Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 42799
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ቦንጋ በጉራጌ ጉዳይ ቀይ መስመር አለፈ! የፖለቲካ መጃጀት ይሏል እንዲህ ነው!

Post by Horus » 24 Mar 2023, 01:50

የሰው ልጅ እድሜው ሲገፋ አንድ ትልቅ ጸሎቱ አሟሟቴን አሳርልኝ ይላል ! ያ የምወደውና የማከብረው ምሁር የፖለቲካ አልዛይመር የታመመ ይመስላል! ነገሩ እንዲህ ነው! ብርሃኑ ነጋ በጎሳው የእዣ ጉራጌ ቢሆንም ተወልዶ ያደገው ናዝሬት ነው ። የጉራጌ ቋንቋም ባህልም ፣ ዘፈንም ጭፈራም አይችልም ። ግን በአባቱም ባቶ ነጋ ቦንጋ ታታሪነትና በሱም የረጅም ዘመን ፖለቲካ ተጋድሎ ጉራጌዎች ሳይኮሎጂካሊ ሲኮሩበት ነበር።

ያም ስለሆነ የዛሬ 4 አመት እሱና ፓርቲው ወደ ኢትዮጵያ በትልቅ ሆሆታ ሲመልስ የጉራጌ ሕዝብ ጋብዞት ወልቂጤ ሄዶ ነበር። ያን ግዜ ሕዝቡ ለጉራጌ ክልልነት ምን ልታበረክት አስበሃል ብሎ ሲጠይቀው ቀጥተኛና እውነተኛ መልሱ እኔ የዜጋ ፖለቲካ መሪ ስለሆንኩኝ ክልልነት በሚመለከት ከእኔ ምንም አትጠብቁ የሚል መልስ ሰጠ ! በዚህ መልሱ ማንም የተበሳጨም ሆነ የሰደበው የለም ። ስለዚህ ብርሃኑ ነጋ የጉራጌ ክልልነት ተሟጋች ባለመሆኑ አይደለም የጉራጌ ሕዝብ መብት ቀይ መስመር የረገጠው!

አቢይ አህመድ እና የኦሮሙማ ባለግዜዎች ሲስተማቲክ በሆነ ደረጃ ጉራጌ አንገቱን ቀና እንዳያደርግ፣ ሰው እንዳይሆን፣ እንዲበተን ፣ እንደ ሕዝብ፣ እንደ ካልቸር እንዲከስም የሚዳክሩ ጠላቶች እንደ ሆኑ እናውቃለን ! ስለሆነም አቢይ አህመድ የጉራጌ ባለሃብቶችን ሰብስቦ ሲፎግርና ሲሸውድ ቢገኝ ለማንም አያስደንቅም!

አቢይና የዙሪያው ኦሮሞች ጉራጌ ክልልነት አይገባውም ተበትኖ የማንም መረማመጃ መሆን ያለበት አገር አልባ፣ ማንነት አልባ ብትን ዱቄት ነው ብለው የሚያምኑና በፓርቲ ደረጃ ወስነው ጉራጌን የሚያጠፉ ቡድን ናቸው ።

አሁን የብርሃኑ ነጋ ፖኦለቲካ መጃጀት፣ መጃጃል ሳይሆን ትራጀዲ ተመልከቱ ። ብርሃኑ የብልጽ ግና መሪ ሳይሆን የኢዜማ መሪ ነው ። ጉራጌን የሚወክሉት ኢዜማዎች የጉራጌን ክልልነት ከሚመሩት እና ከሚታሰሩት ከሚገደሉት ቀዳሚዎቹ ናቸው። ሃቁና የፖለቲካ አሰላለፉ ይህ ሆኖ ሳለ የብልጽኛው አቢይ የጉራጌን ክልልነት ለማክሸፍ በጠራው ስብሰባ ብርሃኑ ነጋ ምን ያደርጋል? ለምን ተገኘ? ማንን ለመደገፍ ተገኘ? በክክልነት ስብሰባ ብርሃኑ ምን አገባው?

