Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 42853
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

በጦር ሜዳ እያሸነፈ እያለ ለድርድር የሚጣደፍ በታሪክ የለም!

Post by Horus » 24 Oct 2022, 23:03

አው ቤቱ ቁጭ ብሎ የፖለቲካ ኢንተርቴይንመንት ለሚናፍቀው ይህ ሁሉ አንድ ተከታታይ ሲትኮም እንደ ማየት ነው። አይደለም ፖለቲካ በንግግርም ሆነ በብረት የሚካሄደው በሃይል አማካይነት ነው ። ሁለት ባላንጣዎች እኩል የድርድር ፍላጎት የሚኖራቸው ሁለቱም በሃይል ተመጣጥነው ጽኑ እስቴልሜት ላይ ሲቀረቀሩ ነው እንጂ አንዱ ወገን በየቀኑ እያሸነፈ የነገሮች ሁሉ ሚዛን ወደሱ እየደፋ ለዚህ ቶክሲክ የሆነ ከባንዳዎች ጋር ለሚደረግ ንትርክ ምን ያስቸኩለዋል ። የኢትዮጵያ መንግስት ጦርነቱን በያዘው መልክ እየገፋ፣ ድሉ በበረከተለት ቁጥር የድርድር ዲማንዱን (የዝርርቡ ዋጋ) ከፍ እያረገ ከድሉ ተመጣጣኝ ዋጋ ማስከፈል አለበት ። ያ የጦርነትም የዲፕሎማሲም ህግ ነው ። ደሞስ ደብረጽዮን ደ/አፍሪካ ካልሄደ ለምድን ነው የኢትዮጵያ ም/ጠ/ ሚ የሚሄደው?

ኢትዮጵያ ባለ ሙሉ ስልጣን ዴሊጌሽን መላክ አለመፈለጉ የሚያሳየን አንድ ቁልፍ ነገር አለ እሱም ሜዳ ያለው ጦርነት እስከሚያበቃ ምንም አይነት ፋይዳ ያለው ስምምነት ውስጥ መግባት አትፈልግም ኢትዮጵያ ! ለምሳሌ ትህነግ ከዚህ በኋላ ማንኛውም አይነት የጎሬላ ዉጊያ ሆነ አሸባሪ ዉጊያ ላለማድረግ ሙሉ በሙሉ ሳይስማማ የምር ድርድር አይኖርም ። የሚኖረው ለነአሜርካና ተመድ የሚወረወ ቁራጭ ጥሬ ስጋ ነው፣ ያም በዝቅተኛ ዴሊጌሽን (ምንም መወሰን በማይችል ቡድን የተራዘመ አቺ ቢቺ ቺ ቺት ቻት) እያደረጉ ጦርነቱ አንድ አመርቂ ሎጂካል ፍጻሜ እንዲደርስ ነው የሚሆነው ።

ምንድን ነው የድርድር ችኮላው? ማነው ይህን ድርድር ዛሬ የሚፈልገው? አሜርካና የወያኔ ሌቦች ናቸው ። የቀረው ሕዝብ የትግሬ ችግር ከስሩ እንዲፈታ እንጂ የብልጽግናና ትህነግ ተከታታይ ድራማ አይፈልግም ። በዚህ ድርድር ውስጥ ያለው ግዙፉ ዝሆን ትህነግ ሳይሆን አሜሪካ ነው ። ስለዚህ እንዲያውም ጦርነቱ በደምብ እየተወጋ ኢትዮጵያ ካሜሪካ ጋር ነው ስለአዲስ ያሜሪካ ፖሊሲ ለውጥና ስለተከታታይ ጣልቃ ገብነቷ ድርድር እና ስምምነት ላይ መደረስ ያለበት ።

የትህነግ ጦርነት ያሜሪካና እንግሊዝ ጦርነት ነው! ስለዚህ በኔ እምነት ትንሹ ድርድር ቀስ ብሎ ደቡብ አፍሪካ ይካሄድ፤ ትልቁ ድርድር ኢትዮጵያ አሜሪካ ሌላ ቦታ በምስጢር ያካሂዱት ያም ማለት አሜሪካ የፕሮክሲ ጦርነቷን እንድታቆም ማለት ነው ። አቢይ አህመድ ይህን ኢትዮ አሜሪካ ድርድር ማድረግ የነበረበት የዛሬ አመት ነበር ። ያኔ አሳሳቱት! ዛሬ ሁለተኛ እድል አግኝቷል ያን ስህተት ለማረም ። ትርጉም ያለው ፖለቲካና ዲፕሎማሲ ይህ ነው!!
Last edited by Horus on 25 Oct 2022, 15:36, edited 1 time in total.

