ምን ተብሎ እስኪነገራቸው ድረስ እንደሚጠብቁ አይገባኝም። ባህላዊ ጨዋታ ያሉት ጦርነት ከእንግዲህ አብቅቷል። በኢትዮጵያና በኤርትራ ሰራዊት ተሸንፈናል፥ ትጥቃችንን አስፈቱን።
ለነገሩ በጥቅምና በከንቱ ውዳሴ ከአሸባሪ ጁንታው ጋር የተሳሰሩ ስለሆኑ እውነቱን መቀበል ያስቸግራቸዋል። እንደዚህ የሚያሳዝን ድፍረት በትግራይ ታሪክ ታይቶ አያውቅም። ፈጣሪ ምህረት ካላደረገልን የትግራይን አቅጣጫ እየከፋ መሄዱ አይቀርም። በወገኖቻችን ደም የተጨማለቃችሁ ሁላ ምን ይሆን ትርፋችሁ? ጥርስክ ካልሆነ አሸዋ አኝክበት! ደይስንኻ ሑፃ ቖርጥመሉ!