Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum

Meleket
Member+
Posts: 5070
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: ሀጠው፥ቀጠው፥ ከምኢሱ፤

Post by Meleket » 09 Feb 2023, 10:51

እኛ ኤርትራዉያን የመሃልና የመስመር ዳኞች፡ ለጀግናው የዩክሬን ህዝብ ከነጀግናው መሪያቸዉ ትልቅ ክብር እንሰጣቸዋለን! :mrgreen:

ጀግናው ዘለንስኪ ባያነሳ ጋሻ፡
በቦረቀ ነበረ አውሮፓ ላይ ራሻ። :mrgreen:

ወራሪ ከሰሜን ይምጣ ከደቡብ ከምስራቅ ይምጣ ከምዕራብ ወራሪ ነው፡ በህዝብ ትግልም ይሸነፋል![ አራት ሚሊየን ነጥቦች]

ክሬሚያ ሆይ ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ!” ቀኜ ትርሳኝ” እያለ ነው የኣውሮፓው ሻዕብያ፡ ዘለንስኪ ጀግናው!


ሲጠቃለል
መለስ = ፑቲን = የማሌ (የማርክስና የሌኒን ግርፍ) ልዑላዊ ሃገሮችን የወረሩ ወፈፌ መሪዎች

የታላቋ ትግራይ ህልም = የታላቋ ሩስያ ህልም = የታላቋ ጦቢያ ህልም

ደደቢት ብቻ ኣይደለም ደደብ፤ ሩስያም (ክሬምሊንም) ጭምር ደደብ ነው!

ዘለንስኪ ጀግና ነው!

ድል ለሰፊው የዩክሬን ህዝብ!
:mrgreen:

Axumezana
Senior Member
Posts: 19179
Joined: 27 Jan 2020, 23:15

Re: ሀጠው፥ቀጠው፥ ከምኢሱ፤

Post by Axumezana » 09 Feb 2023, 13:58

የፑቲን፥ ወዳጅ፥ከሆነው፥ ከጌታህ፥ ኢሳያስ፥ ጋር፥ መጣላት፥ ፈልገሃል፥ ማለት፥ ነው። ነፃ፥ አገር፥ የሰጠህን፥ መለስ፥ ከፑቲን፥ ጋር፥ ማወዳደርስ፥ ደደብነትና፥ ከሃዲነት፥ እይደለም?

Meleket
Member+
Posts: 5070
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: ሀጠው፥ቀጠው፥ ከምኢሱ፤

Post by Meleket » 10 Feb 2023, 05:57

ወዳጃችን Axumezana ምነው ከፋህ? እኛ ኤርትራውያን የመሃልና የመስመር ዳኞች ጌታችን ሰማያዊው ንጉስ ብቻ ነው። ምድራዊው ታጋይ ኢሳይያስ የታሪክ ኣጋጣሚ ሆኖ ኤርትራን በመምራት የሚገኝ ዜጋችን ነው። ከወራሪውና ዕብሪተኛው ልዑላዊት ሃገር ሃገረ ዩክሬንን በኃይል ለመደፍጠጥ ከተነሳው ከፑቲን ጋር ለመወዳጀት መሞከሩን እኛ ኤርትራውያን የመሃልና የመስመር ዳኞች “በብሪንስብል ደረጃ” ኣልወደድንለትም። :lol: ምክንያቱም እላይ እንዳስቀመጥነው ወራሪ ከሰሜን ይምጣ ከደቡብ ከምስራቅ ይምጣ ከምዕራብ፡ መወገዝ እንጂ መደገፍና መወደስ ኣይገባውምና ነው። ኤርትራውያን ጋዜጠኞችንና ነባር ታጋዮችን የያዘበትን ሁኔታ ኣልወደድንለትም። ህዝባችን ከዓመታት በፊት መክሮና ዘክሮ ያዘጋጀውን ሕገ መንግስታችንን ሙሉ በሙሉ ኣለመተግበሩን ኣልወደድንለትም። ከዚህም ኣልፎ በይፋ “ፊዚካል ዲማርኬሽን” ይከናወን ብሎ ለህዝብ ባለመንገሩም፡ በኤርትራዊ ጭዋነት ኩራትና ትህትና ጭምር እንነቅፈዋለን:mrgreen:

ነፍስኄር ኣቶ መለስን ከወፈፌው ፑቲን ጋር ማመሳሰላችንን በማስረጃ ኣስደግፈናል። ሁለቱም የማርክስና የሌኒን ቡችሎች ናቸው። ሁለቱም ለሥልጣናቸው ብለው ቀያቸውን ለማስፋት በመስፋፋት ህልም ሰክረውና በዕብሪት ተወጥረው በጎረቤት ህዝቦች ላይ ጦርነት ከፍተዋል። ኣቶ መለስ “ያይን ቀለም” ቦተሊካ ኣራማጅ፡ የ70 ሽህ ኤርትራውያንና ትውልደ ኤርትራዉያን ንብረት ዘርፈው ያባረሩ “ሰው መሳይ በሸንጎ” ነበሩ። ይባስ ብሎም በዓለም ማኅበረሰብ የፈረሙበትን ይግባኝ ዬማይባልበትን ብዪን ከመተግበር ኣሻፈረኝ ብለው፡ ኤርትራንና ህዝቧን ለመቅጣት “ኣይኵናት ኣይሰላም” የሚል መመርያ ተከትለው፡ ወደቦቻችንንም የገመል መጠጫ እንዲሆኑ ተመኝተው በይፋም ለፍፈው ሲናገሩ ሰምተናቸዋል። መጨረሻውም ኣላማረም “ዓባዪ ትግራይን” ሳያዩ፡ ሂደዋል ነጉደዋል ወደዚያኛው ዓለም።

ለኛ ለኤርትራውያን የመሃልና የመስመር ዳኞች፡ ካለ ኤርትራውያን ስውኣት በስተቀር፡ ነፃነትን የሰጠን ማንም ኣካል ዬለም፡ ይቅርና ኣቶ መለስ ኣቶ ኢሳይያስም ጭምር ነጻነትን ኣልሰጡንም።
:mrgreen: ለዛም ነው “ናጽነት ኤርትራ ህያብ ስውኣትና ኢያ!” ማለትም “ነጻነት የተሰው ወንድሞቻችንና እህቶቻችን የሰጡን ስጦታ ነች!” የምንለው። እርግጥ ነው ኣቶ መለስ ወደውም ይሁን በነባራዊው ሁኔታ ተገደው ለሃገረ ኤርትራ ነጻነት በቀዳሚነት “ዕውቅና” መስጠታቸውን እናውቃለን፡ ለዚያ ተግባራቸውም እናደንቃቸዋለን። በሚደነቁበት አድንቀን በሚወቀሱበት ደግሞ (ሙት ወቃሽ ኣያድርገንና) ለትምህርትና መጪው ትውልድ ይማርበት ዘንድ ብለን እንወቅሳቸዋለን፡ተግባባን ወዳጃችን Axumezana። [አራት ሚልየን ነጥቦች- ይህ ምልከታችን የጦርነት ጥቅመኞች (ጦ.ጥ.) ምልከታ ኣያካትትም]
:mrgreen:
Axumezana wrote:
09 Feb 2023, 13:58
የፑቲን፥ ወዳጅ፥ከሆነው፥ ከጌታህ፥ ኢሳያስ፥ ጋር፥ መጣላት፥ ፈልገሃል፥ ማለት፥ ነው። ነፃ፥ አገር፥ የሰጠህን፥ መለስ፥ ከፑቲን፥ ጋር፥ ማወዳደርስ፥ ደደብነትና፥ ከሃዲነት፥ እይደለም?

Axumezana
Senior Member
Posts: 19179
Joined: 27 Jan 2020, 23:15

Re: ሀጠው፥ቀጠው፥ ከምኢሱ፤

Post by Axumezana » 10 Feb 2023, 09:24

ችግርህ፥ እንደፖለቲኮኞቹ፥ በአንድ፥ በኩል፥ጨዋና፥ የመሃል፥ ዳኛ፥ ነኝ፥ እያልክ፥እውነትና፥ ውሸትን፥ እየቀላቀልክ፥ ለማምታታት፥ መሞከርህ፥ ነው።

ከ1991 ጀምሮ፥ እስከ፥1998፥ ከኤርትራ፥ ወደ፥ ኢትዮጵያ፥ ምን፥ ያህል፥ህዝብ፥ተባረረ? ለምን?
መለስ፥ እውቅና፥ ባይሰጥ፥ የኤርትራ፥ እጣ፥ ፈንታ፥ ምን፥ ይሆን፥ ነበር?
የ 1998 - 2000 ጦርነት፥ ኢሳያስ፥ ነው፥ ወይስ፥ መለስ፥ የጀመረው?
መለስ፥ 2000 ላይ፥ ጦርነቱን፥ባያቆም፥ ውጤቱ፥ ምን፥ ይሆን፥ ነበር፥?
ላለፍት፥ሁለት፥ አመታት፥ እስከአሁን፥ የኤርትራ፥ ጦር፥ በትግራይ፥ምን፥ ወንጀል፥ ስራ?

