Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
-
Abere
- Senior Member
- Posts: 15462
- Joined: 18 Jul 2019, 20:52
Post
by Abere » 25 Oct 2022, 16:45
የአደራዳሪዎች ምርጫ ላይ ወያኔ ያሸነፈች ይመስላል። እንድያደራድሩ የፈለገቻቸው አካላት በሙሉ ተካተውበታል። የቅድመ ሁኔታውን ዝርዝር አልሰማንም እንጅ የእርሱም ዕጣ የተለየ ላይሆን ይችላል።
ወያኔ የፈለገቻቸው:-
1)ኡሁሩ ኬንያታ -
2) ተመድ
3) አሜሪካ
ወያኔ የማትፈልገው፥
1) ኦሌሰንጎ ኦባሳንጆ
ብልጽግና-ኦዴፓ የሚፈልግው፥
1) ኦሌሰንጎ ኦባሳንጆ
ሂሳቡን እናንተው ስሩት። (Hint) ኦሌሰንጎ ኦባሳንጆን በኡሁሩ ኬንያታ አጣፉት።
ሌላው ዝርዝሩ ኪስ ይቀዳል ምክንያቱም, the devil is in the detail.
-
Horus
- Senior Member+
- Posts: 42861
- Joined: 19 Oct 2013, 19:34
Post
by Horus » 25 Oct 2022, 21:43
Abere wrote: ↑25 Oct 2022, 16:45
የአደራዳሪዎች ምርጫ ላይ ወያኔ ያሸነፈች ይመስላል። እንድያደራድሩ የፈለገቻቸው አካላት በሙሉ ተካተውበታል። የቅድመ ሁኔታውን ዝርዝር አልሰማንም እንጅ የእርሱም ዕጣ የተለየ ላይሆን ይችላል።
ወያኔ የፈለገቻቸው:-
1)ኡሁሩ ኬንያታ -
2) ተመድ
3) አሜሪካ
ወያኔ የማትፈልገው፥
1) ኦሌሰንጎ ኦባሳንጆ
ብልጽግና-ኦዴፓ የሚፈልግው፥
1) ኦሌሰንጎ ኦባሳንጆ
ሂሳቡን እናንተው ስሩት። (Hint) ኦሌሰንጎ ኦባሳንጆን በኡሁሩ ኬንያታ አጣፉት።
ሌላው ዝርዝሩ ኪስ ይቀዳል ምክንያቱም, the devil is in the detail.
አበረ፣
የኔ ግምት ይለያል ። አንድ ቦታ ላይ የሩቁን ሁሉ ማየት፣ የቅርቡን ሁሉ ማየት ያልኩት ነገር እዚህ ይመጣል። ዙን ጹ የሚባለው የጥንታዊ ቻይና እስትራተጂስት ምን ይል መሰለህ፤ በምስራቅ ሁካታ ፈጥረህ በምዕራብ አጥቃ ይላል።
ዛሬ ላይ ትልቁ የትህነግ መንጠልጠያ ባላ ዲፕሎማሲ ነው ። የአሜሪካና አውሮፓን (ተመድ የነሱ ስራ አሰጻሚ ነው) ዲፖላቲክ ድጋፍ አረጋግጦ ኢትዮጵያን በውጥረት ጠፍንጎ እንደ ገና ማታጠቅ ነው ። ስለዚህ አቢይ ከወዲሁ አሜሪካና ተመድ (ኡሁሩ ያሜሪካ ተላላኪ ነው) ሊካፈሉ አይችሉም ካለ በቀጥታ ፉክቻው ኢትዮጵያና አሜሪካ መሃል ሆነ ማለት ነው ። የትግሬን ጉዳይ ኢተርናሽናላይዝ ማድረግ ማለት ያ ነው ። ወያኔ ድርድር አስመስሎ የዲፕሎማሲ ዉጊያ እያደረገ ነው ።
ልብ በል ኬን ያ ከኢትዮጵያ ስንዴና ኮሬንቲ ትገዛለች፣ ሌላውን አገር ተው ኬንያን እንኳ የምር ማበሳጨር ትቅማችንን ይጎዳል ። ስለሆነም አሜሪካና ተመድ ወላ ኡሁሩ ደቡብ አፍሪካ ይምጡ ። አቢይ ብቁ ሰዎች ካሉት የሚያደርገው ዘዴ የማርሻል አርት መርህ አለ። እሱም ባላንጣህ አንተን ሊመታ ተደርድሮ የሚወረውረውን ጡጫ (ሞሜንተም) ለመመከት ሃይልን ማባከን ሳይሆን የሱን ሞሜንተም ተጠቀም፣ እሱን መግታት ሳይሆን አንተም እሱን ወዳንታ ሳበው፣ ያኔ በራሱ መንደርደር ትጥለዋለህ የሚል ፍቱን የማርሻል አርት ስልት ነው።
