Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 42846
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

ከረምቦላ ጨዋታ

Post by Horus » 03 Nov 2022, 22:56

የትግሬ ጦርነት ምዕራፍ ሁለት!

ጦርነት በአመጽ የሚካሄድ ፖለቲካ ነው ብለናል ። ይህ ሳይንስ ነው ።

ፖለቲካ ደሞ ልክ እንደ ካራምቦላ ጨዋታ ነው፤ አንዱ ጠጠር አንዱን ጠጠር ሲመታ የቀሩት ጠጠሮች ሁሉ በመነቃነቅ ቦታቸውን ይለውጣሉ ። አዲስ የጠጠሮች ሰልፍ ይፈጠራል!

ስለዚህ አንድ ፖለቲከኛም ሆነ የጦር መሪ ችሎታ የሚለካው ፊቱ ላይ ያለውን ጠላት በመምታቱ አይደለም ። አንዱ ከተመታ በኋል ቀጥሎ የሚመጣውን የሃይል አሰላልፈና አዲስ የሃይል ሚዛን ቀድሞ በማወቁ ነው።

ለምሳሌ ትላንት ትህነጎችን በመርህ ደረጃ ለመብለጥ ሲባል ሕገ መንግስቱን አክብሩ ተባሉ ። እናም ትጥቅ ፍቱ ተባሉ ። ባንድ እራስ ሁለት ምላስ፣ ባንድ አገር ሁለት መከላከያ ሰራዊት ካካ ነው ተባሉ ። ትህነግ ይህው ዛሬውኑ ኦሮሞ አማራ፣ ሱማሌ አፋር ሁሉ ግዙፍ ጦር ይዞ ትግሬ ብቻውን በምን ሕገ መንግስት ነው ጦር የሚፈታው እያለ ነው።

አቢይ አህመድ በጎሳ ፈረስ እየጋለበ ትህነግን አያሸንፍም፣ ትህነግን አያጠፋም የሚባለው ለዚህ ነው ።

የጻድቃንና ጌታቸው (ሁለት ራያዎች) አንድ ዶክመንት መፈረም ምንም ማለት አይደለም። ትህነግ ይከፋፈላል! ገሚሱ ብልጽግና ገብቶ የውስጥ አርበኛ ይሆናል፤ ገሚሱ በረሃ ገብቶ የውጭ አርበኛ ይሆናል ።

ዉጊያው ለግዜው ጋብ ብሎ ሁሉም እረፍት ይወስድና ጦርነቱ ይቀጥላል!

የሚመጣው ዝናብ ካድማስ ባሻገር ባለው ደመና ይታወቃልና !!!