የፖለቲካ አሽከርነት ችግር ይህን ይመስላል!!!!

ለምንና እንዴት ብሎ የኢዜማ መሪ ሆኖ ጉራጌን መብት ለመቃወም የብልጽግ ና መሪ ሆኖ እንደ እርስቱ እርዳው ያሉ የወያኔና ያኦፒዲኦ እስኩቢኒ አሸከሮች ጋር ቆሞ የጉራጌ ሕዝብ ክልል የመሆን መብት አይገባውም ሊል ቻለ?

ያገራችን ሰው ሲያረጅ አያምርም ይላል ! ብርሃኑ ነጋ ቦንጋ ወዴት እየሄደ ነው? ምን እየሆነ ነው? የጉራጌ ሕዝብ ለክልልነት ታገልልን አላለውም ! ግን የህግና ፍትህ ፓርቲ የተባለው ኢዜማ ምን ጅብ በላው! ብርሃኑ ነጋ ከነ እርስቱ፣ ከነሬዳውን፣ ከነመኩሪያ ፣ ካሱ መንደር ወርዶ ያቢይ አሽከር እየሆነ ነው ወይስ በእውን ያይምሮ በሽታ አልዛይመር መሰለል ነገር ያዘው?!

እጅግ እጅግ አፍረናል! አዝነናል ! በዚህም የተነሳ በኢዜማ ውስጥ ሕይወታችሁን ምታባክኑ የጉራጌ ተወላጆች መልቀቂያ ደብዳቤ አዘጋጁ ! ታሪክ ወደፊት እንደ ሚመሰክረው ብልጽግ ና ኢዜማ የተባሉ ፓርቲዎች በጉራጌ ምድር ዘው የማይሉበት ዘመን ይመጣል !

Last edited by Horus on 24 Mar 2023, 02:36, edited 1 time in total.

TGAA
Member+
Posts: 5747
Joined: 07 Apr 2019, 20:34

Re: ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ቦንጋ በጉራጌ ጉዳይ ቀይ መስመር አለፈ! የፖለቲካ መጃጀት ይሏል እንዲህ ነው!

Post by TGAA » 24 Mar 2023, 02:18

ብርሀኑ ወዶ አብይ ማኖፕሌት አድርጎ እንደመሳሪያ የሚጠቀመው መሳሪያ ከሆነ ውሎ አድሯል ፤ የኢትዮጵያዊያኑን ካምፕ ድምጽ ለማቀብ ብርሀኑን ይጠቀምበታል ፤ ይህንን ያህል አንጋፋ ኢዜማን የሚያህል ድርጅት ይዞ ይሄንን ያህል የኢትዮጵያን መሰረት የሚያናጋ ስራዎች ሲሰሩ በወያኔ ግዜ ስቴት ዲፓርመንት እንደሚያደርገው መግለጫ we are concerned የሚል መግለጫ ካወጡ በኋላ ድራሻችው ይጠፋል ፤ ይህንን ደግሞ አብይ በጣም ወዶታል ፤ ኦሮሙማዎች ስራን እንጁ የፖለቲካ መግለጫዎችን የግርግር መሳሪዎች ናቸው ብለው ከወሰኑ ቆይተዋል ፤ እንግዲህ አሁን እላን እንደጠቀስከው የማንንነትን ፖለቲካ ተቃዋሚ ከሆነ ለምንድን ነው እራሱን ለአብይ መጠቀሚያነት የሚያቀርበው በተለይ በአሁኑ አብይ በተጠላበት ሰአት ፤ አብይ ስብሰባው ላይ እንዲሳተፍ ያደረገው የብርሀኑን ጉራጌነት ክሬዴንሻል ለፖለቲካው ለመጠቀም ነው ብርሀኑ ግን የተገኝበት ምክንያት አንተ እንደጠረጠርከው አምኒሺያ ወይም መጃጃት ወይም አብይ ምን ሊያደርግ ሳያውቅ ቀርቶ ሳይሆን ፕሪንሲፕላዊ የወገብ አጥንት ስለሌለው ነው ፤

Horus
Senior Member+
Posts: 42799
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ቦንጋ በጉራጌ ጉዳይ ቀይ መስመር አለፈ! የፖለቲካ መጃጀት ይሏል እንዲህ ነው!