ወደኛ ስናመጣው አሌሪካና ተመድ አትምጡ በሚል ካሜሪካ ጋር ሃይል ማባከን ሳይሆን ድርድሩ ውስጥ አስገብተህ ከወያኔ ጋራ እንዲሸነፉ ማድረግ ነው። ይህም ማለት ለምሳሌ በትግሬ ወደፊት የሚጥፋውን ቢሊዮን ወጪ የነሱ ሸክም ማድረግ! አሜሪካ የትግሬ ችግር አካል ለመሆን መርጦ የገባ ሃይል ነው። ስለሆነም የሽክሩ አካል እንደሆኑ ፍሬም አድግሮ በግልጽ የውዝግቡ አካልና ምንጭ ማድረግ ንግግርና ዲፕሎምሲ በሚመለከት ማለት ነው ።
በሪያሊቲ በጦር ሜዳ የሃይል ሚዛን ሙልጭ አድርጎ ማሸነፍ! ከልቤ ነው የምልህ እኔ እዚያ ደቡብ አፍሪካ ቡድን ውስጥ ብሆን ዋና እስትራተጂ አድርጌ ይዤ የምሄደው ስልት ተመድና አሜርካ የችግሩ ምንጭ የሚያደርኛ መፍትሄው እንዲያስከፍላቸው የሚያስገድድ መንገድ ቀይሼ ነበር የምገባው ። ወያኔን በጦር ሜዳ እየመታሁት ስለሆነ እሱን በፍጹም የድርድሩ ትኩረት አላደርገውም ነበር ።
Last edited by
Horus on 25 Oct 2022, 22:18, edited 1 time in total.
-
Abe Abraham
- Senior Member
- Posts: 14414
- Joined: 05 Jun 2013, 13:00
Post
by Abe Abraham » 25 Oct 2022, 21:51
Kenyatta ከመጣ ለምን Afrika Bambaataa ቀረ የሚል ጥያቄ ኣካራከሪ ይሆናል !!!
-
Sam Ebalalehu
- Member
- Posts: 3639
- Joined: 23 Jun 2018, 21:29
Post
by Sam Ebalalehu » 25 Oct 2022, 22:12
ይሀ ምንም ብስለት የተሳነው ርእስ እና ውይይት ነው። የድርድሩ ውጤት በአደራዳሪዎቹ አይደለም የሚወሰነው በተደራዳሪዎቹ ነው። የኢትዮጵያ መንግስት የ ድርድሩን outcome የመፃፍ ሙሉ ቁመና ላይ ነው።
-
Selam/
- Senior Member
- Posts: 17917
- Joined: 04 Aug 2018, 13:15
Post
by Selam/ » 25 Oct 2022, 22:19
It’s the “half empty or half full glass” thing. We have so many folks on ER, who don’t have the courage to ask but make assumptions at every turn.
Sam Ebalalehu wrote: ↑25 Oct 2022, 22:12
ይሀ ምንም ብስለት የተሳነው ርእስ እና ውይይት ነው። የድርድሩ ውጤት በአደራዳሪዎቹ አይደለም የሚወሰነው በተደራዳሪዎቹ ነው። የኢትዮጵያ መንግስት የ ድርድሩን outcome የመፃፍ ሙሉ ቁመና ላይ ነው።
-
Horus
- Senior Member+
- Posts: 42861
- Joined: 19 Oct 2013, 19:34
Post
by Horus » 25 Oct 2022, 22:26
ሳም
አደራዳሪዎች በድርድር ላይ ፋይዳ ከሌላቸው ለምንድን ነው ተደራዳሪዎች ማ ያደራር በሚለው ላይ የሞት ሽረት ትግል የሚያደርጉት! በተለይ እንደ አሜሪካና ተመድ ያሉ የፕሮክሲ ጦርነቱ ባለቤቶች እና ወያኔን አስታጣቂ መጋቢውች ዞረው አስታርቂ ሆነው ሲዳኙ እንዴት ኢንፍሉወንስ የላቸውም ይባላል? አይደለም አሜሪካ ኦባሳንጆና ኡሁሩ አጨቃጫቂ ሆነዋልኮ! ሳም ስላልከው ነገር ያልገባን ካለ ብታብራራው?
