ሴት ጨቅላዎች የቅርብ ክትትል እየተደረገላቸው እና አካላዊ እድገትም እያሳዩ መሆኑን ተናግረዋል።

እንደ ጤና ባለሙያው ከሆነ በመሰል ሁኔታ ጨንቅላታቸው ተጣብቆ የሚወደለዱ ልጆችን በቀዶ ሕክምና ከመለያየት በፊት ሕጻናቱ ሁለት ዓመት እስኪሞላቸው መጠበቅ ግድ ሊሆን ይችላል ብለዋል።

በኤርትራ ዘመናዊ የሆነ የውስጥ አካላትን የሚያሳይ መሳሪያ (ኤምአርአይ) ባለመኖሩ የጨቅላዎቹ ጨንቅላት የውስጥ ክፍል በምን አይነት ሁኔታ ተጣብቆ እንዳለ ለማወቅ አዳጋች እንደሆነባቸው ዶ/ር ዘሚካኤል ጨምረው ተናግረዋል።

“እዚህ ጥርት ባለ ሁኔታ የሚያሳይ ‘ኢሜጂንግ ሥርዓት’ ስለሌለ የትኛው የአዕምሮ ከፍላቸው ተገናኝቶ እንዳለ ማወቅ አልቻልንም” ብለዋል።


ዶ/ር ዘሚካኤል ለጨቅላዎቹ ቀዶ ጥገናው የሚደረግላቸው በማን እና በየትኛው አገር የሚለውን የሚወስነው የአገሪቱ ጤና ሚንስቴር መሆኑን ጨምረው ተናግረዋል።

“ከዚያ በፊት ግን እነዚህ ህጻናት የተጣበቀው የትኛው የአእምሯቸው ክፍል ነው? የሚጋሩት የአእምሮ ክፍል አለ? የሚለውን ለመለየት ከፍተኛ ጥራት ባለው ኤምአርአይ መታየት አለበት” ብለዋል።

የሕጻናት ሐኪሙ ዶ/ር ዘሚካኤል ጨንቅላታቸው ተጣብቀው የሚወለዱ ሕጻናትን ለመለያየት የሚደረገው ቀዶ ሕክምና ረዥም ጊዜ የሚወስድ፣ ውስብስብ እና በርካታ ባለሙያዎችን የሚጠይቅ ከመሆኑም ነው።

በተጨማሪ ህክምናው እጅግ ዘመናዊ መሳሪያዎች እንደሚያስፈልጉት የገለጹት ዶክተሩ፣ ጨቅላዎቹን የመለየት ህክምናው ከተደረገ በኋላ በሕይወት የመትረፍ ዕድላቸው ጠባብ መሆኑን ጠቅሰዋል።

“በጭንቅላታቸው ተጣብቀው የተወለዱ ሕፃናት በቀዶ ሕክምና የመትረፍ ዕድላቸው ከ20 አስከ 30 በመቶ ነው። አብዛኞቹ በሕይወት የመትረፍ ዕድል የላቸውም” ይላሉ።

ዶ/ር ዘሚካኤል እንደሚሉት ከሴት እንቁላል እና ከወንድ የዘር ፍሬ የተፈጠረ ጽንስ በሁለት ሳምንት ጊዜ ውስጥ ውህደት ፈጥረው በመከፈል መንታ ልጆች ሊጸነሱ ይችላል።

“መከፋፈሉ ጊዜውን ጠብቆ የሚጨርስ ከሆነ መንታ ጽንስ ይፈጠራል፤ የመከፋፈሉ ሂደት ሳይጨረስ ከቀረ ግን ሕጻናቱ በአንድ የአካላቸው ክፍል በኩል ተጣብቀው ሊወዱ ይችላሉ” በማለት ሕጻናት እንዴት ተጣብቀው እንደሚወለዱ ያስረዳሉ።

እንደዚህ አይነት ክስተት ተመሳሳይ መንትያ (አይደንቲካል ትዊንስ) በሆኑት ላይ እንደሚያጋጥም የሚናገሩት የጤናው ባለሙያ፤ ተጣብቆ የመወለድ ዕድል ሊያጋጥም የሚችለው ከ2.5 ሚሊዮን ውልደት በአንዱ ላይ ነው ይላሉ።

ዶ/ር ዘሚካኤል ከዚህ ቀደም ጭንቅላታቸው ተጣብቆ የተወደሉ ሕጻናት ገጥሟቸው እንደማያውቅ ተናግረው፤ ሆዳቸው ተጣብቀው የተወለዱ ሕፃናት ግን ወደ ጤና ተቋማቸው መጥተው እንደነበረ ያስታውሳሉ።