Post by Horus » 24 Mar 2023, 02:27

TGAA wrote:
24 Mar 2023, 02:18
ብርሀኑ ወዶ አብይ ማኖፕሌት አድርጎ እንደመሳሪያ የሚጠቀመው መሳሪያ ከሆነ ውሎ አድሯል ፤ የኢትዮጵያዊያኑን ካምፕ ድምጽ ለማቀብ ብርሀኑን ይጠቀምበታል ፤ ይህንን ያህል አንጋፋ ኢዜማን የሚያህል ድርጅት ይዞ ይሄንን ያህል የኢትዮጵያን መሰረት የሚያናጋ ስራዎች ሲሰሩ በወያኔ ግዜ ስቴት ዲፓርመንት እንደሚያደርገው መግለጫ we are concerned የሚል መግለጫ ካወጡ በኋላ ድራሻችው ይጠፋል ፤ ይህንን ደግሞ አብይ በጣም ወዶታል ፤ ኦሮሙማዎች ስራን እንጁ የፖለቲካ መግለጫዎችን የግርግር መሳሪዎች ናቸው ብለው ከወሰኑ ቆይተዋል ፤ እንግዲህ አሁን እላን እንደጠቀስከው የማንንነትን ፖለቲካ ተቃዋሚ ከሆነ ለምንድን ነው እራሱን ለአብይ መጠቀሚያነት የሚያቀርበው በተለይ በአሁኑ አብይ በተጠላበት ሰአት ፤ አብይ ስብሰባው ላይ እንዲሳተፍ ያደረገው የብርሀኑን ጉራጌነት ክሬዴንሻል ለፖለቲካው ለመጠቀም ነው ብርሀኑ ግን የተገኝበት ምክንያት አንተ እንደጠረጠርከው አምኒሺያ ወይም መጃጃት ወይም አብይ ምን ሊያደርግ ሳያውቅ ቀርቶ ሳይሆን ፕሪንሲፕላዊ የወገብ አጥንት ስለሌለው ነው ፤
TGAA

ሌባ ላመሉ ቅቤ ይልሳል ይባላል ! አቢይ ሆነ ብርሃኑ ይህን ስላሉ ያን ስላሉ የሚፈይዱት ነገር የለም! ሕዝብ ለመኖር ለመከበር ማድረግ ያለበትን ያደርጋል !!! መሪ ከህዝብ ሲገነጠል ክንፍ የሌለው አሞራ ይሆናል ! ጨው ለራሱ ሲል ነው የሚጣፍጠው !!!The people and the people alone are the makers of history!!!

justo
Member
Posts: 3226
Joined: 05 May 2013, 17:54

Re: ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ቦንጋ በጉራጌ ጉዳይ ቀይ መስመር አለፈ! የፖለቲካ መጃጀት ይሏል እንዲህ ነው!

Post by justo » 24 Mar 2023, 03:37

Horus wrote:
24 Mar 2023, 03:19
https://www.youtube.
November ነበር የተከለከልኩኝ ኣለ ደግሞ

Pretoria ሄዶ ነበር መታከም የፈለገው ... እዛ negotiationኑ በተካሄደበት ሆቴል። እዛ ሄጄ መካፈል ኣለብኝ ሲል ኣልነበረም እንዴ ... ኣሁን ደግሞ ታሪኩ ተቀይሮ ለህክምና እዛ ሲብሰባው ኣድራሽ ቀጠሮ ነበርኝ እያለን ነው. There is no end to your ብልጣብልጥነት, it kind of gets tiring.

ethiopianunity
Senior Member
Posts: 10965
Joined: 30 Apr 2007, 17:38

Re: ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ቦንጋ በጉራጌ ጉዳይ ቀይ መስመር አለፈ! የፖለቲካ መጃጀት ይሏል እንዲህ ነው!

