Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Abere
Senior Member
Posts: 15445
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

የክረምት ወር ጠብቆ የሚነሳው የኢትዮጵያ ጦረነት በመጭው ክረምት አይቀሬ ነው ---- የጦርነት ደመና ቁልሎች በግልጽ ይታያሉ።

Post by Abere » 12 Jan 2023, 15:37

የክረምት ወር ጠብቆ የሚነሳው የኢትዮጵያ ጦረነት በመጭው ክረምት አይቀሬ ነው ---- የጦርነት ደመና ቁልሎች በግልጽ ይታያሉ።ስራ ፈት የሆነው የትግራይ ወንበዴ ድንች እና ሽንኩርት ይተክል ይመስል በየድንጋይ እና ቋጥኙ ስር መሬት እየቆፈረ መሳርያ ይደብቃል። ሀምሌ ግም ሲል ግን እርሻ እና ጉልጓሎ ሳይሆን የፈረደበት የአማራ እና አፋር ሰርቶ አደር እንደ ዝንጀሮ ጥበቃ ከወያኔ ጋር ይፋጠጣል። ወንጀል እና እርግማን እንደ መዳልያ በአንገቱ ያጠለቀው ዐብይ አህመድ የጦርነት አውድማውን በውሸት እና ሽንገላ እያመቻቸ ይገኛል። በሶስት ዙር ብዙዎችን በጦርነት አስጨርሶ አሁንም ምኑም ያልተቋጨ ጉዳይ በእጁ ይዞ እያጨማለቀ ለፈረንጆቹ ደስ ይበል ምስኪን ገበሬ ማስጨረሱ አይቀርም። ወደ ትግራይ እያጋዘ ያለው ስንደ እና ምግብ ብቻ አይደለም የጦር መሳርያ እንጅ። ይህ መሳርያ ክረምት ላይ ወደ ወያኔ እጅ በተለያየ መንገድ ይገባል - ከዚያም ልማደኛው የመከላከያ ሰራዊት ሲፈልግ ወያኔ ሁኖ ወገን ላይ ይተኩሳል ሲሸነፍ የወገን ጦር ሁኖ ይመጣል። ይህ ሁሉ ቁማር አላማው ግልጽ ነው። የሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል በጦርነት አዙሪት እንድ ቀጥል በምንም መልኩ ቢሆን በጎሳ አባዜ በልማት ደቀው ከጨዋታ ውጭ እንድሆኑ የዕርዳታ ጥገኛ የማድረግ የውጭ ሃይላት እና ለኦሮሙማ የተሰጠ ተልዕኮ ነው። የሰሜኑ የኢትዮጵያ ህዝብ የሰላም እና የእደገት ጸር የሆነው ወያኔ የግድ ነፍስ መዝራት እና መኖር አለበት። ወያኔ ከጠፋ የሰሜኑ ህዝብ እንደ አብዛኛው የደቡብ ህዝብ የጸረ ጎሳ ክልል ሃይል ስለሚሆን ይህ በፍጹም የሚፈለግ አይሆንም። በሌላ መልኩ ደግሞ መቸም ቢሆን በቀኝ ገዥዎች ጫን ወደ አገር ውስጥ የገባው የወያኔ እና ኦነግ ህገ-መንግስትን አማራ በፍጹም አይቀበለውም - ስለዚህ ጦርነት ወቅት እየጠበቀ እንደ ክረምት ይገባል። የጦርነት ወጥመድ ላይ የተቀመጠው ቀይ ስጋ የትግሬው ወያኔ ደግሞ መኖሩ እና መሞቱ ሳይታወቅ የጦርነት ማላምያ ሁኖ ይቀጥላል።

Abere
Senior Member
Posts: 15445
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: የክረምት ወር ጠብቆ የሚነሳው የኢትዮጵያ ጦረነት በመጭው ክረምት አይቀሬ ነው ---- የጦርነት ደመና ቁልሎች በግልጽ ይታያሉ።

Post by Abere » 12 Jan 2023, 18:09

ለመጭውን ጦርነት ዋና ገፊ ምክንያት የሚሆነው የወልቃይት እና ራያ ጉዳይ መሆኑ አጠራጣሪ አይደለም። የአብይ አህመድ መንግስት ይህን ጉዳይ ድብብቆሽ ሲጫዎትበት ቢቆይም በመጨረሻ ላይ በእራሱ ላይ እሳት ይጭራል። በመቀጠልም ቅጥ ያጣው የኦሮሙማ እብደት በአዲስ አበባ ከተማ ላይ ነዋሪውን ሳይወድ በግድ ምናልባትም የከተማ ውስጥ ትግል ሊያስጀምር ይችላል። ይህ ደግሞ በድሮን አይሆን፥በአውሮፕላን አይሆን፤ በቦዘኔ ባለቦኔት ቆብ አይሆን ወይም ዘመዶች :mrgreen: ከሱሉልታ በፈረስ ሽምጥ ጋልበው ደረሰው እሳቱን ማጥፋት አይችል አስቸጋሪ ምጥ ሊያመጣ ይችላል።ይህ እውነተኛውን push-up ያመጣል

Post Reply