“ለመሆኑ በስብሰባው የሚካፈሉት እነማን ናቸው?”
ሚኒስትሩ የማስታወሻ ደብተሩን ገላልጦ ማንበብ ጀመረ።
“ . . . መለስ ዜናዊ - ዋና ፀሀፊው ማለት ነው፣ ስዬ ኣብርሃ፣ ፃድቃን ገብረትንሳኤ፣ ኣባይ ፀሀዬ፣ ስብሀት ነጋ፣ አለምሰገድ ገብረአምላክ፣ ክንፈ ገብረመድህን - ይኸ የህወሀት የስለላ ጉዳይ ሀላፊ ነው። ተወልደ ወልደማርያም - ስዩም መስፍን - ይኸ የውጭ ጉዳዮቻቸውን የሚከታተል ነው፣ እና . . . እና ለዘመናት እንደ አሳ እየተሙለጨለጨ ሲያመልጠን የኖረው የወያኔ ቁልፍ ሰው . . . ሀየሎም አርአያ! . . . እነዚህ ናቸው ፊትአውራሪዎቹ። እነዚህ ተወገዱ ማለት ወያኔ ኣከተመለት ማለት ነው። በጣም . . . በጣም . . . ባለን አቅም ሁሉ መስዋእትነት ከፍለን እነዚህን መርዘኞች ካጠፋን ሁሉም ነገር ይዘጋል . . . ሁሉም ነገር ይዳፈናል። የኢትዮጵያ ህዝብም የእፎይታ ባለቤት ይሆናል። ይኸው ነው!”
ገጽ 17-18 የቡርቃ ዝምታ በተስፋዬ ገብረአብ 1992 ዓ.ም
ትንሽ ነገሮችን ለመታዘብ ያህል ነው። ይህ ጥሁፍ በ1992 ነፍስኄር ተስፋዬ ገብረአብ ከጣፈው የቡርቃ ዝምታ የተቀነጨበ ነው። አሁን ካለው ነባራዊ ሁኔታ ጋር እንድናናብበው ነው። የማስታወሻ ደብተሩን የገለጠው ሚኒስትር የደርግ ሚኒስትር እንደነበር ነው ተስፋዬ የተረከልን። . . . “ከምኡ’ዩ ዘሎ እቲ ወረ!” ብሎ እንዳቀነቀነው ኤርትራዊ ድምጻዊ ተመስገን (ጣኒቆ) . . . አሁንም ከሰላሳ ዓመታት በኋላም ወሬውም ጨዋታውም የተቀየረ አልመሰለም። ኣይደል?
ሰላም ዚደሊ ሰላም ይሃቦ፡
ውግእ ዚደሊ ባርዕ ትረኽቦ! (ድምጻዊ ሳሚ ብርሃነ)