Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Thomas H
Senior Member
Posts: 13068
Joined: 27 Jan 2007, 16:30
Location: Kaliti
Contact:

Must Read Eyewitness report : ከንቲባ አበደች ደደቤ በ19 ሚሊዮን ብር ስለገዛችው አዲሱ ባስ የኢትዮጵያ ሕዝብ ምን አለ ?

Post by Thomas H » 22 Feb 2023, 09:50

Perfect Media
49m ·
በአዲሱ ባስ የተሳፈረ ሰዉ ምስክርነት !
****************. 🙈 😄
ሰሞኑን ሰው ሁሉ በ19 ሚሊዮን ብር ስለተገዛው አዲሱ ባስ ሲያወራ ለምን ሄጄበት አልሞክረውም ብዬ ዛሬ ከጀሞ 1 ወደ ሜክሲኮ ሄጄ ነበር።
...
ባስ ስቴሽኑ ጋ የደረስኩት ከጠዋቱ 12 ሰአት ሲሆን ከተደረደሩት አዲስ ባሶች ውስጥ አንዱን መርጩ ገባሁ። በር ላይ ሚኒ ስከርት የለበሰች አስተናጋጅ በፈገግታ ተቀብላኝ ጉንጬን ከሳመችኝ በኋላ ስልኳን ሰጥታኝ ወደ ውስጥ አስገብታ ወንበር አስያዘችኝ።
...
በጣም ብርድ ስለነበር ከወንበሬ አጠገብ የነበረውን Heat የሚለውን በተን ክሊክ ሳደርገው ወዲያውኑ ከወንበሬ ዙሪያ ጠርዝ ላይ ነጭ ጋቢ ወጥቶ ሙሉ ሰውነቴን አለበሰው። በዚህ ተገርሜ እንደምንም ከጋቢ ውስጥ እጄን አውጥቼ ፊት ለፊቴ ያለውን ስክሪን ሳበራው መኪናው ላይ ስለተገጠሙት ቴክኖሎጂዎች የሚገልፅ ፅሁፍ መጣልኝ።
...
ፅሁፍ ላይ እንዳነበብኩት ከሆነ ክረምት ክረምት መንገዶች በጎርፍ ሲሞሉ ይሄ ባስ ወዲያውን ቅርፁን ወደ ዝርግነት በመቀየር ወደ መርከብነት የሚለወጥ ሲሆን በውስጡም መለስተኛ ኳስ ሜዳ እና የባስኬት ቦል ኮርቶች እንዲሁም ለፈረስ ግልቢያ የሚሆን ሰፊ ሜዳ ይዟል።
...
ምናልባት ከቤቱ ተቻኮሎ ፊቱን ሳይታጠብ የመጣ ተሳፋሪ ካለ ባሱ የራሱን የፊት ሳሙና እና የጥርስ ብሩሽ ከኮልጌት ጋር እንዲሁም ከማይመለስ አንድ ፎጣ ጋር የሚያቀርብ ሲሆን ስቲም እና ሳውናም ከሾፌሩ ጀርባ ባለው ክፍል ውስጥ ዝግጁ ሆኖ ተሳፋሪዎቹን ይጠብቃል።
...
በተጨማሪም መንገድ በሚዘጋበት ጊዜ ከጎን እና ከጎን ክንፎቹን በመዘርጋት ልክ እንደ ዴር 33 ከራዳር እይታ ውጪ መብረር የሚችል ሲሆን ምናልባት በሰማይ ላይ እያለ የሰማይ ትራፊክ መጨናነቅ ቢያጋጥመው እንኳን ከስሩ እሳት በመፍጠር ራሱን ወደ መንኮራኩነት በመቀየር ወደ ጨረቃ የሚያምዘገዝግ የሮኬት ቴክኖሎጂ ተገጥሞለታል።
...
ለባለስልጣኖች ራሱን የቻለ መኝታ ቤት ያለው ሲሆን ለሰፊው ህዝብ ደግሞ ትኬት ሳይቆርጥ የገባን ቆርጦ ከገባው የሚለይ ሴንሰር ተገጥሞለታል። የሚገርመው ትኬት ያልቆረጡትን ሰዎች በስም መለየት የሚችል ሲሆን አንዱ ተሳፋሪ ሳይቆርጥ ገብቶ ወዲያኑ "ደጀኔ እባክህ ወይ ቁረጥ ወይ ውረድ አትሞላፈጥ" በሚል ድምፅ ተሳፋሪውን ሲያስጠነቅቅ በጆሮዬ ሰምቻለሁ።
...
በመጨረሻም ሜክሲኮ ባስ ስቴሽን ደርሰን ስንወርድ ለሁላችንም የጫማ ማስጠረጊያ እና ለቀጣይ ታክሲ መሄጃ 60 60 ብር የተሰጠን ሲሆን ሾፌሩን ጨምሮ ሁሉም የባሱ ሰራተኞች በእግራቸው የተወሰነ መኔገድ ሸኝተውናል። በእኔ እይታ ይሄ ባስ 19 ሚሊየን ሲያንስበት እንጂ ከዚህም በላይ ይገባዋል። Thank you አዴክስ ጭሷ!

...


Assegid S.
Member
Posts: 950
Joined: 11 Aug 2013, 07:11
Contact:

Re: Must Read Eyewitness report : ከንቲባ አበደች ደደቤ በ19 ሚሊዮን ብር ስለገዛችው አዲሱ ባስ የኢትዮጵያ ሕዝብ ምን አለ ?

Post by Assegid S. » 22 Feb 2023, 13:29

ሰዉ ገንዘቡ የትና ምን ላይ እንደዋለ ለማወቅ ለምን እንዲህ ትዕግስት እንዳጣ አልገባኝም። ትንሽ ቆይተው ልማደኛዋ ከንቲባ እራሳቸው ... "ከየት እንደተላከ የማላውቀው 2 ቢልዮን ብር ባንክ አካውንቴ ውስጥ ተገኘ" ብለው እንቆቅልሹን ይፈቱልን የለ?

Thomas H
Senior Member
Posts: 13068
Joined: 27 Jan 2007, 16:30
Location: Kaliti
Contact:

Re: Must Read Eyewitness report : ከንቲባ አበደች ደደቤ በ19 ሚሊዮን ብር ስለገዛችው አዲሱ ባስ የኢትዮጵያ ሕዝብ ምን አለ ?

Post by Thomas H » 23 Feb 2023, 09:48

ለባሕላዊው አምባሳደር ሱለይማን ደደፎ ጥሪ ተደረገ

Dereje Habtewold
5h
·
ክቡር አምባሳደር ሱለይማን ደደፎ፣
ጀግንነት ተላብሰው እንደ ባልቻ ሳፎ፣
ከለውጡ ፊት ሆነው ግብዓት ያቀበሉን፣
ስለ ሜቴክ መርከብ -ዝርፊያ ጉድ ያስባሉን....
ዛሬም ሲጠበቁ - እንዲመሰክሩ፣
የአውቶቡሱ ጊዜ ወዴት ተሰወሩ?


Post Reply