Selam/
Senior Member
Posts: 17917
Joined: 04 Aug 2018, 13:15

Re: በጦር ሜዳ እያሸነፈ እያለ ለድርድር የሚጣደፍ በታሪክ የለም!

Post by Selam/ » 24 Oct 2022, 23:14

I want Redwan Hussien to finally flip Getcho the bird.

TGAA
Member+
Posts: 5747
Joined: 07 Apr 2019, 20:34

Re: በጦር ሜዳ እያሸነፈ እያለ ለድርድር የሚጣደፍ በታሪክ የለም!

Post by TGAA » 24 Oct 2022, 23:34

"የቀረው ሕዝብ የትግሬ ችግር ከስሩ እንዲፈታ እንጂ የብልጽግናና ትህነግ ተከታታይ ድራማ አይፈልግም"
አብይ በእውነት አዲስ የተለወጠች ፤ ጠንካራ ኢትዮጵያን ቢፈልግ ኖሮ ይህንን ጦርነት በሙሉ አሸናፊነት ጨርሶ ፤ ለትግራይም ሆነ ለኢትዮጵያ ህዝብ ስቆቃ ምክንያት የሆኑትን ለፍርድ ቢያቀብ ወይም ቢያስወግድ አሜሪካ በአንድ ቀን አቋሟን ትቀይር ነበር ፤ ነገር ግን አብይ ከዚይ ድርድር የሚገባበት ምክንያት ከወያኔ የነገድ ፖለቲካ ህይወቱ እዲቀጥል የፈልገው ነገር ስላለው ነው፤ ወያኔ መደራደሪያ አድርጎ የሚቀርበው እራሱ የቀመረውን ኮንስቲቲውሽን ነው ፤ ያንን ደግሞ ብልጽግና ተሸክሞት የሚዞረው የወያኔ ልብስ ነው ፤ ስለዚህ ወያኔ በዚያ እንካን ቢደራደር አሸናፊ ነው የሚሆነ ፤ እነአብይ በዚያ ላይ ምንም ችግር የለባቸውም እንደውም ሊያጠናክሩት የሚፈልጉት ሲስተም ነው ፤ ጎጠኛ ስርአት ሀብታም እንደሚያረግ ተገንዝበዋል ፤ የአብይ ስልጣን ዋስትና እስካገኝ ድረስ ያለው መቀጠሉን ይፈልጉታል ፤ ስለዚህ የአሜሪካንን ጭነት በር ክፈቶ የሚያስገባው አብይ እና የወያኔ የቄስ ተማሪዎች ናቸው ፤ ጫወታው ፍጹም ሲቀየር አሜሪካ ሁሌም ጫወታዋን ትቀይራለች ፤ የአብይ ሰዎች ናቸው ሆን ብለው ከድል ስር ሽንፈትን ጎትተው የሚያወጡት " አብይ ወጥቶ እንዳለፈው " ለአንድዬ ብዬ ነው " ማለቱ አይቀርም ፡፡ የሚያሳዝነው ግን ከሌልው የኢትዮጵያ አስተዳደር የበለጠ የወያኔ ህይወት መቀጥለ ትግራን ህዝብ ነው የሚያሰቃየው ፡ ጦርነቱም በጭራሽ አይቆምም፡፡

Horus
Senior Member+
Posts: 42853
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: በጦር ሜዳ እያሸነፈ እያለ ለድርድር የሚጣደፍ በታሪክ የለም!

