Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 42808
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

A REGIME IN DIRE CRISIS - በኦርቶዶክስ ማዕበል እስከ ሰሩ የተናወጠው የአቢይ አህመድ አሊ አምባ ገነን ቡድን!

Post by Horus » 10 Feb 2023, 03:41

ዝም ብላችሁ ተከታተሉ አሁን መንግስት ስራ አቁሟል! ትምህርት የለም! ካቢኔ ስብሰባ ላይ ነው! በሚሊዮን የሚቆጠር ፖሊስና ጸጥታ ሕዝባዊ አመጽ ለማስቆም በመላ አገሩ ይታመሳል ። የፈለገ ሰው በፈለገው የዳቦ ስም ሊጠራው ይችላል ! ሃቁ ግ ን ኢትዮጵያ አገር አቀፍ አብዮት ውስጥ ነው ያለችው!

መንግድስት መግዛት አቅቶታል፣ ማስተዳደር አልቻለም! ሕዝብ አልገዛም ብሏል ! በቃ አብዮት ማለት ይህ ነው ! ይህ ሁሉ ለምን ሆነ? በአንድ ግብዝ ዲክታተር ራሱን አምላኪ ቅጥ ማጣት በቃ!


Last edited by Horus on 10 Feb 2023, 03:57, edited 1 time in total.


Horus
Senior Member+
Posts: 42808
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: A REGIME IN DIRE CRISIS - በኦርቶዶክስ ማዕበል እስከ ሰሩ የተናወጠው የአቢይ አህመድ አሊ አምባ ገነን ቡድን!

Post by Horus » 10 Feb 2023, 04:00

ዲክታተር አቢይ አህመድ አሊ በምን ምክንያት ነው ይህን የሰማይ ስባሪ የሚያክል ስህተት ሊፈጽም የቻለው?

እኔ ሆረስ ቃላት በመፍለጥ ግዜያችሁን አላባክንም! በቀጥታ የዲክታተሩን ችግር በስሙ እጠራዋለሁ፣ በዳቦ ስሞቹ ሳይሆን።

ነጥብ 1፣
ዲክታተሩ የተበላ ዕቁብ ሕግን መግደፉ ነው ። የተበላ ዕቁብ ሕግ ማለት አንድ ዲክታተር ወይም ተንኮለኛ ከዚህ ቀደም የተጠቀመበትን ዘዴ መላልሶ ለመጠቀም መሞከር ጂልነት ነው፤ ስልቱ ወይም ብልጠቱ ሁሉም ስላወቀው ማለት ነው። አቢይ ሊያደርግ የሞከረው መለስ ዜናዌ ያደረገውን ብቻ ሳይሆን እራሱ አቢይ በሙስሊም መጅሊስ ላይ ያደረገውን ደባ ነው በኦርቶዶክስ ላይ ሊያደርግም ሲምክር እጅ ከፍንጅ የተያዘው!

ነጥብ 2፣
አቢይ አህመድ ናርሲሲስት ራስ አምላኪ ዲክታተር ስለሆነ ነው ። የዲክታተሩ እጅግ መሰረታዊ እና መውደቂያ በሽታው እራሱን ሁሉን ቻይ፣ ሁሉን አዋቂ፣ ስለሁሉን ሰውና ሕዝብ አውቅላችኋለሁ ባይ የራሱን ምናብና ቅዠት እንደ ነባራዊ ሪያሊቲ የሚያምን ግብዝ ራስ አምላኪ ስለሆነ ነው። ይህ ደሞ የሳይኮሎጂ በሽታ ነው ።

ነጥብ 3፣
በነጥብ 2 መሰረት ራሱን ያገነነው ራስ አምላኪ የኦርቶዶክስን ጥልቀት፣ ግዝፈት፣ ኃይል፣ የሰው የውቀት፣ ክህሎትና የቁስ ሃብት፣ የኦርቶዶክስን ዝናና ክብር ልክ ፈጽሞ ያልተገነዘበ የሚመኘውን የሚያምን በራሱ ምናብ ውስጥ የሚመላለስ ግብዝ ራስ አምላኪ ስለሆነ ነው። ኦርቶዶክስ እጅግ እጅግ ግዙፍና እንደ አለት የጸናች ሓያል እምነትና ተቋም ናት ።

ዲክታተር አቢይ አህመድ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ላይ ያሳየው የእብሪት፣ የንቀት፣ የድፍረትና እዩኝ እዩኝ ባይነት የዚህ የራሱ ልብ ወለድ ራስ አምላኪነት በሽታ ውጤት ነው ። በሳይኮሎጂ አነጋገር ከሪያሊቲ ጋር የተፋታ ሳኮቲክ ማለት ነው ።

ነጥብ 4፣
ዲክታተር አቢይ አህመድ አሊ በእውነተኛ ውስጠ ልቡ የኦሮሞ ብሄረተኛ እንጂ ኢትዮጵያዊ አይደለም፤ የስልጣን እና ዝና ነጋዴ እንጂ ክርስቲያንም አይደለም ። ይህ ሌላው ትልቁ የአቢይ አህመድ መውደቂያ ነው ። በዚህም ምክንያት የዲክታተሩ ቃላት ኢትዮጵያ የሚል ድምጽ ሲያስተጋቡ፣ የዲክታተሩ ተግባር ግን ኦሮሙማ የሚል ሃቅ ያበራሉ ። ይህ መጣረስ ደሞ የዲክታተሩ ውድቀት ሰበብ ነው ።

ኦርቶዶክስ ላዕለ ኩሉ ኢትዮጵያ ዘላለማዊ!!!

Post Reply