Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
-
Meleket
- Member
- Posts: 3989
- Joined: 16 Feb 2018, 05:08
Post
by Meleket » 09 Nov 2022, 10:35
የኤርትራ እና የኢትዮጵያ 146ቱ የጋራ ፈርጦች! - የ146ቱ ካምፖች ወግ!
ጐበዝ እነዚህ 146 የጋራ ፈርጦቻችን ከነ 'ኮኦርዲኔታቸው' በማያሻማ መልኩ “ይግባኝ በማይባልበት” ፍርድ ተወስነው፡ ቁልጭ ብለው ትግባሬን እየጠበቁ የተቀመጡ ናቸው።
https://legal.un.org/riaa/cases/vol_XXVI/771-799.pdf
ታድያ ሃገራችን ኤርትራና ጐረቤቷ ኢትዮጵያ በሰላም ይኖሩ ዘንድ፡ እንዲህ ቢደረግ ምን ይመስላችኋል?
1.) በ146ቱ ነጥቦች፡ በያንዳንዷ ስፍራ የጋራ ወታደራዊ ካምፕ በመገንባት የደንበር ጸጥታ አስከባሪ ሃይል ማስፈር።
2.) በ146ቱ ካምፖች የሚኖሩት የሁለቱ ሃገራት የሰራዊት ብዛት 80 ከኢትዮጵያ (ሁሉን ኢትዮጵያዊ ብሄር ብሄረሰቦች የወከለ እንዲሆን ማለትም ኣልተወከልኩም የሚል ኢትዮጵያዊ ብሄር እንዳይኖር ማለት ነው።) ኤርትራም በበኩሏ ከ80 ያልበለጡ የሰራዊቷ ኣባሎችን በነፍስወከፍ 146ቱ ካምፖች ውስጥ እንድታስቀምጥ ማድረግ።
3.) ይህም ማለት 146*80 = እያንዳንዷ ሃገር ቢያንስ ቢያንስ 11,680 በወታደራዊ ዲሲፕሊን የተመሰከረላቸውን የሰራዊት አባሎቿን ለድንበር ጥበቃ እንድታሰማራ ማድረግ። ይህ የሁለቱ ሃገራት መንግስታት የሰራዊት ክፍል፡ ፈጣን በሆነ ዘመናዊ የመገናኛ መሳርያዎች የታጠቀ ማድረግ። [ስለ ወጪው አትጨነቁ፡ የሁለቱ ሃገራት ህዝብ ሊሸፍነው ይችላል፤ የሁለቱ ሃገራት ህዝብ በረባ ባልረባው ከመናቆር፡ ገንዘብ አዋጥቶ ሰላሙን ማስጠበቅ ይቀለዋል!]
4.) የሁለቱም ሃገሮች የአየር ሃይል፡ ሃገሮቹ ዬተስማሙባቸውን ያህል የአሰሳና ዳሰሳ ሂሊኮፕተሮችና ድሮኖች ለዚሁ ድንበር ጸጥታ መመደብ። [በሂሊኮፕተርና በድሮን ከመጨፋጨፍ ይሄ ሳይሻል ኣይቀርም ትላላችሁን?]
5.) በዚህ መሰረት፡ በድንበር አካባቢ ምናልባት ሊፈጥር የሚችልን ግጭት በግዜ ማጤንና ፈጣን ፈውስ በመሻት እልባት ላይ ማድረስ።
በዚህ መልኩ “ፊዚካል ዲማርኬሽኑን” ብንጀምረው የሁለቱ አጎራባች ሃገሮች ህዝቦች ዘለቄታዊ ሰላምና እፎይታን ለማግኘትና ለማጣጣም አይችሉም ትላላችሁን? እስከ መቼ ድረስ እርስ በእርስ ማናቆር ጐበዝ!
ለዛሬ 146 የጋራ ፈርጦቻችንን እዚህ ተመልከቷቸው!ከገጽ 786-794 ወይም ከ ገጽ 17-25 ቁልጭ ብለው አሉላችሁ።
ጐበዝ "ፊዚካል ዲማርኼሽኑ" በዚህ ሃሳብ አኳያ ቢተገበር ምን ይመስላችኋል? እስቲ የሚጐድለውን አጉድላችሁ፡ የሚጨመረውን ጨምራችሁ ሃሳባችሁን አክሉበትና ወደ ትግባሬ እናምራ። የየሃገሮቻችን ቦተሊከኞቻችንን እንዲህ አድርገን 'ጭራውን መያዝ' የፈሩትን ነገር በማደፋፈር እናግዛቸው እንጂ ጐበዝ! አይመስላችሁም። "ፊዚካል ዲማርኼሽን ይቻላል!"