Post by Horus » 25 Oct 2022, 00:07

TGAA
አኔና አንተ ይህን ነገር ደጋግመን ብለነዋል፤ ቀጥታና አጭሩ ወያኔ ማጥፊያው ዲዲቲ ይህን የጎሳ ቂጣ ሰባብሮ ዱቄት ማድረግ ነው። ያኔ ትህነግ ከስሩ ነው ሚነቀለው። ግና ያ ስር ደሞ የአቢይና የኦሮሙማም ስር ነው። ስለዚህ ትህነግ ከስሩ አይነቀልም፣ ቀን ጠብቆ የክክልና የራስ ገዝነት መብቱን ተጠቅሞ እንደ ገና ይነሳል። ዛሬም ቢሆን የዚህ ሕገ መንግስት አለመነካት አንዱ የትህነግ ዲማንድ ይሆናል ። እንዳልከው አቢይም ስለሚፈልገው ይህው ሰላም እንዲኖር የጎሳ ሕገ መንግስት መኖር አለበት ባይለን ምን አለ በል!

ለዚህም ነው ለምሳሌ ከብልጽግና ውጭ ያሉ ያማራ ባለድርሻዎች በድርድሩ ይኑሩበት የምንለው ። ጥሩነቱ ይህው እስካሁን ድረስ ሰው ሁሉ ድርድር ድርድር ያላል እንጂ የድርድሩ ጭብጦች ምን እንደ ሆኑ አንድ ግልጽ የሆነ ጉዳይ የለም። ያ ማለት ደሞ የምር ድርድር እንደሌለ ያሳያል።

Horus
Senior Member+
Posts: 42853
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: በጦር ሜዳ እያሸነፈ እያለ ለድርድር የሚጣደፍ በታሪክ የለም!

Post by Horus » 25 Oct 2022, 14:16

የፖለቲካ አላማ ወይ በንግግር ወይም በጦር ማሳካት ይቻላል ። በንግግር ማግኘት ያልቻልነው፣ በጦር እናገኝ ይሆናል ። ነገር ግን በጦር ያላገኘውን በንግግር ማግኘት አንችልም!
። ይህ ነው የወያኔ ትልቅ ፈተና! በሁለት ግዙፍ እግጅ ግዙፍ ህዝባዊ ማዕበል ጦርነቶች ያላሳካው ድል አሁን በደቡብ አፍሪካ ንግግር ሲያሳካ በፍጹም አይችልም ። የትግሬ ወያኔ ወይ ሽንፈቱን ተቀብሎ ወደ ሚሰደድበት አገር መሄድ፣ አለያም በረሃ ወርዶ ተዋግቶ መሞት ነው! ሌላ አማራጭ የለም !!!
Last edited by Horus on 25 Oct 2022, 14:49, edited 1 time in total.

Abere
Senior Member
Posts: 15459
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: በጦር ሜዳ እያሸነፈ እያለ ለድርድር የሚጣደፍ በታሪክ የለም!

Post by Abere » 25 Oct 2022, 14:41

ሆረስ፤

የሚስጥሩ ያልከው ነው። እረጭ እረጩ ነው እንጅ ትርፍ የሆነው ኢትዮጵያ የጦር ኃይሎች እጃቸው አመድ አፋሽ ነው or victim of their own success.

ከዚህ በፊት 2 ጊዜ ወያኔን አይቀጡ ቅጣት በሳምንት ውስጥ አሳይተው ድል አድርገው - አባረርናቸው በቃ! ተመለስ ተብሎ ቁም! ባለህ በት ትዕዛዝ ተሰጠው። ታዲያ 2 ጊዜ ማን አሸነፈ? ወያኔ ናታ !- የትም ፍጭው ዱቄቱን አምጭው ነው። ትግሬዎች እንደሆኑ ለሰው ህይወት ዋጋ አይሰጡ 900,000 ቢሞትም ገና ጥርግራጊ እርሾ የተረፈ ካለ ፈልገው ድንጋይ ስር ይሸፍታሉ። አሁንም ለ3ኛ ጊዜ አባረርናቸው በቃ! ተመለስ ይባላል። :mrgreen: ይደቡብ አፍሪካው ስብሰባ ወያኔ እንደት በአሸናፊነት እንደሚወጣ ሂሳብ እየተሰራ ነው። በማን አገር ነው ታዲያ አሸናፊ ከተሸናፊ እግር ስር የሚልፈሰፈሰው። የጦር ሃይሉ ሳተና ነው መሪው ግን ልፍስፍስ ነው - ምክንያት አለቻ:: ሰው ያለ አንድ ነገር አያጎነብስም ወይ ዕቃ ሊያነሳ ወይ ፈሱን ሊፈሳ ነው ይላል - በጥሬ አማርኛ ይህን አይነቱን ጉዳይ።

Horus
Senior Member+
Posts: 42853
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: በጦር ሜዳ እያሸነፈ እያለ ለድርድር የሚጣደፍ በታሪክ የለም!