Meleket
Member+
Posts: 5070
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: ሀጠው፥ቀጠው፥ ከምኢሱ፤

Post by Meleket » 10 Feb 2023, 10:39

ወዳጃችን Axumezana የኛ የኤርትራውያን የመሃልና የመስመር ዳኞችን ለጥያቄዎችህ ኤርትራዊ መልሳችንን እንሆ ብለንሃል። በጥሞናና ከቍጭትና ከጥላቻ ስሜት ነጻ ወጥተህ ኣንብበው። ያዝ እንግዲህ
Axumezana wrote:
10 Feb 2023, 09:24
ችግርህ፥ እንደፖለቲኮኞቹ፥ በአንድ፥ በኩል፥ጨዋና፥ የመሃል፥ ዳኛ፥ ነኝ፥ እያልክ፥እውነትና፥ ውሸትን፥ እየቀላቀልክ፥ ለማምታታት፥ መሞከርህ፥ ነው።

ከ1991 ጀምሮ፥ እስከ፥1998፥ ከኤርትራ፥ ወደ፥ ኢትዮጵያ፥ ምን፥ ያህል፥ህዝብ፥ተባረረ? ለምን?
ይህን ጥያቄ ስዬ ኣብርሃ በስልጣን ላይ በነበረበት ግዜ ተጠይቆ ነበር። በ1991 በኢትዮጵያውያን በተለዪም የትግራይ ሰዎች ከኤርትራ ተባረዋል ለምን ተብሎ ተጠይቆ “ስንት ከደርግ ጋር ኣሾክሿኪ የትግራይ ሰው (ትግራዋይ) እንደነበረ እናውቃለን። ሻዕብያ ያባረራቸው የደርግ ኣሾክሾኪዎችን ነው” ብሎ ቁርጡን ተናግሮ ነበር። የደርግ ወታደር ደግሞ ተማርኮ፡ መሳርያውን አስረክቦ በጨዋ ደንብ ነው ወደ ሃገሩ የተሸኘው። በ1998 አካባቢ በፍላጎቱ ወደ ሃገሩ የገባ ኢትዮጵያዊ እንጂ “ያይን ቀለምህ ኣላማረንም" ተብሎ ውጣ ተብሎ ከኤርትራ የተባረረ ኢትዮጵያዊ ዬለም። ስንትና ስንት የትግራይ ሰው እሁን ድረስ ኤርትራ ውስጥ እንደሚኖርም እናውቃለን። ስንቱ የኢትዮጵያዊ የቦለቲካ ቡድንም መጠጊያና መሸሻው ኤርትራ መሆኗን ኣትስትም፡ ደምህት በል አርበኞች በል ወዘተ በል። ኣይደልም እንዴ? :mrgreen:
Axumezana wrote:
10 Feb 2023, 09:24
መለስ፥ እውቅና፥ ባይሰጥ፥ የኤርትራ፥ እጣ፥ ፈንታ፥ ምን፥ ይሆን፥ ነበር?
መለስ እውቅና እንዲሰጥ እኮ ኤርትራውያን ታጋዮቻችን ደህና አድርገው ነበር ስኳር እያላሱ ‘’የመለመሉት’። መለስ ለኤርትራ እውቅና ባይሰጥ ኖሮ፡ ኢትዮጵያን 27 ዓመታት ለመግዛት ባልቻለ ነበር፡ ይህን ደግሞ መለስ ጠንቅቆ ያውቅ ነበር። :mrgreen:
Axumezana wrote:
10 Feb 2023, 09:24
የ 1998 - 2000 ጦርነት፥ ኢሳያስ፥ ነው፥ ወይስ፥ መለስ፥ የጀመረው?
ጦርነቱ የተጀመረው በ1998 ኣይደለም፡ ከዛ በፊት በ1997 ነው። ባድመ ላይ ሳይሆን ዓዲምሩግ ላይ ነው ዋናው ጕዳይ ዬነበረው። ስዉእ ጅግና ኣምባሳደር ኣድሓኖም ገብረማርያም እንዲህ ብሎ ነበር የጻፈው "ኣብ 1997 ዓ.ም. ወያነ ልኡላዊ መሬት ኤርትራ ደፊሮም ህዝብና እንዳበሳበሱ እንከለዉ፡ ፕረዚደንት ነቲ ጉዳይ ካብ ህዝብናን ሚንስትራትን ካልኦት ላዕለዎት ሓለፍትን ዓቢጡዎ፡ ድሕሪ 9 ኣዋርሕ ንዅሎም ሃገራዊ ኣገልግሎት ንምእቶታዊ ልምዓት ኢሉ ኣኪቡ ኢዩ ኣብ ናይ ህልቂት ዉግእ ነቝትዎም።”ብሎ ነው የጻፈው ከዚህ ምን እንረዳለን ግልጽ ነው። :mrgreen:
Axumezana wrote:
10 Feb 2023, 09:24
መለስ፥ 2000 ላይ፥ ጦርነቱን፥ባያቆም፥ ውጤቱ፥ ምን፥ ይሆን፥ ነበር፥?
ጦርነቱን ባያቆም ብሎ ነገር ዬለም፡ ኤርትራ ውስጥ ወደ ተዘጋጀለት ወጥመድ ይገባ የነበረው የጦብያ ሰራዊት ምን ያህል እንደረገፈ የሚያው ቅ ነው የሚያውቀው። ጦርነቱን መለስ ኣይደለም ያቆመው፡ ጦርነቱን ያቆመው ራሱ ጦርነቱ ነው። ወደ ኤርትራ የገባው ሰራዊት ሁኔታዎችን ሲያይ እንደማያዋጣው ሲያውቅ፡ ዬቻለው ወጣ ያልቻለው ደግሞ . . ። ይሄው ነው ጨዋታው።
Axumezana wrote:
10 Feb 2023, 09:24
ላለፍት፥ሁለት፥ አመታት፥ እስከአሁን፥ የኤርትራ፥ ጦር፥ በትግራይ፥ምን፥ ወንጀል፥ ስራ?
"ኣንተ ግብዝ ጓደኛህ ዓይን ውስጥ ያለ ጉድፍ ከማዬት ይልቅ መጀመርያ ዓይንህ ውስጥ ያለውን ግንድ ብታይ ምን ነበር" ያለው ማን ነበር እቴ። ይህን ጥያቄ ከመጠዬቅህ በፊት፡ በለስ ዬቀናው የመሰለው የጦብያ ሰራዊት በሞልቂ በማይድማ በሰንዓፈ ምን ኣድርጎ ነበርም ብለህ እስቲ ራስህን ጠይቅ። የመጠራ ሃውልትን ምን ኣደረገ ብለህ ራስህን ጠይቅ መጀመርያ። ኤርትራውያን ግን ጨዋዎች በመሆናችን አልባሌና እርኩስ ተግባር ያደርጋሉ ብለህ እራስህን ኣታሞኝ። ይልቅስ ወንጀል ተሰርቷል ብለህ የምታምን ከሆነ፡ በገለልተኛ ኣካል እንዲጠናና ገለልተኛው ኣካል ውጤቱን ለህዝብ እንዲያሳውቅ ማድረግ ነው መፍትሄው። ኣይመስልህም ወዳጃችን Axumezana! ሰላምና ጤና ተመኝተንልሃል ባለህበት! :mrgreen:

