Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 42805
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

የሰሞኑ ሜታፎር ፣ በግ !

Post by Horus » 17 Feb 2023, 16:22

የጠፋ፣ የተግኘ ፣ ደግሞ የጠፋ :lol: :lol:

justo
Member
Posts: 3226
Joined: 05 May 2013, 17:54

Re: የሰሞኑ ሜታፎር ፣ በግ !

Post by justo » 17 Feb 2023, 18:08

Horus wrote:
17 Feb 2023, 16:22
የጠፋ፣ የተግኘ ፣ ደግሞ የጠፋ :lol: :lol:
ኣንተ ሞኝ ሰዉየ ምነው ኣርፈህ ብትቀመጥ። ድልድይ ኣፍራሽ መሆን ቢቀርብህስ። ኣሁን እንደገና born again ሬቮ ልትሆን ነዉ እንደ ጥላሁን እንደ ቸ ጎቬራ

Abere
Senior Member
Posts: 15441
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: የሰሞኑ ሜታፎር ፣ በግ !

Post by Abere » 17 Feb 2023, 18:21

የቤተመንግስቱ ተኩላ እና የመስዋዕቱ በግ ቅዱስ ሲኖዶሱ። ተኩላው ያታልላል፤በጎቹም ገና ወጥመድ አልገቡለትም።


Assegid S.
Member
Posts: 950
Joined: 11 Aug 2013, 07:11
Contact:

Re: የሰሞኑ ሜታፎር ፣ በግ !

Post by Assegid S. » 17 Feb 2023, 19:33

ሰላም ወንድም Horus;

በዚህ ፎረም ላይ ያለህን መልካም ተሳትፎ በእርግጥ አደንቃለሁ። ወደ ቀልድ መሰል ቁምነገሩ ስመለስ ግን ... ጠቅላዩ ነገር ላሳምር ብለው እንጂ እንደ እውነቱ ከሆነ የተሸጠ (የተገዛ) እንጂ የጠፋ በግ የለም። በተረትና ምሳሌ ግን የኦርቶዶክስን ጥርስ ጠቅላዩ አዋዝተው አነቃንቀውታል፡፡ ከዚህ ቦኃላ ቤተክርስቲያኗ አትነክስበት፣ አታኝክበት ... ቀኑ ደርሶ እስኪወልቅ ጌጥ ሆኗት ይቀመጣል።

በነገራችን ላይ ጠቅላይ ሚንስትሩ በየመድረኩ በእምነት ተቋማት ላይ እንደሚዘምቱ ሲፎክሩ የነበረው ከመንፈቅ በፊት ነበር። ዛሬ ላይ የሰሜኑን ጉዳይ "ዳር ያደረሱ" መስሎ ሲሰማቸው ወደ መሐሉ መጡ። አሁንም በየክልሉና በኣዲስ አበባ እየተካሄደ ያለው "ሰልፍ አስተባባሪና ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ናቸው" ተብሎ የታመነባቸውን ግለሰቦች እየለቀሙ የማሰር ምስጢር ... ነገ የተገዛው በግ "ዋናው ሲኖዶስ ነኝ" ብሎ ሲመጣ የሚፈጠረውን ረብሻ ለማስቀረት ... መንግስት ለህገወጡ ኣካል የሆሳዕና ጉዞ አስቀድሞ እያነጠፈ ያለው ዘንባባ ነውይበልሽ! ይሁዳን ያመንሽ!

መልካም ሰንበት; ወንድም Horus

Horus
Senior Member+
Posts: 42805
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የሰሞኑ ሜታፎር ፣ በግ !

Post by Horus » 17 Feb 2023, 21:40

justo wrote:
17 Feb 2023, 18:08
Horus wrote:
17 Feb 2023, 16:22
የጠፋ፣ የተግኘ ፣ ደግሞ የጠፋ :lol: :lol:
ኣንተ ሞኝ ሰዉየ ምነው ኣርፈህ ብትቀመጥ። ድልድይ ኣፍራሽ መሆን ቢቀርብህስ። ኣሁን እንደገና born again ሬቮ ልትሆን ነዉ እንደ ጥላሁን እንደ ቸ ጎቬራ
ጁስቶ የምትባል ሹክሻክ ለምን ትሽን አታስብም ። ይህ አባ ሳዊሮስ የተባለ የስልጣን ጥመኛክ እድሜውን ሙሉ ቤተ ክህነት የፈጃ ጳጳስ ነው፣ ለምን ፓትሪያርክ አልሆንም የሚለው ሰው ነው ። ትላንት በአለም ፊት የሰጠውን ቃል፣ የተስማማውን ዛሬ ያጥፋል ። እናስ ከዚህ በኋላ አንድ አማኝ እንዴት ከዚህ ሰው መስቀል ይሳለማል ። እንደዚህ ያለን ከሃዲ ክቶስ እንዴት የእግዚብሄር መልክተኛ ተብሎ ይታመናል ። አሳፋሪ የስልጣን እና የገንዘብ ነጋዴዎች !!!