Post by Horus » 25 Oct 2022, 15:03

አበረ፣
ትክክል ነው፤ ጎበዝ ወታደር በጦር ሜዳ ያገኘውን ድል፤ ልፍስፍስ ፖለቲካ በጠረጴዛ ዙሪያ አሳልፎ ይሰጣል። ያን የሚያሳይ ታሪክ አለ ። ዛሬ ትህነጎች ከኢትዮጵያ ተደራዳሪዎች ያን መሰል ፋውል የሚያሰሉ ይመስለኛል ። ምክንያቱም ይህን መሰል ውስብስብ ጉዳይ ላይ ስትደራደር የቅርቡን ሁሉ ማየት፣ የሩቁን ሁሉ ማየት፣ የቅርቡ ሲርቅ ምን እንደ ሚሆን፣ የሩቁ ሲቀርብ ምን እንደ ሚመስል ፤ ጌም ቲኦሪ የሚባለው አስቸጋሪ ስሌትን ማወቅ ይፈልጋል። ወደፊት ምን እንደ ሚሆን ዝርዝር ኮዛሊቲ በዝርዝር ማወቅ ከባድ ቢሆንም ኒጎሺዬሽን ሳይንስ ነው፣ እሱን ብቻ የሚያጠኑና መሪዎችን የሚመክሩ አሉ ። እስቲ ለማንኝውም ያቢይ ጌም ቲኦሪስቶች እነማን እንደ ሆኑ የምናየው ይሆናል ። ወያኔዎቹ በጣም የሰለጠኑበት ነው ። ከጎሬላነት ጀምሮ ትምህርታቸው ያ ብቻ ነው ። ትንሽ ሆኖ ትልቅ ሃይል ማሸነፍ፣ ተሸንፎም አሸናፊ መሆን ወዘተ የመሳሰሉት ብልሃቶችን ሲያሰሉ ነው የኖሩት!

የመጀምሪያው ዙር ንግግር 6 ቀን ይወስዳል ተባለ ። የአሜሪካ ቁጥር 1 የድርድር ነጥብ ተኩስ ማቆም ነው ፣ የኢትዮጵያው ደሞ መሆን ያለበት የትህነግ ብረት ማውረድ ነው ። እነዚህ እንደ ሰማይና ምድር የተራራቁ ናቸው ። ስለዚህ ይህ ድርድር አይደለም 6 ቀን 6 ሳምንታት ሊቀጥል ይችላል ።ያ ለኢትዮጵያ ጦር በቂ ግዜ ይመስለኛል።

ኢትዮጵያ ሙሉ ጦርነት እያካሄደች ወያኔ ድርድር መቀመጡ አንድ የሽንፈቱ ምልክት ነው ። አሁን ኢትዮጵያ በችኮላ ምንም ኮንሴሽን አለመስጠት ነው ያለባት!

Horus
Senior Member+
Posts: 42853
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: በጦር ሜዳ እያሸነፈ እያለ ለድርድር የሚጣደፍ በታሪክ የለም!

Post by Horus » 25 Oct 2022, 15:33

የመቀሌ ኤየርፖርት በጥምር ጦር ከተያዘ በኋላ መባል ያለበት የወጣ አይገባም ነው ወይስ የገባ አይወጣም? !!!

Abere
Senior Member
Posts: 15459
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: በጦር ሜዳ እያሸነፈ እያለ ለድርድር የሚጣደፍ በታሪክ የለም!

Post by Abere » 25 Oct 2022, 15:47

ሆረስ፤
You nailed it! አዎን "ጎሺዬሽን ሳይንስ ነው፣ እሱን ብቻ የሚያጠኑና መሪዎችን የሚመክሩ አሉ".