ተጻፈ፡ በኤርትራውያን የመሃልና የመስመር ዳኞች፡ በኤርትራዊ ጭዋነት ኩራትና ትህትና ጭምር። ![Mr. Green :mrgreen:](./images/smilies/icon_mrgreen.gif)
-
Meleket
- Member
- Posts: 3989
- Joined: 16 Feb 2018, 05:08
Post
by Meleket » 10 Nov 2022, 04:14
እንጠረጥራለን፡ ለዘለቄታዊ ሰላም ሲባል፡ ናይሮቢ ላይ "የኤርትራ እና የኢትዮጵያ 146ቱ የጋራ ፈርጦች!" የመወያያ ኣርእስትም ሊሆኑ እንደሚችሉ! ![Mr. Green :mrgreen:](./images/smilies/icon_mrgreen.gif)
-
Meleket
- Member
- Posts: 3989
- Joined: 16 Feb 2018, 05:08
Post
by Meleket » 15 Nov 2022, 06:07
ኤርትራውያን "ናትና ኣይንህብን ዘይናትና ኣይንደልን!" የምትል የትግል መርህ አለችን። ይህ ማለት ደግሞ ከነዚህ ከ146 የጋራ ፈርጦቻችን ወዲያ ኢትዮጵያ ከኛ የምትሻው ቅንጣት ታህል መሬት ሊኖር አይገባም፤ እኛም እንዲሁ እንደማለት ነው። ኣይደለም እንዴ?
ፈጣሪ እጅግ አድርጎ ከባረካቸው ቀናት አንዷ "ይግባኝ የሌለበት ፍርድን" እንቀበላለን ተብሎ የተፈረመባት ዕለት ኣንዷ ነች፤ ሁለተኛዋ ደግሞ "ብይኑ የተበየነባት" ዕለት ነች። ሌሎች የተባረኩ ቀናትም ሞልተዋል። ![Mr. Green :mrgreen:](./images/smilies/icon_mrgreen.gif)
-
Meleket
- Member
- Posts: 3989
- Joined: 16 Feb 2018, 05:08
Post
by Meleket » 26 Nov 2022, 04:06
ፈጣሪን '146 የጋራ ፈርጦች' ስለሰጠን እጂግ እናመሰግነዋለን።
ለኤርትራና ለኢትዮጵያ ህዝብ ቀጣዩዋ እጂግ የተባረከችው ዕለት "ይግባኝ የማይባልበቱ ብዪን መሬቱ ላይ መተግበር የሚጀመርባት ዕለት ነች" ይቺ ህዝባችን በጉጉት የሚጠብቃት ዕለት ግን መቼ ትሆን? ![Mr. Green :mrgreen:](./images/smilies/icon_mrgreen.gif)
-
Meleket
- Member
- Posts: 3989
- Joined: 16 Feb 2018, 05:08
Post
by Meleket » 30 Nov 2022, 04:31
የማርያም ልጆችን በሙሉ "እንኳን ለህዳር ጽዮን ኣመታዊ ክብረበዓል ኣደረሳችሁ" ለማለት ነው።
እምዬ ማርያም ኣንድያ ልጇን በጥበቧ እነዚህ 146 የጋራ ፈርጦቻችንን "ፊዚካሊ ዲማርኬት" አስደርጎ ሙሉ ሰላም በኣፍሪካ ቀንድ ያሰፍንልን ዘንድ ሹክ ትበልልን።
"146ቱ የጋራ ፈርጦቻችን የዘላቂ ሰላማችን ዋስትኖች ናቸው!" ቢለና እኛ ኤርትራውያን የመሃልና የመስመር ዳኞች፡ በኤርትራዊ ጭዋነት ኩራትና ትህትና ጭምር።
-
Meleket
- Member
- Posts: 3989
- Joined: 16 Feb 2018, 05:08
Post
by Meleket » 16 Dec 2022, 09:29
Meleket wrote: ↑09 Nov 2022, 10:35
የኤርትራ እና የኢትዮጵያ 146ቱ የጋራ ፈርጦች! - የ146ቱ ካምፖች ወግ!
ጐበዝ እነዚህ 146 የጋራ ፈርጦቻችን ከነ 'ኮኦርዲኔታቸው' በማያሻማ መልኩ “ይግባኝ በማይባልበት” ፍርድ ተወስነው፡ ቁልጭ ብለው ትግባሬን እየጠበቁ የተቀመጡ ናቸው።
https://legal.un.org/riaa/cases/vol_XXVI/771-799.pdf
ታድያ ሃገራችን ኤርትራና ጐረቤቷ ኢትዮጵያ በሰላም ይኖሩ ዘንድ፡ እንዲህ ቢደረግ ምን ይመስላችኋል?
