Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Abe Abraham
Senior Member
Posts: 14414
Joined: 05 Jun 2013, 13:00

ዓሊ ዓብደላ ሳልሕና ሑሲዎች !!! ከታሪክ ምን ትማራለህ ?

Post by Abe Abraham » 12 Nov 2022, 18:26

  • ዓሊ ዓብደላ ሳልሕና ሑሲዎች !!! ከታሪክ ምን ትማራለህ ?
  • ዓሊ ዓብደላ ሳልሕ ከ ሑሲዎች በፉክክርና ክርክር ገብቶ ለብዙ ጊዜ ተዋጋ ። ከስልጣኑ ከመውረዱ በፊት እሱ ለመጨረሻ በተራራማውን የሃገረ ሑሲ ሳዕዳ በተለያዩ ኣቅጣጫዎች ውግያ ሲከፍት ሳዑዲያ ደሞ በበኩልዋ ከሳዕዳ በሚያዋስኑ ደንበሮችዋን ሆና ጥቃቱን ትደገፍ ነበር ። ሑሲዎች ለረዘም ያሉ ሳምንቶች ጸንተው ከተዋጉ ቡኋላ ትንሽ ድክመትና ተሸናፊት ሊያሳዩ በቀረቡበት ሰዓት ዓሊ ዓብደላ ውግያውን ሊያቁምና ከበባውን ሊያነሳ ወሰነ ። ከዚያ በወራት ነው መሰለኝ ውሳኔውን ሊያብራራ ሲጠየቅ " ምክንያቱ ሰብኣዊ ርህራሄ ነው። ሁኔታቸው በጣም መጥፎ ነበር ። " የሚል መልስ ሰጠ ።

    የቱኒስያና የግብጽ ህዝባዊ ፍንዳታዎች ተከትሎ በየመንም ጭምር ተመሳሳይ ሁኔታ ተፈጥሮ ዓሊ ዓብደላ ሳልሕ ከስልጣኑ ወርዶ በ ዓብድረቦ መንሱር ሃዲ ሲተካ ሑሲዎች ከተራራቸው ወርደው በሰንዓ ገብተው ባለ ምንም ተቃውሞ የወታደሮችን ከባድ መሳርያ በቁጥጥራቸው ስር ኣስገቡት ። ከዚያም ዓብድረቦን ከቤቱ እንዳይንቀሳቀስ ከልክለው ከነሱ ድርድር እንዲከፍት ጫና ኣደረጉለት ። እንደሚባለው የሑሲዎች ፍላጎት በዓብድረቦ የሚመራ መንግስት ተካፋይ ሊሆኑ እያለ ፡በሳዑዲ ዓረብያ ግፊት ፡ ዓብድረቦ ሑሲዎች የመንግስት ሰራዊት ከባድ መሳርያ ኣስረክበው ወታደሮቻቸው ወደ ሳዕዳ እንዲመልሱ ጠየቃቸው ። በዛው ነጥብ መረዳዳት ሊደረስ ስላልቻለ ሑሲዎች በኣለም ታዋቂነት እንድናገኝ ይረዳናል ብለው ይዘውት የነበረው ሰው ከሰንዓ ኣምልጦ ወደ ዓደን ገባ ። በዓደን ብዙ ሳይቆይ ወደ ሳዑዲያ ሄዶ በኣሪቱ ህጋዊ መሪነቱ ተረጋግጦለት በህግና በስሙ በሳዑዲያና ተባባሪዎቻቸው - ኢማራትና ቐጠር - በሑሲዎች ላይ ውግያ ተከፈተ ።

    ያን ጊዜ ዓሊ ዓብደላ ሳልሕ የመን በባእድ ስትጠቃ ከየመን ጋር መቆም ኣለብኝ ብሎ ለሑሲዎች ድጋፉ ኣሳይቶ ከቆየ በኋላ
    ፡እንደሚባለው፡ሳዑዲዎች ከሱ ጋር ልዩ የመገናኛ መስመር ስለ ከፈቱ ከሰንዓ በመኪና ሊያመልጥ ሲሞክር በተከታታዮቹ (የሑሲ ሰዎች) ተገድሎ ሞተ ። ያዳናቸው ኣላዳኑትም ማለት ነው!!!!