Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 42853
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

የደቡብ ክልል ቀውስና ያቢይ አህመድ አርባ ምንጭ ድራማ!!

Post by Horus » 02 Nov 2022, 01:25

ዛሬ እዚህ ER Forum ላይ አንድ ቪዲዮ ተለጥፎ ነበር ። ቪዲዮው አቢይ አህመድ ከእርስቱ ይርዳው ጋር ሆኖ በአርባ ምንጭ ሕዝብ እየዘፈነለት እሱ የራሱን መኪና እየነዳ የሚያሳይ የኪም ኢል ሱንግ አይነት አይን ያወጣ ፕሮፓጋንዳ ነው ። ቪዲዮ የተሰራው እራሱ አቢይ ከፈበረካቸው ሺ እልፍ ፌክ ዩ ቲዩብ ቻነሎች አንዱ ነው ። አቢይን ንጉስ ይለዋል! እዚህ የሚያዘወትር የብልጽግና ቲፎዞ ያቢይን ተወዳጅነት ለማሳየት ለጥፎት ነበር!!

ትልቁ ጥያቄ ዛሬ ላይ ያቢይ መንግስት ስንትና ስንት አገር አቀፍና አለማ አቀፍ ውጥረት ላይ እያለ ይህ የአርባ ምንጭ ድራማ ለምን አስፈለገ? የሚለው ነው። ልብ በሉ አቢይ አርባ ምንጭ የራሱን መኪና እየነዳ የሚዝናናው በታላቁ የፍቅርና ሰላም ሕዝብ በጋሞ ፣ በዶርዜ ሕዝብ መሃል ነው !

የሱ ሕዝቦች፣ ኦሮሞች ግን በወለጋ አይደለም እሱን በሰልፍ ሊቀበሉ ሌላ ጎሳ በሰላም አይኖርም። አቢይ በአርባ ምንጭ የፍቅርና ሰላም ካልቸር ውስጥ ሲዝናና የሱ ሕዝቦች ኦሮሞች በሰላሌ ቄስና ዲያቆን ያርዳሉ! ይህን መሰል በቪቿል ሪያልቲ ህልም ውስጥ ለመኖር የሚጥር ፍጡር ነው አቢይ ማለት! ለምንም ነገር ሃላፊነት የማይወስድ የዲዝኒ ላንድ ተጫዋች ህጻን!!!

ደቡብ በብልጽግና በጉልበት በክለስተር ተጨፍለቅ ተብሎ አቅም ስለሌለው ያን የኦሮሞ ትዕዛዝ ተቀብሎ አዲስ ክልል ሊሆን በብርቱካን መደቅሳ ሬፈረንደም እንደ መንጋ እየተነዳ ነው ። እርስቱ የሚባለው የ11ኛ ክፍል ካድሬ እየተሽኮረመመ ላቢይ ሲያደገድግ ማየት ራሱ አንድ ትርኢት ነው! እዚም እዛም ውስጥ ለውስጥ ቅዋሜዎች ስላሉ (5 ክልልነት የጠየቁና 6 ልዩ ዞኖች ናቸው ባንድ ክለስተር የተጨፈለቁት) ይህን ለማረጋጋት ነው አቢይ ዛሬ በዚህ የተጣበበ ሁኔታ አርባ ምንጭ ድራማ ለመስራት የሄደው !!!

ልብ በሉ የጋሞ ህዝብ ልክ እንደ ጉራጌ ሕዝብ ነው ። ስኛት ያለው፣ ሴራ ያለው ስርዓት ያለው ሕዝብ ነው! አንድን መንግስት ወደከው ጠላሃው እስከ ሚነሳ ድረስ እንደ መንግስት ታስተናግደዋለህ ! ጋሞ ባለጌ ህዝብ አይደለም! ጋሞ ክቡር ሕዝብ ነው! እራሱንም እንደዚያው ስለሚያከብር ማለት ነው ። ግን ጋሞ ፖለቲካውን ከማንም በላይ የሚያውቅ ሕዝብ ነው ።

ለምሳሌ አርባ ምንጭ አለ ምንም ጥርጥር የአዲሱ ደቡብ ክልል ዋና ከተማ ይሆናል ። እነወላይታ ሶዶ ምን እንደ ሚሆኑ አይታወቅም ። አቢህ አህመድ ይህን ሁሉ የደቡብ ጎሳ ፖለቲካ ቀውስ ለማለሳለስ ነው የሄደው ። ድራማው ደሞ የተቀናበረው በእርስቱ ይርዳው ነው ። ሌላው የጉራጌ ሙሰኛ ኮራፕት የድሮ ጉራጌ ዞን ፕሬዚዳንት ትላንት ከስልጣን ተወግዶ ነው ዛሬ አቢይ ጎፋ የሄደው !

54ቱ የደቡብ ጎሳዎች የኦሮሙማ ራስ ምታት መሆናቸው ገና መጀመሩ እንጂ ማብቂያው አይደለም !