___ከዚህ ላይ ነው ልዩነቱ። ወያኔ ጥርሷን የሰበረችበት ነው ይህን አይነቱን የማፍያ ችሎታ። የመጨረሻ ሌባዎች እና መልቲዎች ናቸው። ባጫ ደበሌ እና መሰሎቹ አንድት የጦር መሳርያ አላስቀረንላቸውም በሙሉ ቀምተናቸዋል የቀረም ካለ አበካሽተነዋል ባለ ሰሞን ነው ከምድር እየቆፈሩ 27 አመት የተዘረፈ የጦር ማሳርያ ከመሬት ታንክ ወዘተ እንደ ጉንዳን እየተግተለተለ ሰሜን ሸዋ ድረስ የዘለቀው አሁንም አረር የሚተፋው።

_____ TPLF's military and political dialogue is engineered by world class foreign strategists and lobbyists - they invested Ethiopian resources against Ethiopia - see what the genocidal Tedros Adhanom is doing. The PP-OLF leadership is only after its narrow interest of what Orommuma is espousing at its core - does not care about the long term and sustainable interest of Ethiopia. It is obvious, the only lasting solution is to defeat TPLF in the battlefield, disarm remnants, and do away its tribal federalism - then Tigray and the rest of the country will have peace. [ deleted ] fox TPLF sitting with all its expatriate strategists vs. amateurish ethno-centric is like a wrestling between fox and lamb.

Horus
Senior Member+
Posts: 42853
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: በጦር ሜዳ እያሸነፈ እያለ ለድርድር የሚጣደፍ በታሪክ የለም!

Post by Horus » 25 Oct 2022, 16:03

Abere wrote:
25 Oct 2022, 15:47

"TPLF's military and political dialogue is engineered by world class foreign strategists and lobbyists - they invested Ethiopian resources against Ethiopia" እጅግ ትክክል!

ጦርነቱኮ ያሜሪካና ያውሮፓ ጦርነት ነው! ምን እሱ ብቻ! አሜሪካ ከቻይናና ሩሲያ የሚያደርገው ጦርነት ነው! TPLF is only the face of the war. ሁላችን እናውቀው የለም እንዴ? ለዚህም ነውኮ አቢይ እኛን በኢትዮጵያዊ አርበኘት ሆስቴጅ ይዞ ባሜሪካ ሲሸነፍ ሰልፍ ይጠራናል፣ አሜሪካ ጋብ ሲብ ብልጽግና ይቀዝንብናል! ሆስቴጅ የተያዘው የትግሬ ሕዝብ ብቻ እንዳይመስልህ፤ እኛም ያቢይና ብልጽግና ሆስቴጅ ነን!

Selam/
Senior Member
Posts: 17917
Joined: 04 Aug 2018, 13:15

Re: በጦር ሜዳ እያሸነፈ እያለ ለድርድር የሚጣደፍ በታሪክ የለም!

Post by Selam/ » 25 Oct 2022, 17:15

Ethiopia should demand that Woyanes pay billions in indemnities and surrender immediately.
Horus wrote:
25 Oct 2022, 15:03
አበረ፣
ትክክል ነው፤ ጎበዝ ወታደር በጦር ሜዳ ያገኘውን ድል፤ ልፍስፍስ ፖለቲካ በጠረጴዛ ዙሪያ አሳልፎ ይሰጣል። ያን የሚያሳይ ታሪክ አለ ። ዛሬ ትህነጎች ከኢትዮጵያ ተደራዳሪዎች ያን መሰል ፋውል የሚያሰሉ ይመስለኛል ። ምክንያቱም ይህን መሰል ውስብስብ ጉዳይ ላይ ስትደራደር የቅርቡን ሁሉ ማየት፣ የሩቁን ሁሉ ማየት፣ የቅርቡ ሲርቅ ምን እንደ ሚሆን፣ የሩቁ ሲቀርብ ምን እንደ ሚመስል ፤ ጌም ቲኦሪ የሚባለው አስቸጋሪ ስሌትን ማወቅ ይፈልጋል። ወደፊት ምን እንደ ሚሆን ዝርዝር ኮዛሊቲ በዝርዝር ማወቅ ከባድ ቢሆንም ኒጎሺዬሽን ሳይንስ ነው፣ እሱን ብቻ የሚያጠኑና መሪዎችን የሚመክሩ አሉ ። እስቲ ለማንኝውም ያቢይ ጌም ቲኦሪስቶች እነማን እንደ ሆኑ የምናየው ይሆናል ። ወያኔዎቹ በጣም የሰለጠኑበት ነው ። ከጎሬላነት ጀምሮ ትምህርታቸው ያ ብቻ ነው ። ትንሽ ሆኖ ትልቅ ሃይል ማሸነፍ፣ ተሸንፎም አሸናፊ መሆን ወዘተ የመሳሰሉት ብልሃቶችን ሲያሰሉ ነው የኖሩት!

