Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Wedi
Member+
Posts: 8649
Joined: 29 Jan 2020, 21:44

ይድረስ ለውታፍ ነቃዮች እና ለመደመር ካምፕ ወዶ ገብ አባላት በሙሉ

Post by Wedi » 01 Nov 2022, 04:47

ይድረስ ለውታፍ ነቃዮች እና ለመደመር ካምፕ ወዶ ገብ አባላት በሙሉ

Ermias Legesse Wakjira

ይድረስ ለመደመር ካምፕ ፣

ዛሬ መሪያችሁ አብይ አህመድ አሊ ይህንን ብሏል። ንግግሩን እንደታዘብኩት ከሆነ በቀጣይ ለምታካሂዱት የተቃውሞ ሰልፍ ጥሩ ጥሩ መፈክሮች ይወጡታል።

እነሆ ዲስኩሩ፣

" በምግብ ራስን መቻል የሚለውን ራዕያችንን ማሳካት የምንችለው ዘላቂ ሰላም ሲኖር ብቻ ነው ። ስለዚህ ከሰላም አንጻር አሁን እየሰራን ያለነው ህውሓትን የማሳመን ስራ ነው ። ህውሓቶች የአገሪቷን ህግ እና ሕገ መንግሥት እንዲያከብሩ እና እንደ አንድ ክልላዊ መንግስት እንዲንቀሳቀሱ ነው ። ህውሓቶች ፍላጎታችንን ከተረዱና የራሳቸውን ሕገ መንግሥት አምነውበት በሕገ መንግሥቱ መሰረት ከተንቀሳቀሱ ሰላም ይረጋገጣል። ከግራ እና ከቀኝ የተለያዩ ጣልቃ ገብነቶች ቢኖሩም እኛ ኢትዮጵያውያን የራሳችንን ጉዳዮች በራሳችን ከፈታን ሰላማችንን እናረጋግጣለን።"

አብይ አህመድ አሊ

እስቲ እኔ ደግሞ ጥቂት መፈክር ላግዛችሁ። ግራ እጃችሁን ለመፈክር ወደ ላይ ስቀሉ፣

፩. ህውሃት ሆይ! የአገሪቱን ሕገ መንግሥት አክብር!
፪. ህውሃት ሆይ! እንደ አንድ የኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ተንቀሳቀስ!
፫. ህውሃት ሆይ! የመሪያችን አብይ አህመድ ፍላጎትና ልመና ሕገ መንግስቱን አክብራችሁ እንድትንቀሳቀሱ ነው!
፬. እኛ ኢትዮጵያውያን የራሳችንን ችግር በራሳችን በመፍታት ሰላማችንን እናረጋግጣለን!

:!:
Please wait, video is loading...
:!:
:!:
Please wait, video is loading...