1.) በ146ቱ ነጥቦች፡ በያንዳንዷ ስፍራ የጋራ ወታደራዊ ካምፕ በመገንባት የደንበር ጸጥታ አስከባሪ ሃይል ማስፈር።
2.) በ146ቱ ካምፖች የሚኖሩት የሁለቱ ሃገራት የሰራዊት ብዛት 80 ከኢትዮጵያ (ሁሉን ኢትዮጵያዊ ብሄር ብሄረሰቦች የወከለ እንዲሆን ማለትም ኣልተወከልኩም የሚል ኢትዮጵያዊ ብሄር እንዳይኖር ማለት ነው።) ኤርትራም በበኩሏ ከ80 ያልበለጡ የሰራዊቷ ኣባሎችን በነፍስወከፍ 146ቱ ካምፖች ውስጥ እንድታስቀምጥ ማድረግ።
3.) ይህም ማለት 146*80 = እያንዳንዷ ሃገር ቢያንስ ቢያንስ 11,680 በወታደራዊ ዲሲፕሊን የተመሰከረላቸውን የሰራዊት አባሎቿን ለድንበር ጥበቃ እንድታሰማራ ማድረግ። ይህ የሁለቱ ሃገራት መንግስታት የሰራዊት ክፍል፡ ፈጣን በሆነ ዘመናዊ የመገናኛ መሳርያዎች የታጠቀ ማድረግ። [ስለ ወጪው አትጨነቁ፡ የሁለቱ ሃገራት ህዝብ ሊሸፍነው ይችላል፤ የሁለቱ ሃገራት ህዝብ በረባ ባልረባው ከመናቆር፡ ገንዘብ አዋጥቶ ሰላሙን ማስጠበቅ ይቀለዋል!]
4.) የሁለቱም ሃገሮች የአየር ሃይል፡ ሃገሮቹ ዬተስማሙባቸውን ያህል የአሰሳና ዳሰሳ ሂሊኮፕተሮችና ድሮኖች ለዚሁ ድንበር ጸጥታ መመደብ። [በሂሊኮፕተርና በድሮን ከመጨፋጨፍ ይሄ ሳይሻል ኣይቀርም ትላላችሁን?]
5.) በዚህ መሰረት፡ በድንበር አካባቢ ምናልባት ሊፈጥር የሚችልን ግጭት በግዜ ማጤንና ፈጣን ፈውስ በመሻት እልባት ላይ ማድረስ።
በዚህ መልኩ “ፊዚካል ዲማርኬሽኑን” ብንጀምረው የሁለቱ አጎራባች ሃገሮች ህዝቦች ዘለቄታዊ ሰላምና እፎይታን ለማግኘትና ለማጣጣም አይችሉም ትላላችሁን? እስከ መቼ ድረስ እርስ በእርስ ማናቆር ጐበዝ!
ለዛሬ 146 የጋራ ፈርጦቻችንን እዚህ ተመልከቷቸው!ከገጽ 786-794 ወይም ከ ገጽ 17-25 ቁልጭ ብለው አሉላችሁ።
ጐበዝ "ፊዚካል ዲማርኼሽኑ" በዚህ ሃሳብ አኳያ ቢተገበር ምን ይመስላችኋል? እስቲ የሚጐድለውን አጉድላችሁ፡ የሚጨመረውን ጨምራችሁ ሃሳባችሁን አክሉበትና ወደ ትግባሬ እናምራ። የየሃገሮቻችን ቦተሊከኞቻችንን እንዲህ አድርገን 'ጭራውን መያዝ' የፈሩትን ነገር በማደፋፈር እናግዛቸው እንጂ ጐበዝ! አይመስላችሁም። "ፊዚካል ዲማርኼሽን ይቻላል!"
ተጻፈ፡ በኤርትራውያን የመሃልና የመስመር ዳኞች፡ በኤርትራዊ ጭዋነት ኩራትና ትህትና ጭምር።
-
sarcasm
- Senior Member
- Posts: 10789
- Joined: 23 Feb 2013, 20:08
Post
by sarcasm » 14 Jan 2023, 21:38
ምሕንጻጽ ዶብ ሻዕብያ ድዩ ዋላ ሕወሓት ሓንጊዱ? FAO Eripoblikan & Meleket - Why Isiais doesn't want demarcation & he won't let it happen
Please wait, video is loading...