የመጀምሪያው ዙር ንግግር 6 ቀን ይወስዳል ተባለ ። የአሜሪካ ቁጥር 1 የድርድር ነጥብ ተኩስ ማቆም ነው ፣ የኢትዮጵያው ደሞ መሆን ያለበት የትህነግ ብረት ማውረድ ነው ። እነዚህ እንደ ሰማይና ምድር የተራራቁ ናቸው ። ስለዚህ ይህ ድርድር አይደለም 6 ቀን 6 ሳምንታት ሊቀጥል ይችላል ።ያ ለኢትዮጵያ ጦር በቂ ግዜ ይመስለኛል።

ኢትዮጵያ ሙሉ ጦርነት እያካሄደች ወያኔ ድርድር መቀመጡ አንድ የሽንፈቱ ምልክት ነው ። አሁን ኢትዮጵያ በችኮላ ምንም ኮንሴሽን አለመስጠት ነው ያለባት!

Abere
Senior Member
Posts: 15459
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: በጦር ሜዳ እያሸነፈ እያለ ለድርድር የሚጣደፍ በታሪክ የለም!

Post by Abere » 25 Oct 2022, 17:29

let's assume Ethiopia demands indemnity from Woyane? Where is the money coming from :lol: Ethiopia is being asked to shower Tigray with billions of Birr as it did before worth of 100 billion Birr for 3 months operating budget - which was transferred to the Dedebit TPLF account. This is even priority#1 followed by giving away Humera- Welqait corridor. You are making me laugh.
Selam/ wrote:
25 Oct 2022, 17:15

Post by Selam/ » 25 Oct 2022, 22:22

“ስቀን አናውቅም!”
Abere wrote:
25 Oct 2022, 17:29

DefendTheTruth
Senior Member
Posts: 13256
Joined: 08 Mar 2014, 16:32

Re: በጦር ሜዳ እያሸነፈ እያለ ለድርድር የሚጣደፍ በታሪክ የለም!

Post by DefendTheTruth » 26 Oct 2022, 16:04

Horus wrote:
24 Oct 2022, 23:03
አው ቤቱ ቁጭ ብሎ የፖለቲካ ኢንተርቴይንመንት ለሚናፍቀው ይህ ሁሉ አንድ ተከታታይ ሲትኮም እንደ ማየት ነው። አይደለም ፖለቲካ በንግግርም ሆነ በብረት የሚካሄደው በሃይል አማካይነት ነው ። ሁለት ባላንጣዎች እኩል የድርድር ፍላጎት የሚኖራቸው ሁለቱም በሃይል ተመጣጥነው ጽኑ እስቴልሜት ላይ ሲቀረቀሩ ነው እንጂ አንዱ ወገን በየቀኑ እያሸነፈ የነገሮች ሁሉ ሚዛን ወደሱ እየደፋ ለዚህ ቶክሲክ የሆነ ከባንዳዎች ጋር ለሚደረግ ንትርክ ምን ያስቸኩለዋል ። የኢትዮጵያ መንግስት ጦርነቱን በያዘው መልክ እየገፋ፣ ድሉ በበረከተለት ቁጥር የድርድር ዲማንዱን (የዝርርቡ ዋጋ) ከፍ እያረገ ከድሉ ተመጣጣኝ ዋጋ ማስከፈል አለበት ። ያ የጦርነትም የዲፕሎማሲም ህግ ነው ። ደሞስ ደብረጽዮን ደ/አፍሪካ ካልሄደ ለምድን ነው የኢትዮጵያ ም/ጠ/ ሚ የሚሄደው?

