Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 11594
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

"አብይ አንባገነን መሆን አለበት" እያለ ሲሰብክ የነበረው ታምራት ነገራ የአምባገነንነትን ጣዕም ለወራት ካጣጣመ በኋላ ትናንት በትዊተር "ገረመኝ ማዳንህ" በሎ የመዝሙር ሊንክ ለጥፏል

Post by sarcasm » 24 Dec 2022, 10:18

ምን ተባለ?

- የቤተ መንግሥቱ ነብይ የኢትዮጰያ ኦርቶዶክስን ሰድቧል እና አውግዝ ተብሎ ስብሰባ የተጠራው የኢትዮጵያ ሃይማኖቶች ምክር ቤት ሁለት ሁለት ሃይማኖት ሆነው ተቧድነው ተገኙ ተብሏል። ይሄ ሁሉ ፀብ በእርስ በርስ ጦርነቱ ወይም ሃገር ውስጥ በተፈፀሙ እልቂቶች ምክንያት ሳይሆን በስድብ የተነሳ መሆኑ ገራሚ ነውም ተባለ።

- ዮሐንስ ቧያለው እና ስዩም ተሾመ ተጣልተው ተካሰሱ: ስዩም የአራት ወር እስራት ተፈረደበት። ኢቲቪ ስቱድዮ ሄዶ የሚያስረው ወንድ ጠፋ ተባለ።

- ቀንተሌት ህወሓት ህወሓት በማለት መንግስትን ያገለገለው ወንድሙ ኢብሳ አፉ ለምዶበት ኦህዴድ ያስፃፈውን መዝሙር ህወሓት ነው የፃፈው ብሎ በመዋሸቱ ታሰረ ተባለ።

- "አብይ አንባገነን መሆን አለበት" እያለ ሲሰብክ የነበረው ታምራት ነገራ የአምባገነንነትን ጣዕም ለወራት ካጣጣመ በኋላ ትናንት በትዊተር "ገረመኝ ማዳንህ" በሎ የመዝሙር ሊንክ ለጥፏል አሉ። ቅዱስ መፅሃፍ "በሚገባኝ መንገድ አስተማርከኝ" ይላል ተባለ።