Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Wedi
Member+
Posts: 8649
Joined: 29 Jan 2020, 21:44

የድርድሩ ውጤት ይህ ከሆነ ህወሃት በዜሮ ወጥታለች/ማለትም ህወሃት እጅ ወዳላይ ብላለች!!

Post by Wedi » 02 Nov 2022, 12:47

የድርድሩ ውጤት ይህ ከሆነ ህወሃት በዜሮ ወጥታለች/ማለትም ህወሃት እጅ ወዳላይ ብላለች!!

በደቡብ አፍሪካ በህወሃት እና በፒፒ የተደረገው ስምምነት

በደቡብ አፍሪካ በተካሄደው የሰላም ውይይት የህወሓት መዋቅር ፈርሶ የፌደራል መንግሥት የሚመራው ጊዜያዊ አስተዳደር እንዲቋቋም እና ቡድኑ ሙሉ በሙሉ ትጥቅ እንዲፈታ ስምምነት ላይ ተደረሰ።

በደቡብ አፍሪካ ለስምንት ተከታታይ ቀናት ሲካሄድ የነበረው የሰላም ድርድር የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት፣ የግዛት አንድነት እና ዘላቂ ሰላም በሚያረጋግጥ መልኩ በስምምነት መቋጨቱን ከውስጥ ምንጮች የተገኙ መረጃዎች ይጠቁማሉ።

ለሁለት አመታት የዘለቀው የሰሜኑ ጦርነት መቋጫ እንደሚሆን የተገመተ የሰላም ስምንነት ፊርማ በዛሬው እለት በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ በኢትዮጵያና በህወሓት ተደራዳሪዎች መፈረሙን ያስታወቁት ምንጮች ፤ ውይይቱ የሀገራችንን ብሔራዊ ጥቅም ባስጠበቀ፣ የሕግ የበላይነትን ባረጋገጠ እና ለውጭ ጣልቃ ገብነት እድል በማይሰጥ መልኩ በስኬት መጠናቀቁን ገልጸዋል።

የስምምነት አጀንዳዎች፦

  • ህወሓት ሙሉ በሙሉ ትጥቅ ለመፍታት መስማማቱን፦ በስምምነቱ መሰረት ከዛሬ ጀምሮ በሰላሳ ቀናት ውስጥ ቡድኑ ሙሉ በሙሉ ትጥቅ እንደሚፈታ፤ ይህንን ውሳኔ ተግባራዊ ለማድረግ የሁለቱ ወገን ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች በ24 ሰዓት ውስጥ አመቺ ቦታ መርጠው ንግግር ያደርጋሉ፤

  • ስምምነቱ በተፈረመ አምስት ቀናት ውስጥ የሁለቱ ወገን ወታደራዊ አመራሮች የትጥቅ ማስፈታት ሂደቱ የሚመራበትን ዝርዝር አፈጻጻም በጋራ በማውጣት ተግባራዊ ሥራዎችን መሥራት ይጀምራሉ፤

  • ወገን ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች በተገናኙ አስር ቀናት ውስጥ ህወሓት ያሉትን ሁሉንም የቡድን እና ከባድ መሣሪያዎች ለመከላከያ ሠራዊት ያስረክባል፤

  • ስምምነቱ በተፈረመ ሰባት ቀናት ውስጥ የፌደራል መንግሥት መቀሌን ተረክቦ በከተማው ውስጥ እና ዙሪያ ሁሉንም አይነት የጦር መሣሪያ ያስፈታል፤

  • በአጭር ቀናት ውስጥ አሁን ያለው የህወሓት መዋቅር ፈርሶ የፌደራል መንግሥት የሚመራው የጊዜያዊ አስተዳደር ይቋቋማል። በሚዋቀረው ጊዜያዊ አስተዳደር ውስጥም የትግራይን ሕዝብ የሚወክል አካል ይሳተፋል፤