-
Meleket
- Member
- Posts: 3989
- Joined: 16 Feb 2018, 05:08
Post
by Meleket » 16 Jan 2023, 10:49
ወዳጃችን sarcasm ለ"ፊዚካል ዲማርኬሽን" እንቅፋት ሆኖ የቆየውማ፡ ለዓመታት በዓለሙ ፍርድ ቤት የተበየነውን፡ ይግባኝ የማይባልበትን ብይን ከመተግበር ይልቅ ኣሻፈረኝ በማለት "ዲያሎግ" የሚል ቅድመ ሁኔታ የፈጠረው፡ በሕወሓት የሚመራው የጦቢያ መንግሥት ነበር።
እንደምታውቀው ላለፉት በርካታ ዓመታት ሕወሓት 1100 መግለጫወችን ስታወጣ፡ "ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ከዛሬ ጀምሮ 'ፊዚካል ዲማርኬሽን' እንዲተገበር እንጠይቃለን" ብላ መግለጫ ለመስጠት ሳትበቃ፡ የእፍረት ካባዋን ተከናንባለች።
ለዚህም ነው "ህግ የማይገዛውን . . . " የሚባለው! መቼም ሕወሓት የኤርትራ ሕዝብ ሰራዊትና መንግሥትን ትዕግስት ለዓመታት ለመፈታተን ሞክራ ነበር፡ ኣሁን ግን ከባለፈው 'የትዕቢት ጉዞዋ' ተምራ፡ "ኣልቻልኩም" የሚለውን ዜማ እያዜመች በጠቅላዪ ኣብዪ ብልጽግናዊ የመደመር ኣመራር እየተመራች "ፊዚካል ዲማርኬሽንን" መተግበር ነው የሚያዋጣት፡ ለቀጠናችን ዘላቂ ሰላም የሚያዋጣው ብቸኛው መንገድ ይህ ስለሆነ። ኣይደለም እንዴ ወዳጃችን sarcasm?
sarcasm wrote: ↑14 Jan 2023, 21:38
ምሕንጻጽ ዶብ ሻዕብያ ድዩ ዋላ ሕወሓት ሓንጊዱ? FAO Eripoblikan & Meleket - Why Isiais doesn't want demarcation & he won't let it happen
Please wait, video is loading...
-
Meleket
- Member
- Posts: 3989
- Joined: 16 Feb 2018, 05:08
Post
by Meleket » 06 Feb 2023, 10:05
ኢትዮጵያውያን ጎረቤቶቻችን ፈጣሪ እንኳን ይህንን ለማዬት ኣበቃችሁ። ጉዳያችሁን በጠረጴዛ ዙርያ ለመፍታት መጣራችሁ እጅግ የሚደነቅ ተግባራችሁ ነው። በቀጠናችን እውነተኛ ሰላም ይሰፍን ዘንድም "ፊዚካል ዲማርኬሽን ኣሁኑኑ" የሚል መግለጫ በማውጣት፡ ለኤርትራና ኢትዮጵያ የአዋሳኝ ህዝቦች ዘላቂ እፎይታ መፍጠር ይጠበቅባቸዋል፡ በዚህ ስብሰባ ውስጥ የተካፈላችሁ ኣካላት በሙሉ ለማለት ነው፡ በኤርትራዊ ጭዋነት ኩራትና ትህትና ጭምር።
![](https://ichef.bbci.co.uk/news/800/cpsprodpb/da45/live/6678e5a0-a3e9-11ed-9883-512178163a9f.jpg)
-
Meleket
- Member
- Posts: 3989
- Joined: 16 Feb 2018, 05:08
Post
by Meleket » 08 Apr 2023, 05:31
"ሳዕስዕ'ሞ 'ፊዚካል ዲማርኬሽን' ኣይትረስዕ!" ዘመናዊት ምስላ ደቂ ኤርትራ ኣብ ወርሒ "ኣብሪል" ተባሂላ ኣብ ታሪኽ ክትምዝገብ ንሓትት፡ ንሕና ኤርትራውያን ደያኑ ማእከልን መስመርን፡ ብኤርትራዊ ጭዉነት ሓበንን ፍናንን!
![](https://tesfanews.net/wp-content/uploads/2015/03/Lord_Avebury_letter_ethiopia.jpg)
-
Meleket
- Member
- Posts: 3989
- Joined: 16 Feb 2018, 05:08
Post
by Meleket » 13 Apr 2024, 06:10
ዝክረ ሚያዝያ 13 2002 እ.ኤ.ኣ ![Mr. Green :mrgreen:](./images/smilies/icon_mrgreen.gif)