ከ 15 ዓመታት በፊት ደግሞ ሁለት ጭንቅላት ያለው ልጅ ተወልዶ እንደነበረ የጠቀሱት ሐኪሙ፣ በዚህም ክስተት የተወለደው ልጅ አንዱ ጨንቅላት ሙሉ በሙሉ ያደገ እና ሌላኛው በሙሉ ያላደገ እና ሕይወት እንዳልነበረው በመግለጽ ሕይወት የሌላው ጭንላት እንዲወገድ መደረጉን ያስታውሳሉ።

ለዚህ ታዳጊ ሕክምናው በኤርትራ ከተደረገ በኋላ አሁን ስላለበት ሁኔታ የሚያውቁት ነገር እንደሌለ ዶ/ር ዘሚካኤል ለቢቢሲ ትግርኛ ገልጸዋል።

“ልጁ የት እንዳለ አናውቅም ምክንያቱ ደግሞ ሕብረተሰቡ ለመሰል ክስተቶች ያለው አመለካከት የተሳሳት ነው። ቤተሰብም ለክትትል እንዲመጡ ተነግሯቸው አልተመለሱም” ብለዋል።

በማዕከላዊ ኤርትራ ዓንሰባ ዞን ሊበን ተብሎ በሚጠራ ስፍራ ነዋሪ የሆኑት የጨቅላዎቹ ወላጅ እናት ወይዘሮ ኡሙና መሐመድ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።

https://www.bbc.com/amharic/articles/cg3zkjjy0gjo
የነጻነት ታጋዩና የሕጻናት ሐኪሙ ዶ/ር ዘሚካኤል ባንድ ወቅት እንዲህ ብለው ነበር "እድገቴ በካቶሊክ ሲስተሮች ጥረትም ነው።" በአ/አ ዩኒቨርሲቲ ይሁን በጀነራል ዊንጌት ት/ቤት ዘነጋነው እንጂ ዶ/ር ዘሚካኤል ከቀድሞው ነፍስኄር ጠቅላዪ መለስ ዜናዊ ጋር ባንድ ላይ የተማሩና፡ በአንድ ክፍል ውስጥም ይኖሩ ነበር። ታድያ ያኔ ለገሰ ዜናዊን "ትሪባ" በሚል ቅጽል ስም ነበር የምንጠራው ብለው ሲናገሩ ሰምተናቸው ነበር፡ እኒህ ታታሪና የስንት ህጻናትንና እናቶችን ህይወት ዬታደጉ ታጋዪ ሐኪም። ኣምላክ ዕድሜና ጤና ይሰጣቸው ዘንድም ተመኝተንላቸዋል እኛ ኤርትራዉያን የመሃልና የመስመር ዳኞች፡ በኤርትራዊ ጭዋነት ኩራትና ትህትና ጭምር። :mrgreen:

Meleket
Member+
Posts: 5070
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: Zmeselo ይህ ኤርትራን የተመለከተ ዜና ምን ያህል እውነት ነው? እባክህ ንገረን!

Post by Meleket » 13 Apr 2023, 04:05

ዘሜ Zmeselo ስራ በዝቶበት ነው ወይስ "ኣብሪል 13" ላይ ሆኖ ስለ "ፊዚካል ዲማርኬሽን" ለመናገር ባለመቻሉ ኣሳፍሮት . . . ኣዬ የካድሬ ነገር! :mrgreen:

sesame
Member+
Posts: 8554
Joined: 28 Feb 2013, 17:55

Re: Zmeselo ይህ ኤርትራን የተመለከተ ዜና ምን ያህል እውነት ነው? እባክህ ንገረን!

Post by sesame » 13 Apr 2023, 08:13


ልመለኸት ዕንክሊሎ
ታይዩ ልቐርጾ ለሎ

Please wait, video is loading...

Meleket
Member+
Posts: 5070
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: Zmeselo ይህ ኤርትራን የተመለከተ ዜና ምን ያህል እውነት ነው? እባክህ ንገረን!

Post by Meleket » 13 Apr 2023, 09:51

ተራ ካድር sesame ኩሕሎ፡
"ፊዚካል ዲማርኬሽን" ይጸልእ ኣሎ፡ . . . ይበሃል ኣሎ!

ስለምንታይ እንተተባህለ፡
ነገር ሓናኺሩ እናፈተለ፡

ካብ ህግን ሓቅን ኅልናኡን እናተከወለ፡
"ኣይተኣዘዝኩን' ምበለ።
:mrgreen:

sesame
Member+
Posts: 8554
Joined: 28 Feb 2013, 17:55

Re: Zmeselo ይህ ኤርትራን የተመለከተ ዜና ምን ያህል እውነት ነው? እባክህ ንገረን!

Post by sesame » 13 Apr 2023, 16:01

Deacon Meleket,

This is how Eritros are celebrating after breaking the back of the Agame Junta! Enjoy if you can, and please don't tell me it is Som ArbEa!
:lol: :lol:
Please wait, video is loading...

Post Reply