Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 42856
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

የደቡብ አፍሪካው ክርክር ከትህነግ ሳይሆን ካሜሪካ ጋር ነው!

Post by Horus » 27 Oct 2022, 01:22

የዛሬ ሶስት ቀን ይህን ብዬ ነበር። ኢትዮጵያ ጦር ሜዳ ላይ እያሸነፈች ከትህነግ ጋር የምታደርገው ድርድር አይደለም ። ድርድር ካለ የሚደረገው ካሜሪካ ጋር ነው፤ ያም ማለት አሜሪካ ጣልቃ መግባቱን እንዲያቆም ማለት ነው ። ይህው ዛሬ የተረጋገጠው ያ ነው። አሜሪካ አደራዳሪ ሳይሆን ተደራዳሪ ነው ተባለ!

ቋንቁና የትግሬ ጉዳይ፤
ቋንቋ ሳይጸዳ ሃሳብ አይጸዳም። ሃሳብ ሳይጸዳ ድርድር አይጸዳም ። ስለዚህ በደቡብ አፍሪካ ምን እየሆነ ነው?

ድርድር? ምንድን ነው የሚደረደረው? ሃሳብ ነው? ብርጭቆ ነው? መጽሃፍ ነው? ስለዚህ በደቡብ አፍሪካ ምንም አይነት ድርድር እየተደረገ አይደለም።

ድልድል? ምንድን ነው የሚታደለው? ምንድን ነው ለዚም ለዛም የሚታደለው? የሚሰጠው? ገንዘብ? መሬት? አስቤዛ? የዝናብ ልብስ? ምናልበት ስልጣን? ስለዚህ በደቡብ አፍሪካ ምንም አይነት ድልድል እየተደረገ አይደለም።

ንግግር? ንገር = ቴል፣ ንግግር =ቴሊንግ። ማነው ለማ የሚነግረው? ምንድን ነው ማ ለማ የሚነግረው? መርዶ፣ ልደት? አደጋ? ናፍቆት? አው በደቡብ አፍሪካ የሆነ ንግግር ሊኖር ይችላል።

ውይይት? ስለ ለምን ነው የሚወያዩት? ውይይት = አውያት = ጩኧት ወይም አቤቱታ ነው ። ወይይት ወይ ወይ ማለት ተማጽኖ ማድረግ ነው ። ማነው ችግሩን በማ ላይ ዋይ ዋይ የሚለው? ስለዚህ በደቡብ አፍሪካ ወይይት የለም።

ሙግት? ሙግት ምንድን ነው? ሙግት ወቱጋገት ማለት ስለአንድ ነገር ማውጣትና ማወረድ፣ ከምክክር የጠነከረ ክርክር ማለት ነው ።

ክርክር? ፖለቲካ አንድም በሰላም አንድም በአመጽ ይካሄዳል ሲባል ይህ ነው ። ሰላማዊ የፖለቲካ ትግል የሚደረገው በክርክር ነው ። አመጻዊ የፖለቲካ ትግል የሚደረገው በጥይት ነው ፣ በዱላ ነው። ስለዚህ በደቡብ አፍሪካ እየተደረገ ያለው ክርክር እንጂ ድርድር አይደለም።

ልውውጥ? ለውውጥ ማለት ኒጎሺዬት ማድረግ ሲሆን ንግድ ላይ አንድ ነገር ለሌላ ነገር መለዋወጥ፣ ላንድ ነገር አንድ ነገር መስጠት ማለት ነው። ሰው ቤት ሲገዛ፣ ሽሮ ሲገዛ፣ ጫማ ሲገዛ የእቃና የዋጋ ልውውጥ ኒጎሺዬሽን ያደርጋል ። ለምሳሌ የትግሬና አማራ ድምበር ከሆነ የልውውጥ ክርክሩ አው በደቡብ አፍሪካ ልውውጥ (ኒጎሺዬሽን) ሊኖር ይችላል። ያ ከሆነ ደሞ ያለው ድርድር ሳይሆን ልውውጥ ነው ።