ኢትዮጵያ ባለ ሙሉ ስልጣን ዴሊጌሽን መላክ አለመፈለጉ የሚያሳየን አንድ ቁልፍ ነገር አለ እሱም ሜዳ ያለው ጦርነት እስከሚያበቃ ምንም አይነት ፋይዳ ያለው ስምምነት ውስጥ መግባት አትፈልግም ኢትዮጵያ ! ለምሳሌ ትህነግ ከዚህ በኋላ ማንኛውም አይነት የጎሬላ ዉጊያ ሆነ አሸባሪ ዉጊያ ላለማድረግ ሙሉ በሙሉ ሳይስማማ የምር ድርድር አይኖርም ። የሚኖረው ለነአሜርካና ተመድ የሚወረወ ቁራጭ ጥሬ ስጋ ነው፣ ያም በዝቅተኛ ዴሊጌሽን (ምንም መወሰን በማይችል ቡድን የተራዘመ አቺ ቢቺ ቺ ቺት ቻት) እያደረጉ ጦርነቱ አንድ አመርቂ ሎጂካል ፍጻሜ እንዲደርስ ነው የሚሆነው ።

ምንድን ነው የድርድር ችኮላው? ማነው ይህን ድርድር ዛሬ የሚፈልገው? አሜርካና የወያኔ ሌቦች ናቸው ። የቀረው ሕዝብ የትግሬ ችግር ከስሩ እንዲፈታ እንጂ የብልጽግናና ትህነግ ተከታታይ ድራማ አይፈልግም ። በዚህ ድርድር ውስጥ ያለው ግዙፉ ዝሆን ትህነግ ሳይሆን አሜሪካ ነው ። ስለዚህ እንዲያውም ጦርነቱ በደምብ እየተወጋ ኢትዮጵያ ካሜሪካ ጋር ነው ስለአዲስ ያሜሪካ ፖሊሲ ለውጥና ስለተከታታይ ጣልቃ ገብነቷ ድርድር እና ስምምነት ላይ መደረስ ያለበት ።

የትህነግ ጦርነት ያሜሪካና እንግሊዝ ጦርነት ነው! ስለዚህ በኔ እምነት ትንሹ ድርድር ቀስ ብሎ ደቡብ አፍሪካ ይካሄድ፤ ትልቁ ድርድር ኢትዮጵያ አሜሪካ ሌላ ቦታ በምስጢር ያካሂዱት ያም ማለት አሜሪካ የፕሮክሲ ጦርነቷን እንድታቆም ማለት ነው ። አቢይ አህመድ ይህን ኢትዮ አሜሪካ ድርድር ማድረግ የነበረበት የዛሬ አመት ነበር ። ያኔ አሳሳቱት! ዛሬ ሁለተኛ እድል አግኝቷል ያን ስህተት ለማረም ። ትርጉም ያለው ፖለቲካና ዲፕሎማሲ ይህ ነው!!
ከህዝብ ለህዝብ የሆነ መንግስት የህዝብን ፍላጎት ምንጊዜም መዘንጋት የለበትም። The need of the people will be the overriding goal and the actions and decisions are measured on how the actors take into consideration such an overriding goal, said this politician.

Horus
Senior Member+
Posts: 42853
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: በጦር ሜዳ እያሸነፈ እያለ ለድርድር የሚጣደፍ በታሪክ የለም!

Post by Horus » 27 Oct 2022, 11:42

የዛሬ 3 ቀን ያልኩት ይህን ነበር ...
"ምንድን ነው የድርድር ችኮላው? ማነው ይህን ድርድር ዛሬ የሚፈልገው? አሜርካና የወያኔ ሌቦች ናቸው ። የቀረው ሕዝብ የትግሬ ችግር ከስሩ እንዲፈታ እንጂ የብልጽግናና ትህነግ ተከታታይ ድራማ አይፈልግም ። በዚህ ድርድር ውስጥ ያለው ግዙፉ ዝሆን ትህነግ ሳይሆን አሜሪካ ነው ። ስለዚህ እንዲያውም ጦርነቱ በደምብ እየተወጋ ኢትዮጵያ ካሜሪካ ጋር ነው ስለአዲስ ያሜሪካ ፖሊሲ ለውጥና ስለተከታታይ ጣልቃ ገብነቷ ድርድር እና ስምምነት ላይ መደረስ ያለበት ።