Axumezana
Senior Member
Posts: 19179
Joined: 27 Jan 2020, 23:15

Re: ሀጠው፥ቀጠው፥ ከምኢሱ፤

Post by Axumezana » 10 Feb 2023, 16:26

መልስህ፥ ያረጋገጠልኝ፥ እንዃን፥ ጭዋ፥ ዳኛ፥፥ ለመሆን፥ ከራስህ፥ ጋር፥ እየተሟገትክ፥ ራስህን፥ የምታታልል፥ እውነትን፥ የምትሸፋፍን፥ ከእውነት፥የሸሸህና፥ የምትሸሽ፥ ተራ፥ትእቢተኛ፥ እብሪተኛና፥ አስመሳይ፥ ሰው፥ መሆንክን፥ነው። I call people of your kind as infected by ascari syndrome sickness!

Meleket
Member+
Posts: 5070
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: ሀጠው፥ቀጠው፥ ከምኢሱ፤

Post by Meleket » 11 Feb 2023, 02:58

ወዳጃችን Axumezana ስለ ትዝብትዎ ኣመስግነንዎታል። ባሉበት ሰላምና ጤናም ተመኝተንለዎታል። ነጥብ በነጥብ ስህተታችንን ነቅሰው ቢያሳዩን ደግሞ እንታረምበት ነበር። ነገር ግን ቅንጣት ታህል ሞራላዊ ብቃት እንደሌለዎት ነው የተገነዘብነው፡ እኛ ኤርትራውያን የመሃልና የመስመር ዳኞች፡ በኤርትራዊ ጭዋነት ኩራትና ትህትና ጭምር። :mrgreen:
Axumezana wrote:
10 Feb 2023, 16:26
መልስህ፥ ያረጋገጠልኝ፥ እንዃን፥ ጭዋ፥ ዳኛ፥፥ ለመሆን፥ ከራስህ፥ ጋር፥ እየተሟገትክ፥ ራስህን፥ የምታታልል፥ እውነትን፥ የምትሸፋፍን፥ ከእውነት፥የሸሸህና፥ የምትሸሽ፥ ተራ፥ትእቢተኛ፥ እብሪተኛና፥ አስመሳይ፥ ሰው፥ መሆንክን፥ነው። I call people of your kind as infected by ascari syndrome sickness!

Post Reply