አብን የሰሜኑን ጦርነት በሰላማዊ አማራጭ ለመፍታት የሚደረጉ ጥረቶችን እንደሚደግፍ አስታወቀ
*************************
የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ /አብን/ የሰሜኑን ጦርነት በሰላማዊ አማራጭ ለመፍታት የሚደረጉ ጥረቶችን እንደሚደግፍ አስታወቀ።
ፓርቲው በወቅታዊ ጉዳይ በሰጠው መግለጫ፣ ከአሸባሪው ህወሓት ሥሪት እና ባህሪ አንፃር ቡድኑ ሰላምን አማራጭ እንደማያደርግ ገልጿል።
ቡድኑ ለዓመታት በጭቆና ሥራዓት እና ሕዝብን በጠላትነት ጭምር በመፈረጅ ሲንቀሳቀስ የነበረ መሆኑን የፓርቲው ምክትል ሊቀመንበር አቶ መልካሙ ሹምዬ ተናግረዋል።
በ3 ዙር ባደረገው ወረራ በአማራ እና አፋር ክልሎች ሰብአዊ እና ቁሳዊ ውድመት ያስከተለው አሸባሪው ህወሓት፣ ለዳግም 4ኛ ዙር ወረራ ጊዜ መግዣ እና የእፎይታ ጊዜ እየፈለገ እንደሆነም ገልጸዋል።
አንዳንድ ምዕራባውያን ሀገራት እና ተቋማት አሸባሪው ህወሓት እንዲያገግም ፍላጎታቸውን እና ድጋፋቸውን በአደባባይ እያሳዩ መሆኑን በመግለጫው ተነሥቷል።
በደቡብ አፍሪካ እየተደረገ ባለው በሰላም ንግግር ሕገ-መንግሥታዊ መርሆች መጠበቅ እንዳለባቸውም አብን ጠቁሟል።
በአማራ እና አፋር የወደሙ ተቋማትን መልሶ ከመገንባት አንፃር ሁሉም ሊረባረብ እንደሚገባም የአብን ሊቀመንበር ዶ/ር በለጠ ሞላ አንሥተዋል።
በሙሉ ግርማይ
Please wait, video is loading...