Post by ethiopianunity » 24 Mar 2023, 11:50

Look you are acting only because you are from that ethnic:

The current Eprdf#2 is replaced by another minority using Oromo/Olf, another dangerous agenda. What is expected from Eprp as you are part too, another Liberation Front agenda type, so is Berhanu Nega, Andargachew Tsige, etc, the only difference is they put Shabia/Eplf on Ethiopia replacing Tplf

Za-Ilmaknun
Member
Posts: 4487
Joined: 15 Jun 2018, 17:40

Re: ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ቦንጋ በጉራጌ ጉዳይ ቀይ መስመር አለፈ! የፖለቲካ መጃጀት ይሏል እንዲህ ነው!

Post by Za-Ilmaknun » 24 Mar 2023, 12:22

የሃረሪ ህዝብ ፥ አብላጫው ከክልሉ ዉጭ ይኖራል፥ በክልሉም ዉስጥ ማይኖሪቲ ነው፥ ነገር ግን ክልል ነው። ጉሙዝ ብትሄድ አብላጫው ሌላ ነው ነገር ግን ክልል ነው።

ፕሪፌሰሩ፥ የዜግነት ፖለቲካ አራምዳለው ይሉና፥ ታከለ ኡማ እና አብይ ያሻግሩናል ሲሉን ሲያደነዝዙን አምነን ተኛን። ልክ ነው ከዘመነ ትግሬ ወደ ለየለት ዘመነ ኦሮሞ ፋሽዝም አሻገሩን። አማራው እንደ አማራ ልደራጅ ሲል አይናቸው ደም ይለብሳል፥ መናገር እስኪሳናቸው አንደበታቸው በንዴት ይንተባተባል። ህገመንግስቱን አፀናለው ለሚለው አለቃቸው ደሞ ታማኝ አገልጋይ ሆነው ፥ ጠቅላዪ ለማስመሰል የሚናገራትን ኢትዮጵያ እሳቸው ከምር ተቀበሉ ይሉናል።

አሁን ደግሞ የጉራጌ ህዝብ ኦሮሞማ ሳይሸራረፍ እተገብረዋለው በሚለው ህገ-አራዊት መሰረት የራሴን በራሴ በማልት፥ በጎ የሆነ የክልላዊ መደራጀትን ቢጠይቅ፥ የተረፈው በጥይት መቆላትና በቆመጥ መደብደብ ሆነ።

ምናልባት የጉራጌ ክልል ቢመሰረት ኢትዮጵያን ለማፅናት ከሚሰሩት ጋር ይሰራል የሚለው የጠቅላዩ ስጋት ቢገባንም፥ ህጋዊ መብቱን ለመንፈግ በሚደረገው ሩጫ ግን ፕሮፈሰሩን የመሰሉ ጉምቱ ፖለቲከኞች ፥ አሉታዊ አብርክቶት ትልቅ ስህተት ነው። የጎሳ አደረጃጀት ህግ በሆነበት፥ ህግ አታክብሩ ማለት ፖለቲከኛ አያሰኝም። የተያዘችው ስልጣንም ከሰውየው ተክለ ፖለቲካዊ ቁመና አንፃር እዚህ ግባ የምትባል አይደለችም። ለሆዳቸው እንዳይባል፥ ከራሳቸው በላይ ለሃገር የሚተርፉ ናቸው፥፥ ታዲያ ምን ነካቸው?