Misraq
Senior Member
Posts: 17845
Joined: 27 Sep 2009, 19:43
Location: Zemunda

Re: የሰሞኑ ሜታፎር ፣ በግ !

Post by Misraq » 18 Feb 2023, 01:37

ጠፍቶ የነበረው የዓብይ ኦሮሙማ በግ (አቶ አካለወልድ)


Horus
Senior Member+
Posts: 42805
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የሰሞኑ ሜታፎር ፣ በግ !

Post by Horus » 18 Feb 2023, 02:51

አሰግድ፣
ፈረንጅ ሲተርት ጦጣ ሰማይን ለመጨበጥ ለሊቱን ሁሉ እንጣጥ ስትል ታድራለች ይላል፤ ማለትም ለሊት ላይ እነዚይ እጹብ ድንቅ ከዋክብት ማየት ብቻ ሳይሆን ለትነካቸው ስለምትመኝ !! ያ ማለት አቢይ አህመድ ነው። ይህ ጉዳይኮ ተደጋግሞ ተነገረ ። የኦሮሞ ህዝብ ቁጥር ስንት እንደ ሆኑ ባላውቅም ኦርቶዶክስ ኦሮሞች 10 ሚሊዮን አይሆኑም ማለትም 50 ሚሊዮን ኦርቶዶክሶች ኦሮሞች አይደሉም። ተው ኦሮሞ ትግሬ ነገ ተገንጥሎ ጴንቴ ቢሆን 45 ሚሊዮን ኦርቶዶክስ አለ ።

ስለሆነም ፕሮፓጋንዳ ሳይሆን ኦሮሞ ለራሱ ሲል ኦርቶዶክስ ይሆናል እንጂ በቀረነው ኦርቶዶክስ ኢትዮጵያዊያን ላይ አንዳች ፋይዳ አያመጣም! ሃቁ ይህ ነው ! እነ ስብሃት ነጋ ኦርቶዶክስን አከርካዊውን ሰብረነዋል ብለውን ነበርኮ!!! አከርካሪዋ የተጎማመደ እራሷ ወያኔ ነው ። መሬት ያለው ሃቅ ይመስክር ።

አቢኢ አህመድ የሚባል ወጠጤ ድፍን አራት አመት ኢትዮጵያን መምራት አይደለም ማራጋጋት ያልቻለ አላዋቂ ሳሚ ንፍጥ ለቅላቂ ነው ። ግብዝ አለሁ አለሁ ባይ ነው! እሱ ከዚህ በኋላ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ የነቃ ብርሌ ነው ። ይህ ሁሉ ድራማ መልከ ጥፉን በስም ይደግፉ ስብከት ነው ። ሰው አቢይን ማመን ካቆመ ሰንብቷል ። አሁን የሚቀጥሉት ትር ኢቶች በዲክታተሩ መጻፍ ተዘረዝረዋል ... ስብከት ማስፈራራት፣ ማሰር ፣ ቶርቸር ማድረግ፣ መግደል፣ እንደ ገና ማሳፈራራት !!!! የኔ ወንድም ያ ሁሉ መንግስቱ ሃይለ ማሪያም ፣ መለሰ ዜናዌ ሞክረውታል ። ከታሪክ የማይማር ግብዝ ብቻ ነው ያን መንገድ የሚጓዝ!!

አሁን ቀውስና የርስበርስ ጦርነቱ ከትግሬ ወደ ኦሮሚያ እየመጣ ነው ። ለዚህ ግዙፍ ድራማ ሁላችንም እየተዘጋጀን ነው ። ጉራጌ ሲተርት ነገር የባለቤቱ ነው ይላል ። ስለሆነም አቢይ ያመጣው ነገር እራሱን ነው ከዙፋኑ የሚያወርደው! እንከታተል!!!

Post Reply