Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 42827
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Noble Amara: የዛይ ጉራጌ ሕዝብ ትንሳኤ !!!

Post by Horus » 21 Dec 2022, 03:13

የጋፋት ሕዝብም አንድ ቀን ይነሱ ይሆናል !

ዛይ ግን በርግጠኝነት አይሞትም !!!



Horus
Senior Member+
Posts: 42827
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: Noble Amara: የዛይ ጉራጌ ሕዝብ ትንሳኤ !!!

Post by Horus » 21 Dec 2022, 03:19

ዘርና ታሪኩ እየጠፋ ያለው ታልቁ የላቄ ጉራጌ (ዛይ) ሕዝብ ። ዛይዎች ሌላ ስማቸው ላቂ ይባላል ። ለምሳሌ እኛ ክስታኔዎች ዛይ አንላቸውም ላቂ ወይም ላቄ ነው የምንላቸው ። የዛይ ሃይቅን ላቂ ደምበል ወይም ላቂ ጀምበር ነው የምንለው !


Noble Amhara
Senior Member
Posts: 13728
Joined: 02 Feb 2020, 13:00
Location: Abysinnia

Re: Noble Amara: የዛይ ጉራጌ ሕዝብ ትንሳኤ !!!

Post by Noble Amhara » 21 Dec 2022, 09:07

Horus wrote:
21 Dec 2022, 03:19
ዘርና ታሪኩ እየጠፋ ያለው ታልቁ የላቄ ጉራጌ (ዛይ) ሕዝብ ። ዛይዎች ሌላ ስማቸው ላቂ ይባላል ። ለምሳሌ እኛ ክስታኔዎች ዛይ አንላቸውም ላቂ ወይም ላቄ ነው የምንላቸው ። የዛይ ሃይቅን ላቂ ደምበል ወይም ላቂ ጀምበር ነው የምንለው !

ሸዋ ምን ማለት እንደሆነ ታውቃለህ?

https://pbs.twimg.com/media/FjrxDuLXgAU ... name=small

ሜዳ ማለት ነው።

https://i.ibb.co/Rz7TKtD/Tcheretu.png

Gafat lived south of Gojam Abay river down to Gelila

Tcherets Shoa Agew south east of Abay River in the Meda of Gohatsion up to Gerarso

Horus
Senior Member+
Posts: 42827
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: Noble Amara: የዛይ ጉራጌ ሕዝብ ትንሳኤ !!!

Post by Horus » 21 Dec 2022, 14:15

ኖብል አማራ
ባለፈው ግዜ እነዚያን ቃላቶች ስትልክልኝ ሸዋ ሜዳ መሆኑን አይቼ ገርሞኝ ደግሜ ረሳሁት ። የሸዋን ኢቲሞሎጂ ለብዙ ግዜ ሞክሬ ያስቸረገኝ ቃል ነበር። ለምሳሌ አዋሽና ሸዋ አንድ ቃል ሁነው አንዱ በአረብኛ መንገድ ከቀኝ ወደ ግራ ብሎታል ። ሌሎች በግዕዝ መንገድ ከግራ ወደ ቀኝ ብለውታል ። ዋ ባዶ ቦታ እንደ ሆነ አውቃለሁ፣ ቃሉም ያገው ነው ። ጌ (ምድር ወይም ቤት) ሲጀመር የቀምጥ (ኮፕት) ቢሆንም ኋላ ያገው ነው ። ለምን ካልክ የሴም ቃል ቤት እንጂ ጌ አይደለም። ስለዚህ ሸዋ ሜዳ የሚለው እኔ ከኢቲሞሎጂ አንጻር ትክክል ነው ። ይህም ባዶ ምድር ምለት ነው ። ሜዳ በደን ያልተሸፈነ ሜዳ (ሜሳ) ማለት ነው ። እንደ ምታየው ሜዳ (ሜሳ) ከፖርቱጊዝ ወይም ላቲን የተወረሰ ነው ። የጉርጌና የጋፋት ሜዳ ዋዲ(ቫሊ) ከሚለው የሴም ስረ ይነሳል። እኛ ኧዲየ የምንለው ጋፋቶች አዴሽ ብለውታል ። በኔ ግምት ሸዋና ዋዲም በርቀት የሚገናኙ ይመስለኛል ።

Post Reply