Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Wedi
Member+
Posts: 8649
Joined: 29 Jan 2020, 21:44

የኢትዮጵያ ኦርቶዶኦክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ለአብይ አመድ ማፍያ መንግስት የ2 ቀናት ብቻ እድሜ ያለው Ultimatum ሰጠቸው!!!

Post by Wedi » 09 Feb 2023, 12:16

የኢትዮጵያ ኦርቶዶኦክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ለአብይ አመድ ማፍያ መንግስት የ2 ቀናት ብቻ እድሜ ያለው Ultimatum ሰጠቸው!!!

መንግስት የተጠየቀውን ጥያቄ በቀጣይ ሁለት ቀናት ካልመለሰ ሰልፉ የካቲት 05 ያለማንም ከልካይ የሚደረግ ይሆናል።

ጥያቄው ....

➔"መንግስት ከአጉል እልከኝነቱ ወጥቶ ከሕገ ወጦቹ ግለሰቦች ጋር በመተባበር በአደባባይ እየፈጸመ ያለውን የሕግ ጥሰት ዛሬን ጨምሮ በቀጣዮቹ ፪/ሁለት/ ቀናት ውስጥ እንዲያቆም እና ሕግ እና ሥርዓትን እንዲያስከብር፣

➔በኃይል የወረራቸውን መንበረ ጵጵስና እና አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ለቆ ለቤተክርስቲያኒቱ ሕጋዊ መዋቅር እንዲያስረክብ፣

➔ያለአግባብ ያሠራቸውን ካህናት እና ምእመናን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲለቅ፣

➔ቤተ ክርስቲያኒቱ ላይ ለፈፀመው በደል በአደባባይ ይቅርታ እንዲጠይቅ፤

➔በካህናት እና ምእመናን ላይ ለደረሰው ሞት እና የአካል ጉዳት ተገቢውን ካሳ እንዲክስ እና የወደሙ ንብረቶቿን እንዲጠግን በጥብቅ እንጠይቃለን ፡፡..."
የኢኦተቤ/ክ ቅዱስ ሲኖዶስ !

***
Please wait, video is loading...

Abere
Senior Member
Posts: 15443
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: የኢትዮጵያ ኦርቶዶኦክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ለአብይ አመድ ማፍያ መንግስት የ2 ቀናት ብቻ እድሜ ያለው Ultimatum ሰጠቸው!!!

Post by Abere » 09 Feb 2023, 12:42

በጣም ግልጽ እና ቁርጥ ያለ የአቆም መግለጫ ነው። ምርጫው የአብይ አህመድ ነው - ወይ ወደ ጥፋት ይሄዳል ወይ ከጥፋት ይመለሳል። የተጣላው ከ70 ሚልዮን በላይ ከሚሆን የኦርቶዶክስ ምዕምን ጋር ነው ። ይህ ምዕምን በሰማዕትነት ለእመነቱ ጠባቂ ሰራዊት ነው። ከዚህም በላይ የነባሩ እስልምና እምነት ተከታዮች አበረው ይቆማሉ።

Wedi
Member+
Posts: 8649
Joined: 29 Jan 2020, 21:44

Re: የኢትዮጵያ ኦርቶዶኦክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ለአብይ አመድ ማፍያ መንግስት የ2 ቀናት ብቻ እድሜ ያለው Ultimatum ሰጠቸው!!!

Post by Wedi » 09 Feb 2023, 12:44

ከቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ የተወሰደ!
...በዚህ አጋጣሚ ከኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት እና ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ውጭ ሌሎች የክልል ርዕሳን መስተዳድሮችና ከተሞች በተለይም የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር፤ የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልላዊ መንግሥት፤ የሲዳማ ክልላዊ መንግስት፣ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት፤ የሱማሌ ክልላዊ መንግሥት፤ የቤንሻንጉል ክልላዊ መንግሥት፣ የሐረሪ ክልላዊ መንግሥት፣ የአፋርና ጋምቤላ ሕዝቦች ክልላዊ መንግሥት፤ በጎፋ ዞን የሳውላ ከተማ እና ሌሎች ስማቸውን ያልጠቀስናቸው መንግሥታዊ ተቋማት የቤተ ክርስቲያናችንን ጥሪ በመከተል በአግባቡ ሕግና ሥርዓትን ለማስከበር የወሰዳችሁ ፍትሐዊ እና ሕጋዊ መፍትሔዎችን እናደንቃለን፣ በቤተ ክርስቲያንም ስም እናመሰግናለን፡፡ እንዲሁም ሀዘናችሁ ሀዘናችን ነው ብላችሁ ከጎናችን የተሰለፋችሁ አኃት አብያተ ክርስቲያናት፤ የሃይማኖት ተቋማት፣ ድርጅቶች እና ጉባኤያት፤ የእስልምና እምነት ተከታዮች፤ በእምነት የማትመስሉን ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን ስላደረጋችሁልንና ስለምታደርጉልን እርዳታና ትብብር በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ስም እናመሰግናለን፡፡

ጸሎተ ምሕላውን ስናውጅ መንግሥት ሕግ አክብሮ እንዲያስከብር፣ የቤተክርስቲያኒቱን ክብር እና ልዕልና እንዲያከብር፣ በሃይማኖታችን የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ መግባቱን እንዲያቆምና ወደ ውስጡ ማየት እንዲችል ነበር:: ይህ ድርጊት እስከ አሁን ድረስ ግን መንግሥት ለዘመናት ሕጋዊ ተቋም እና የሀገር ባለውለታ የሆነችውን ቤተ ክርስቲያንን ከመስማት እና ችግሯን ከመቅረፍ ይልቅ የማዋከቡን ሥራ አጠናክሮ ቀጥሎበታል፡፡ በዚህም መንግሥት ችግሮችን ኃላፊነት ተሰምቶት እንዲፈታ ያደርገዋል የሚል እምነት ቢኖረንም አገዛዙ ግን ከጊዜ ወደ ጊዜ ልቡ መደንደኑን መመልከታችን በእጅጉ ልባችንን ሰብሮታል....

Post Reply