ዝብብር፣ ዝርርብ፣ ምልልስ የሚባሉት ወሬ መመላለስ ማለት ነው። ማውራት መናገር ( ቱ እስፒክ ) ማለት ነው ። እርግጥ ውል (መስማማት) ከማውራት (አውራር) ይመነጫል ። ስለዚህ ማውራት (ዝርርብ) ከንግግር ጋር ይጠጋል። ነገር ግን ክርክር አይደለም ። ለምሳሌ በሃሳብ የተለያዩ ሰዎች አንድ ላይ አውርተው አንድ ውል ላይ ይደርሳሉ በክርክር ሳይሆን ወሬ በመለዋወጥ ማለት ነው ። ይህ የሚሆነው ስምምነት ሲሆን ነው ።

ስምምነት? ስምምነት ምንድን ነው? ስምምነት አንድ አይነት ሃሳብ፣ አላማና ተግባር መያዝ ማለት ነው ። ስለዚህ በደቡብ አፍሪካ ስምምነት እየተደረገ አይደለም። ትህነግና ኢትዮጵያ አንድ አይነት ሃሳብ፣ አላማን ተግባር የላቸውም ። ለዚህ ነው ጦርነት የሚዋጉት!

በደቡብ አፍሪካ ስምምነት እየተደረገ ነው የሚሉ ሰዎች የስምምንት ትርጉም የማያውቁ ናቸው ።

ስለዚህ በዋናነት የደቡብ አፍሪካው ድራማ ስሙ ድርድር አይደለም ። የትህነግ ድርጅትና የኢትዮጵያ መንግስትክርክር ነው ። በክርክር ውስጥ አሸናፊና ተሸናፊ አለ!! ማለትም የፖለቲካው ጦርነት ያሸነፈው የፖለቲካው ክርክርንም ያሸንፋል ማለት ነው!!
Last edited by Horus on 27 Oct 2022, 11:50, edited 3 times in total.

Horus
Senior Member+
Posts: 42856
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የደቡብ አፍሪካው ክርክር

Post by Horus » 27 Oct 2022, 11:25

Abe Abraham
Senior Member
Posts: 14414
Joined: 05 Jun 2013, 13:00

Re: የደቡብ አፍሪካው ክርክር ከትህነግ ሳይሆን ካሜሪካ ጋር ነው!

Post by Abe Abraham » 27 Oct 2022, 12:28

Horus wrote:
27 Oct 2022, 01:22
የዛሬ ሶስት ቀን ይህን ብዬ ነበር። ኢትዮጵያ ጦር ሜዳ ላይ እያሸነፈች ከትህነግ ጋር የምታደርገው ድርድር አይደለም ። ድርድር ካለ የሚደረገው ካሜሪካ ጋር ነው፤ ያም ማለት አሜሪካ ጣልቃ መግባቱን እንዲያቆም ማለት ነው ። ይህው ዛሬ የተረጋገጠው ያ ነው። አሜሪካ አደራዳሪ ሳይሆን ተደራዳሪ ነው ተባለ!

ቋንቁና የትግሬ ጉዳይ፤

ቋንቋ ሳይጸዳ ሃሳብ አይጸዳም። ሃሳብ ሳይጸዳ ድርድር አይጸዳም ። ስለዚህ በደቡብ አፍሪካ ምን እየሆነ ነው?

ድርድር? ምንድን ነው የሚደረደረው? ሃሳብ ነው? ብርጭቆ ነው? መጽሃፍ ነው? ስለዚህ በደቡብ አፍሪካ ምንም አይነት ድርድር እየተደረገ አይደለም።

ድልድል? ምንድን ነው የሚታደለው? ምንድን ነው ለዚም ለዛም የሚታደለው? የሚሰጠው? ገንዘብ? መሬት? አስቤዛ? የዝናብ ልብስ? ምናልበት ስልጣን? ስለዚህ በደቡብ አፍሪካ ምንም አይነት ድልድል እየተደረገ አይደለም።

ንግግር? ንገር = ቴል፣ ንግግር =ቴሊንግ። ማነው ለማ የሚነግረው? ምንድን ነው ማ ለማ የሚነግረው? መርዶ፣ ልደት? አደጋ? ናፍቆት? አው በደቡብ አፍሪካ የሆነ ንግግር ሊኖር ይችላል።

