Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Thomas H
Senior Member
Posts: 13070
Joined: 27 Jan 2007, 16:30
Location: Kaliti
Contact:

ሰበር ዜና : የዓብይ አህመድ ጠባቂዎች ዓብይን ክደው በአሜሪካ ጥገኝነት ጠየቁ

Post by Thomas H » 13 Dec 2022, 23:08

ፅናት ሚዲያ -Tsinat media
17h
·
#ሰበር ዜና
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በጠባቂዎቻቸው ተከዱ
ዉጭ ጉዳይ ሚኒስተር ተጨማሪ ጠባቂ እንዲመድብላቸው እየተሯሯጠ መሆኑ ተሰማ
//
ታህሳስ፣04ቀን 2015 ዓ/ም
ፅናት ሚዲያ-Tsinat Midia
አዲስ አበባ ሸዋ
ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ደህንነት ሲባል ከሳምንት በፊት ወደ አሜሪካ አቅንተው ከነበሩት የደህንነት ሰዎች በአሜሪካን ሀገር መሰወራቸው ተሰማ
በጠቅላይ ሚኒስትሩ ምርጫ የተመለመሉ በኳታር በቻይናና በሳዑድ አረቢያ ከፍተኛ ስልጠና ወስደው ጠቅላዩን ለመጠበቅ ተቀጥረው ይሰሩ ከነበሩት ሰዎች መካል አብዛኞቹ በአሜሪካ ደብዛቸው እንደጠፋ ለፅናት ሚዲያ ከደረሰው መረጃ ተረጋገጠ።
በዚህም መሰረት በአሜሪካን ሀገር የግል ሴኪዩሪቲ ሰራተኛ እጥረት አጋጥሞ እንደነበረ ጠቅላዩም እነዚህን የስራ ባልደረቦቻችንን ወደ ስራቸው እንዲመለሱ ወደ አዲስ አበባ የደህንነት መስሪያ ቤት ተደጋጋሚ ስልክ ደውለው ነበር የሚሉት ምንጮች በዚህ መሰረትም ከጠፉት የደህንነት ሹሞችና አባሎች መካከል ሰባቱ ወደ ሀገር ቤት እንደማይመለሱ እና በስራ ገበታቸው ላይ እንደሌሉ ገልፀዋል።
በተያያዘ ዜና ዉጪ ጉዳይ ሚኒስተር ተጨማሪ ጠባቂ እንዲመድብላቸው እየተሯሯጠ መሆኑ ተሰማ
ከዚህ ቀደም በተለያዩ ሀገራት ጠቅላዩ ሲጓዙ ይዘዋቸው ከሄዱት ቦዲ ጋርዶችና የደህንነት መስሪያ ቤቱ አባሎች በድምሩ 7 የሚጠጉ አባሎች በዛው መቅረታቸው አብዛኛው ህዝብ የሚያውቅ ይመስለኛል ያሉት የመረጃ ምንጩ በአሁኑ ስዓት ጠቅላይ ሚኒስትሩን የሚያጅበው ሀይል አነስተኛ በመሆኑ እዚህ ሀገር ቤት ያለውን የመንግስት ሹማምንት ጭምር ስጋት ውስጥ ጥሏል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርም ጉዳዩን ከአሜሪካ መንግስትና ከአሜሪን ኢምባሲ ቢሮ ጋር በመነጋገር በአፋጣኝ ተጨማሪ ጥበቃ ለመላክ ሳምባቸው እስኪቆለፍ እየሮጡ ነው።
//
"ውድ የፅናት ሚዲያ ቤተሰቦች የሚዲያ ቻናላችን #ሼር #ላይክ #ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።"
//
====
ወቅታዊ ፤ ትኩስ እና የተሟላ መረጃዎችን ለማግኘት
//
Youtube: https://youtu.be/LKVCaVUZBm4
//
https://www.facebook.com/ፅናት-ሚዲያ-Tsinat ... 519161840/
//
https://t.me/SintayehuChekol
በተቀመጡት ሊንኮች መረጃዎችን ይከታተሉ ።




Post Reply