ካረጁ አይበጁ ወይስ ሲያልቅ አያምር ምናምን ብለን እንዳናልፈው፥ አሁንም ከፍተኛ ተፅኖ የመፍጠር አቅማቸውን ለ ብሄረተኛው የኦሮሞ ልሂቅ መጠቀሚያነት ሲያውሉት ስናይ ፥ በሃገራችን ተስፋ እንድንቆርጥ ያደርጉናል።

ዛሬ ደሞ ኢዜማና አብን ይሚባል ሽርጉድ እይሰማን ነው። ሁለቱም ግን ህዝብ በፈለጋቸው ሰዐት በትግሉ ሜዳ አልተገኙም። ቁማር ከተበላ በሁዋላ አለሁ ማለት የምን ይሆን?

Abere
Senior Member
Posts: 15438
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ቦንጋ በጉራጌ ጉዳይ ቀይ መስመር አለፈ! የፖለቲካ መጃጀት ይሏል እንዲህ ነው!

Post by Abere » 24 Mar 2023, 12:38

አንድ ነጋ አድራስ የሚጭናቸው አጋሥሶች ስንት ዳውላ ተሸክመው አቀበት ቁልቁለት ወርደው እንደሚሄዱ ካወቀ በኋላ ከአቅማቸው በላይ አጋሥሶቹን አይጭንም። ከጫናቸው መሃል አገር ከእነጭነታቸው ወደቀው እራስህ ተሸከም ይሉታል። አሁን ኢዜማ እና አብን ኢትዮጵያዊነትን ተሸክመው መሄድ የሚችሉ አይደሉም( እንደ ፓርቲ) አቅማቸ ይህን ያህል ነው። ወደፊት ያለው የሃላፊነት ሸክም እና ትግል እጅግ ከባድ ነው። የወደቀ አንስቶ እንደገና ከትግል ሜዳው ከድል ምዕራፍ አድርሰኝ ማለት ድጋሜ ሞኝነት ነው። ኦሮሙማ ኦነግ በቀላሉ ሥስ ጎናቸውን እና የስብዕና አንጻራቸውን ስላወቀው (they are hacked) እንደ ፓርቲ አያስፈልጉም - ኦሮሙማ አክስሟቸዋል። እነርሱ ፋይዳ ለማገኘት ሊምሉ ሊገዘቱ ይችላሉ - ግን ከንቱ ነው።

Za-Ilmaknun wrote:
24 Mar 2023, 12:22
የሃረሪ ህዝብ ፥ አብላጫው ከክልሉ ዉጭ ይኖራል፥ በክልሉም ዉስጥ ማይኖሪቲ ነው፥ ነገር ግን ክልል ነው። ጉሙዝ ብትሄድ አብላጫው ሌላ ነው ነገር ግን ክልል ነው።

ፕሪፌሰሩ፥ የዜግነት ፖለቲካ አራምዳለው ይሉና፥ ታከለ ኡማ እና አብይ ያሻግሩናል ሲሉን ሲያደነዝዙን አምነን ተኛን። ልክ ነው ከዘመነ ትግሬ ወደ ለየለት ዘመነ ኦሮሞ ፋሽዝም አሻገሩን። አማራው እንደ አማራ ልደራጅ ሲል አይናቸው ደም ይለብሳል፥ መናገር እስኪሳናቸው አንደበታቸው በንዴት ይንተባተባል። ህገመንግስቱን አፀናለው ለሚለው አለቃቸው ደሞ ታማኝ አገልጋይ ሆነው ፥ ጠቅላዪ ለማስመሰል የሚናገራትን ኢትዮጵያ እሳቸው ከምር ተቀበሉ ይሉናል።

አሁን ደግሞ የጉራጌ ህዝብ ኦሮሞማ ሳይሸራረፍ እተገብረዋለው በሚለው ህገ-አራዊት መሰረት የራሴን በራሴ በማልት፥ በጎ የሆነ የክልላዊ መደራጀትን ቢጠይቅ፥ የተረፈው በጥይት መቆላትና በቆመጥ መደብደብ ሆነ።