  • የሀገር መከላከያ ሠራዊት ከጎረቤት ሀገራት የሚያዋስኑ የድንበር አካባቢዎችን ደኅንነትና ሰላም የሚያረጋግጥ ስምሪት የሚያደርግ ይሆናል። መከላከያ ሠራዊቱ በማንኛውም የትግራይ አካባቢዎች ተንቀሳቅሶ ሕግ የማስከበር ስልጣኑን ከህወሓት ሙሉ በሙሉ ይቀበላል። ህወሓት ለተግበራዊነቱ ምንም አይነት እንቅፋት እንደማይፈጥር ተስማምቷል።

  • የሚመሰረተው ጊዜያዊ አስተዳደር በሁሉም የትግራይ አካባቢዎች የማኅበራዊ አገልግሎቶች በፍጥነት እንዲጀመሩ ሁኔታዎች ያመቻቻል፤ ተግባራዊነታቸውን ያረጋግጣል፤

  • ህወሓት ያለ ፌደራል መንግሥት እውቅና ከማንኛውም የውጭ አካል ጋር ግንኙነት ማድረግ ያቆማል። እንዲህ አይነት ተግባር የሚፈጹ ግለሰቦች ካሉ በሀገሪቱ ሕግ የሚጠየቁ ይሆናል።

Za-Ilmaknun
Member
Posts: 4487
Joined: 15 Jun 2018, 17:40

Re: የድርድሩ ውጤት ይህ ከሆነ ህወሃት በዜሮ ወጥታለች/ማለትም ህወሃት እጅ ወዳላይ ብላለች!!

Post by Za-Ilmaknun » 02 Nov 2022, 13:07

This are the rosy talking points as coined by the ruling group cadres. The details are something different. :mrgreen: It could be the second coming of the Algiers' agreement. :lol:

Revelations
Senior Member+
Posts: 34573
Joined: 06 Jan 2007, 15:44

Re: የድርድሩ ውጤት ይህ ከሆነ ህወሃት በዜሮ ወጥታለች/ማለትም ህወሃት እጅ ወዳላይ ብላለች!!

Post by Revelations » 02 Nov 2022, 13:16

Za-Ilmaknun wrote:
02 Nov 2022, 13:07
This are the rosy talking points as coined by the ruling group cadres. The details are something different. :mrgreen: It could be the second coming of the Algiers' agreement. :lol:
Very true. BBC news reporter just said "both sides to disarm.." :lol: :lol: :lol: "The neighboring regions to disarm.." said Kalkidan Ybeltal, BBC reporter on BBC World.

Revelations
Senior Member+
Posts: 34573
Joined: 06 Jan 2007, 15:44

Re: የድርድሩ ውጤት ይህ ከሆነ ህወሃት በዜሮ ወጥታለች/ማለትም ህወሃት እጅ ወዳላይ ብላለች!!

Post by Revelations » 02 Nov 2022, 13:27

This twit from a staunch TPLF supporter should give you what's coming after the party of fake success.

Wedi
Member+
Posts: 8649
Joined: 29 Jan 2020, 21:44

Re: የድርድሩ ውጤት ይህ ከሆነ ህወሃት በዜሮ ወጥታለች/ማለትም ህወሃት እጅ ወዳላይ ብላለች!!

Post by Wedi » 02 Nov 2022, 13:28

Revelations wrote:
02 Nov 2022, 13:16
Za-Ilmaknun wrote:
02 Nov 2022, 13:07
This are the rosy talking points as coined by the ruling group cadres. The details are something different. :mrgreen: It could be the second coming of the Algiers' agreement. :lol:
Very true. BBC news reporter just said "both sides to disarm.." :lol: :lol: :lol: "The neighboring regions to disarm.." said Kalkidan Ybeltal, BBC reporter on BBC World.
Za-Ilmaknun and Revelations you are both 100% spot on. I am fooled to post Dire Tube's post who the major Wutaf Nekay / ሜጀር ውታፍ ነቃይ as true news.

Sorry for posting fake news and misleading you guys..

Revelations pls give me link for BBC report

Post Reply