የትህነግ ጦርነት ያሜሪካና እንግሊዝ ጦርነት ነው! ስለዚህ በኔ እምነት ትንሹ ድርድር ቀስ ብሎ ደቡብ አፍሪካ ይካሄድ፤ ትልቁ ድርድር ኢትዮጵያ አሜሪካ ሌላ ቦታ በምስጢር ያካሂዱት ያም ማለት አሜሪካ የፕሮክሲ ጦርነቷን እንድታቆም ማለት ነው ። አቢይ አህመድ ይህን ኢትዮ አሜሪካ ድርድር ማድረግ የነበረበት የዛሬ አመት ነበር ። ያኔ አሳሳቱት! ዛሬ ሁለተኛ እድል አግኝቷል ያን ስህተት ለማረም ። ትርጉም ያለው ፖለቲካና ዲፕሎማሲ ይህ ነው!!"

ይህው ዛሬ ዋናው ተደራዳሪ አሜሪካ ነው ተባለ!

Horus
Senior Member+
Posts: 42853
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: በጦር ሜዳ እያሸነፈ እያለ ለድርድር የሚጣደፍ በታሪክ የለም!

Post by Horus » 27 Oct 2022, 14:39

ቢንጎ!
ደቡብ አፍሪካ ያለው ምንም መወሰን የማይችል ትቅተኛ ል ኡክ ቡድን ነው

https://mereja.com/forum/viewtopic.php?f=2&t=307201

Abere
Senior Member
Posts: 15459
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: በጦር ሜዳ እያሸነፈ እያለ ለድርድር የሚጣደፍ በታሪክ የለም!

Post by Abere » 27 Oct 2022, 15:16

This so-called negotiation is for sure going to be very disappointing for those supporters of PP, in the end. ወያኔ በቅልጥሜ አሸንፋለሁ ብላ የገባችበትን አሁን ስትቀለጠም ውይይት ምን ያስፈልግ ነበር:: የብልጽግና-ኦነግ ነገር በመጨረሻ ህዝብን ኮሶ ማቃም ነው። This will be the third time, you will deal with it. ሴራ እና ፍርሃት ተይዞ እንደት መራመድ ይቻላል? When the right and direct stakeholders wanted to be on the stage, PP-OLF is vehemently got angary at them and its Wutaf-Neqay are smearing personalities. This is a no brainer, the only way to end this war is winning it in the battle and ban the so-called Woyane from the entire land. Ethiopians business should be left to Ethiopians. Why should a sovereign country go through series of flaws and compromise her sovereignty? Just walk away from this so-called fake negotiation and finish it off in the battle filed, do not postpone and nurse problem.

Horus
Senior Member+
Posts: 42853
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: በጦር ሜዳ እያሸነፈ እያለ ለድርድር የሚጣደፍ በታሪክ የለም!

Post by Horus » 27 Oct 2022, 21:45

The Economist ከሆረስ አስተያየት ጋራ ሙሉ በሙሉ ተስማማ ። ኢትዮጵያ የትግሬን ጉዳይ በጦር ሜዳ እየጨረሰች ስለሆነ ለድርድሩ ኬርዳሽ ነች አለ! ትክክል !ደግሞም ጥህነግ ወደ ጎሬላ ጦረነት ይሄዳል አለ ። ትክክል ! ትህነግ ብቻ አይደለም አሜሪካም አውሮፓም ግብጽም ትግሬዎች አንድ ሰው እስቲቀር ፕሮክሲ አላማቸውን እንዲዋጉላቸው ስለሚፈልጉ በፍጹም በግሬ ሰላም እንዲመጣ አይፈልጉም ። በዘመነ ቲክ ቶክ፣ እስማርት ፎን፣ ሳተላይትና ድሮን ትግሬዎች ጎሬላ ጦርነት እንዴት እንደ ሚያሳኩ የሚታይ ይሆናል ። የደ/አፍርካውን 'ድርድር ግ ን እርሱት!

Post Reply