ምሰሶ 1፣
እነዚህ ቁልፍ (ዋና) ደጋፊ ይባላሉ ። እነሱም ሚኒስሮች፣ ከንቲባዎች፣ የክልል ፕሬዚዳንቶች፣ የፓርቲ ሴንትራል ኮሚቴ፣ የሴኩሪቲ፣ የፖሊስ፣ የስለላ፣ የጦር ጄኔራሎች፣ ትላልቅ ባለሃብቶና ኦሊጋኮች ናቸው ። አንድ ዲክታተር ከነዚህ ቁልፍ ደጋፊዎች በብዛት ከከዱት ይወድቃል ። ዛሬ ላይ በዚህ ቁልፍ መደብ ውስጥ ብዙ መክዳት አይታይም ።
ምሰሶ 2፣
እነዚህ ተጽኖ ፈጣሪዎች (ኢንፍሉወንሰር) ይባላሉ ። የነሱ ስራ ዲክታተሩ በሕዝብ እንዲደገፍ፣ እንዲወደድ፣ እንዲከበር፣ እንዲታወቅ፣ እንዲጀግን የሚሰብኩ፣ የሚታስተምሩ፣ የሚያስረዱ፣ የሚቀሰቅሱ፣ የሚያነቁ መደብ ናቸው ። ለምሳሌ የሚዲያ፣ የአርት፣ የእስፖርት፣ የስነጽሁፍ፣ የሃይማኖት፣ የማስታወቂያ፣ የባህል
ሙያተኞች ናቸው ።
ይህ የዲክታተሩ ተጽኖ ፈጣሪ መደብ አሁን ላይ ፍርስርሱ እየወጣ ነው ። እራሱ ዲክታተሩ ከሚያዛቻው የመንግስት ተቀጣሪዎች ውጭ ያሉት እጅግ በብዛት ዲክታተሩን እየከዱት ይገኛሉ ። ኦርቶዶክስ አማኞች፣ ወንጌላዊ አማኞች፣ የግል ሚዲያዎች፣ የፊልምና ድራማ ኢንዱስትሪ ፣ ተዋኛን እያለ ዝርዝሩ ይወርዳል ። እነዚህ ናቸው የሚቀጥለው ምሰሶ 3ን ኢንፍሉወንስ የሚያደርጉ። ይህ አንዱ ትልቁ የዲክታተሩ ውድቀት ምልክትና ምክንያት ነው ።
ምሰሶ 3፣
እነዚህ ድምጽ ሰጭዎች ይባላሉ ። ዲክታተሩ ስልጣን ላይ እንዲወጣ ድምጽ የሚሰጡና ሕጋዊ ሽፋን የሚሰጡት መደብ ነው ። ይህ መደብ በመሰረቱ እንደ ወረደ ኃይል የለውም ። ይህ መደብ ኃያል የሚሆነው በእምቢተኘትና አመጽ ሲነሳ ብቻ ነው ። የምሰሶ 2 ስራ ይህ 3ኛ መደብ ዲክታተሩን ደግፎ እንዲቆም ድምጽ እንዲሰጥ ማንቃት ነው ። ነገር ግን ምሰሶ 2 ዲክታተሩን ከድቶ መደብ 3 እምቢ እንዲል ማስተማርና ማንቃት ከጀመረ የዲክታተሩ ውድቀት በተግባር ይጀምራል ።
ከዚያ የሚቀረው የምሰሶ 1 እርስ በርሱ መከፋፈልና የዲክታተሩ መነሳት ነው ።