ምናልባት የጉራጌ ክልል ቢመሰረት ኢትዮጵያን ለማፅናት ከሚሰሩት ጋር ይሰራል የሚለው የጠቅላዩ ስጋት ቢገባንም፥ ህጋዊ መብቱን ለመንፈግ በሚደረገው ሩጫ ግን ፕሮፈሰሩን የመሰሉ ጉምቱ ፖለቲከኞች ፥ አሉታዊ አብርክቶት ትልቅ ስህተት ነው። የጎሳ አደረጃጀት ህግ በሆነበት፥ ህግ አታክብሩ ማለት ፖለቲከኛ አያሰኝም። የተያዘችው ስልጣንም ከሰውየው ተክለ ፖለቲካዊ ቁመና አንፃር እዚህ ግባ የምትባል አይደለችም። ለሆዳቸው እንዳይባል፥ ከራሳቸው በላይ ለሃገር የሚተርፉ ናቸው፥፥ ታዲያ ምን ነካቸው?

ካረጁ አይበጁ ወይስ ሲያልቅ አያምር ምናምን ብለን እንዳናልፈው፥ አሁንም ከፍተኛ ተፅኖ የመፍጠር አቅማቸውን ለ ብሄረተኛው የኦሮሞ ልሂቅ መጠቀሚያነት ሲያውሉት ስናይ ፥ በሃገራችን ተስፋ እንድንቆርጥ ያደርጉናል።

ዛሬ ደሞ ኢዜማና አብን ይሚባል ሽርጉድ እይሰማን ነው። ሁለቱም ግን ህዝብ በፈለጋቸው ሰዐት በትግሉ ሜዳ አልተገኙም። ቁማር ከተበላ በሁዋላ አለሁ ማለት የምን ይሆን?

Horus
Senior Member+
Posts: 42799
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ቦንጋ በጉራጌ ጉዳይ ቀይ መስመር አለፈ! የፖለቲካ መጃጀት ይሏል እንዲህ ነው!

Post by Horus » 24 Mar 2023, 13:06

Za-Ilmaknun wrote:
24 Mar 2023, 12:22

ካረጁ አይበጁ ወይስ ሲያልቅ አያምር ምናምን ብለን እንዳናልፈው፥ አሁንም ከፍተኛ ተፅኖ የመፍጠር አቅማቸውን ለ ብሄረተኛው የኦሮሞ ልሂቅ መጠቀሚያነት ሲያውሉት ስናይ ፥ በሃገራችን ተስፋ እንድንቆርጥ ያደርጉናል።
እኔ ሲያረጅ አያምር ያልኩት በብርሃኑ ነጋ ላይ ለመለሳለስ አይደለም ። የጎሳ መደራጀት አያስፈልግም እያለና ያን የሚል ፓርቲ እየመራ ጉራጌን በጎሳ ክለስተር መጨፍለቁን ደግፎ ጉራጌ እራሱን የማስተዳደር መብቱን አለማክበሩ ነው ሲጃጁ አይበጁ ያልኩት ። በአንድ ቃል ብርሃኑ የብልጽግና አባል ሳልልሆነ ወይም የፌዴራል ቢሮክራት ስላልሆነ በፍጹም መገኘት አልነበረበትም ። ከተገኘ ደሞ ማንም ሕዝብ እራሱ የማስተዳደር መብቱን ከራሱ ፓርቲ አቋም ተነስቶ መደገፍ ነበረበት !

ስለ ተጽኖ ያለከው ትክክል አይደለም ። ዛሬ እያንዳንዱ ሕዝብ ጥቅሙ ምን እንደ ሆነ ያውቃል ። አንድን መሪ የሚከተለውና የሚያክብረው ፍላጎቱን ለሚያደራጅለት መሪ ነው ። አቢይ አህመድን ተመልከተው ። ምን ያልክ እንደ ዘፈንለት!? ዛሬ የሚሰሙትና የሚከተሉ በስንት እንደ ቀነሱ ትመለከታለህ ።