ውይይት? ስለ ለምን ነው የሚወያዩት? ውይይት = አውያት = ጩኧት ወይም አቤቱታ ነው ። ወይይት ወይ ወይ ማለት ተማጽኖ ማድረግ ነው ። ማነው ችግሩን በማ ላይ ዋይ ዋይ የሚለው? ስለዚህ በደቡብ አፍሪካ ወይይት የለም።

ሙግት? ሙግት ምንድን ነው? ሙግት ወቱጋገት ማለት ስለአንድ ነገር ማውጣትና ማወረድ፣ ከምክክር የጠነከረ ክርክር ማለት ነው ።

ክርክር? ፖለቲካ አንድም በሰላም አንድም በአመጽ ይካሄዳል ሲባል ይህ ነው ። ሰላማዊ የፖለቲካ ትግል የሚደረገው በክርክር ነው ። አመጻዊ የፖለቲካ ትግል የሚደረገው በጥይት ነው ፣ በዱላ ነው። ስለዚህ በደቡብ አፍሪካ እየተደረገ ያለው ክርክር እንጂ ድርድር አይደለም።

ልውውጥ? ለውውጥ ማለት ኒጎሺዬት ማድረግ ሲሆን ንግድ ላይ አንድ ነገር ለሌላ ነገር መለዋወጥ፣ ላንድ ነገር አንድ ነገር መስጠት ማለት ነው። ሰው ቤት ሲገዛ፣ ሽሮ ሲገዛ፣ ጫማ ሲገዛ የእቃና የዋጋ ልውውጥ ኒጎሺዬሽን ያደርጋል ። ለምሳሌ የትግሬና አማራ ድምበር ከሆነ የልውውጥ ክርክሩ አው በደቡብ አፍሪካ ልውውጥ (ኒጎሺዬሽን) ሊኖር ይችላል። ያ ከሆነ ደሞ ያለው ድርድር ሳይሆን ልውውጥ ነው ።

ዝብብር፣ ዝርርብ፣ ምልልስ የሚባሉት ወሬ መመላለስ ማለት ነው። ማውራት መናገር ( ቱ እስፒክ ) ማለት ነው ። እርግጥ ውል (መስማማት) ከማውራት (አውራር) ይመነጫል ። ስለዚህ ማውራት (ዝርርብ) ከንግግር ጋር ይጠጋል። ነገር ግን ክርክር አይደለም ። ለምሳሌ በሃሳብ የተለያዩ ሰዎች አንድ ላይ አውርተው አንድ ውል ላይ ይደርሳሉ በክርክር ሳይሆን ወሬ በመለዋወጥ ማለት ነው ። ይህ የሚሆነው ስምምነት ሲሆን ነው ።

ስምምነት? ስምምነት ምንድን ነው? ስምምነት አንድ አይነት ሃሳብ፣ አላማና ተግባር መያዝ ማለት ነው ። ስለዚህ በደቡብ አፍሪካ ስምምነት እየተደረገ አይደለም። ትህነግና ኢትዮጵያ አንድ አይነት ሃሳብ፣ አላማን ተግባር የላቸውም ። ለዚህ ነው ጦርነት የሚዋጉት!

በደቡብ አፍሪካ ስምምነት እየተደረገ ነው የሚሉ ሰዎች የስምምንት ትርጉም የማያውቁ ናቸው ።

ስለዚህ በዋናነት የደቡብ አፍሪካው ድራማ ስሙ ድርድር አይደለም ። የትህነግ ድርጅትና የኢትዮጵያ መንግስትክርክር ነው ። በክርክር ውስጥ አሸናፊና ተሸናፊ አለ!! ማለትም የፖለቲካው ጦርነት ያሸነፈው የፖለቲካው ክርክርንም ያሸንፋል ማለት ነው!!
Thanks for you extensive explanation. Indeed ቋንቋ ሳይጸዳ ሃሳብ አይጸዳም።

Post Reply