-
Sam Ebalalehu
- Member
- Posts: 3639
- Joined: 23 Jun 2018, 21:29
Post
by Sam Ebalalehu » 25 Oct 2022, 22:54
Horus ተደራዳሪዎቹ አደራዳሪዎቹ የድርድሩን ውጤት ይወስናሉ በሚል ግምት አይደለም አደራዳሪ ምርጫ ላይ የሚፏከቱት። ድርድሩ ውጤት እንደዲኖረው unbaised arbiter ሁሉም ወገን ይፈልጋል። ግን unbaised arbiter is open to interpretaion. ፍጭቱ እዛ ላይ ነው። በእኔ ግምት ዛሪ ህወዋትን የኢትዮጵያ ፈላጭ ቆራጭ እንዲሆን -- save Egypt -- የሚፈልግ ሀይል የለም። አሞሞታቸው ግን በጣም አሳዛኝ እንዳይሆን የሚጥሩ አሉ። ልዩነት አለ በሁለቱ መሀል።
-
Horus
- Senior Member+
- Posts: 42861
- Joined: 19 Oct 2013, 19:34
Post
by Horus » 26 Oct 2022, 00:48
ሳም፣
አሜሪካኖች ትህነግ መሞት አለበት፣ ግን አሟሟቱ ያማረ ይሁን ያሉበት ምን ፋክት፣ ምን ማረጋገጫ አለህ?
-
Abere
- Senior Member
- Posts: 15462
- Joined: 18 Jul 2019, 20:52
Post
by Abere » 26 Oct 2022, 09:47
መስማት እና ማዳመጥ የተለያዩ ድርጊቶች እንደ ሆኑ ሁሉ አንተ ዐርዕስቱን ሰማኸው እንጅ ማዳመጥ አልቻልክም። ይህን ያህል እንኳን ረቂቅ አልመሰለኝም ነበር - ለማጤን ግን እንዳስቸገረህ ተረዳሁኝ።
ምስጋና እንደ ምንግዜውም ሁሉ ለወንድም ሆረስ (Horus) ይድረስ በደንብ አድርጎ ያብራራልህ እና ያስረዳህ መለኝ። አዎን እኔ ደግሞ ይህን ልጨምር። አይደለም አደራዳሪዎቹ እንማን ይሁኑ የድርድር ቦታው (ስፍራው) እንኳን ለመወሰን አጨቃጫቂ ነው። ታዲያ እነማን ያደራድሩ የሚለው ባያስቸግር እኮ ቀደም ብለው ነበር ወያኔ እና ብልጽግና ኦነግ ለድርድር የሚቀርቡት።ምንም እንኳን ብልጽግና ኦነግ የጦርነት ብልጫ አለኝ ቢልም አሁን በአደራዳሪዎች አመራራጥ ላይ ወያኔ የምትፈልገው ነው የሆነው።
ስለ ድርድር ትርጓሜ ሆረስ ቀደም ብሎ በሌላ የውይይት አርዕስት ላይ ተንትኖታል። ከዚያ ልትረዳ ትችላለህ። አሁን ብልጽግና-ኦነግ አሸንፌያለሁ ይላል፤ ድርድር ተቀምጫለሁ ይልሃል። ይቃረናሉ። በሽማግሌ ፊት ሲቀረብ አንድ ጥለህ አንድ አንጠልጥለህ የመሄድ ስርዐት ነው። ታዲያ ብልጽግና-ኦነግ ምን ጥሎ ምን አንጠልጥሎ ይመጣል? አደራዳሪዎቹ እስካሁን በዙህ ጦርነት ያሳዩት ባህርይ ወያኔን የመደገፍ ነው። ቀደም ብየ እንደጠቀስኩት ኡሁሩ እና ኦባሳንጆ ወንበር ላይ ተቀመጡ እንጅ የውይይቱ ዲናሞ (engine) አንቀሳቃሽ እና መሪ አይደሉም። For that matter Uhur cancels out Obasnjao, the remaining negotiators are TPLF sympathizers. ስለዚህ ብልጽግና ነጥብ ጥሏል ወይም ቀደም ብሎ ተስማምቷል። ኢትዮጵያ የምትፈልገው ወያኔ የሚባል ድርጅት በህግ እንድ ታገድ እና ከምድረ- ገጽ እንድጥፋ ነው። የደቡብ አፍሪካው ውይይት ወያኔ ተሸንፎ እንኳን እንደ ድርጅት እንድቀጥል ነው። ወያኔ ከመቀሌ ተደምስሶ ቢባረርም ምዕራባዊያን ወያኔ የሚባል ድርጅት እንድጠፋ የሚፈልጉ አይመስልም - ዐብይ አህመድ ወይም ኦነግም ቢሆን ወያኔ የሚባል ድርጅት እንድጠፋ እና እንድደመሰስ በፍጹም አይፈልጉም። ፓርላማ ሽብርተኛ ብሎ የፈረጀውን ነው ሂዶ እጅ ነስቶ ልደራደር የሚለው።
Sam Ebalalehu wrote: ↑25 Oct 2022, 22:12
ይሀ ምንም ብስለት የተሳነው ርእስ እና ውይይት ነው። የድርድሩ ውጤት በአደራዳሪዎቹ አይደለም የሚወሰነው በተደራዳሪዎቹ ነው። የኢትዮጵያ መንግስት የ ድርድሩን outcome የመፃፍ ሙሉ ቁመና ላይ ነው።