በጉራጌ ጥያቄ ላይ እኔ ከላይ ግልጽ አድርጌያለሁ። በኢዜማ ውስጥ ያሉ የጉራጌ ተወላጆች አባልነታቸውን መሰረዝ ነው ያለባቸው ። ሕዝባቸውን ቤተሰባቸው፣ መብታቸውን የማያስከብርላቸው፣ ድምጽ የማይሆናቸው ፓርቲ ውስጥ የወር ክፍያ እየገፈገፉ ለማንም የስልጣን መወጣጫ መሆን የለባቸውም ።

ጉራጌ አሁን የራሱ የፖለቲካ ፓርቲ አለው ፤ ጎጎት ይብላል ። ስለዚህ የዚያ ፓርቲ አባል ሆነን የህዝባችንን ጥያቄ ከሚደግፉ ጋር ትብብር በመፍጠር ለመብታችን መታገል እንቀጥላለን !

ከህዝብ የተገነጠለ መሪ ተጽኖ መፍጠር አይችልም ! ለዚህ ነው ጉልበት የሚጠቀመው !

Za-Ilmaknun
Member
Posts: 4487
Joined: 15 Jun 2018, 17:40

Re: ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ቦንጋ በጉራጌ ጉዳይ ቀይ መስመር አለፈ! የፖለቲካ መጃጀት ይሏል እንዲህ ነው!

Post by Za-Ilmaknun » 24 Mar 2023, 16:07

ፕሮፌሰሩን መታዘብ የጀመርነው ከ ቡራዩው ፍጅት ጀምሮ በነበራቸው በዝምታ የታጅበ መንግስታዊ ድጋፍ ቢሆንም፥ ምናልባት በሚል ከፍረጃ ተቆጥበን ቆይተን፥ ታከለና አብይ ያሻግሩናል እስኬው እብድ ነው ብለው ሲወጡ፥ ሁሉም ግልፅ ሆነልን። ለሰውየው ከነበረን ግምት አንፃር የራሳችንን መሣት ውጠን፥ ስለሳቸው መልካም ድጋፍ ያላቸውን በሩቅ እያየን፥ በጊዜ ይገለጥላቸዋል ብለን አይናችንን የወደፊቱ ላይ ብቻ አድርገን ዘለቅን።

ወዳጄ፥ ተሳፋሪው የሚንጠባጠበው በሂደት እንጂ አንተ ከድጋፍ ባቡሩ በወረድክበት ቅፅበት አይደለም። ፕሮፌሰሩ ዛሬ ከጉራጌ ፍላጎት መሳ ስለቆሙ ሲዳማው ወይም ወላይታው ወይም እንጦኔው አይደግፍም ለማለት ያው የቀድሞው አይነት እውቀት ይጠይቃል። የዜግነት ፖለቲካ የሙጥኝ ብሎ መዳረሻውን እንጂ መንገዱን ሳይጠርግ የሚርመጠመጠው ዜጋ አንድ መዐት ነው። ያ መአት ደሞ ከነ አሻግሬ ጋር ቆሞ ዛሬም ሲሞግተን ቢውልም፥ ከዛም ባላነስ የብርሌው ከነቃ ወንድምም ፥ ቅፅበታዊ ብያኔ፥ ከመታበይ ያለፈ ነው ብለን ቁብ አንለውም። ሰውየው ከጠቅላዩ ፍቺ በግልፅ ቢፈፅሙ፥ አንደምታው ከበድ ያለ ይሆን ነበር። ከህዝብ ድጋፍ ባሻገር ለ ዲፕሎማቲክ ማህበረሰቡ ብዙ ቅርበት ስላላቸው ፥ ትፅኖውን ማሳነስ አይገባም።

ለመሆኑ የዐማራው ጥያቄ ምንድነው ብለው የአማራውን መጨፍጨፍ ቢያጣጥሉት ስናይ ፖለቲካና ወገንተኝነት፥ ሲደባለቁ ለፍርደገምድልነት መልካም አጋጣሚ መፈጠሩን እንረዳለን።

አሁንም እንላለን ጉራጌ ክልል ነው!! :mrgreen:

Post Reply