
Natnael Mekonnen
ራሰቸውን የአማራ ተወካይ አድርገው ለድርድር የሾሙ ሰዎች ትዊተር ላይ ዛሬ በነበራቸው ውይይት እነማን ተሳተፉ?
በወያኔ በኩል
አሉላ ሰለሞን
የኦነጓ ፀዳለ ለማና ሌሎችም ተሳትፈዋል!
መንግስትን በመጥላት ሰበብ የወያኔ ወዳጅ ሆነው ያረፉት ራሳቸውን ንፁሃ አማራዎች ብለው የሚጠሩት አካላት ዛሬ ትዊተር ላይ ውይይት ነበራቸው።እነዚህ አካላት ቀደም ብለው የጀመሩትና ከስድስት ወራት በላይ የፈጀ ከተቻለ መንግስት የመገልበጥ፣ ካልሆነም በ Deep stateነት የመቀጠል ራዕይን አንግበው ከትህነግ ሰዎች ጋር ተከተታይ ውይይት እያደረጉ ሰነባብተዋል።የባለፈው የእነ ዶ/ር እሌኒ ገብረመድህን፣ ፕሮፌሰር ኤፍሬም ይስሃቅ ስብሰባ ከከሸፈ በኃላ "የትግሬና አማራን ኢሊት አስታርቆ የኦሮሞን ኢሊት ማስተንፈስ በሚል የተጀመረ ስብስብ ነበር።ስብስቡ በሚስጥር የሚገናኝ እና የተለያዩ አደረጃጀቶች ያሉት ነው።
ስብስቡ የትግሬና አማራ ምክክር በዶ/ር አብይ አመራር ባኮረፉ የአማራ አመራሮች ድጋፍ እና በአብን ከፊል አንጃ የሚመራ ነው።
በኢትዮጵያ ውስጥ የሚፈፀመውን ግድያ ዋና መሰባሰቢያ አጀንዳ ያደረገና ቁስልን እያከከ ብዙሃኑን በዙሪያው ለማሰለፍ የፕሮፖጋንዳ ዘመቻው ላይ ሰፊ እቅድ ይዞ እየሰራ የሚገኝ ነው።በዚህ ዘርፍ በተለይ ዲያስፖራውን ለመስበክ ሞክሯል።
በመንግስት መዋቅር ውስጥ ባሉ አካላት ተባባሪነት ጭምር እየታየ ያለው ጫፍ የወጣ ስግብግብነት ለዚህ ስብስብ ምቹጌ ሆኖለታል። ኦነግ ሸኔ በተጠያቂነት ስጋት ባለባቸው ባኮረፉ የብልፅግና ሰዎች ተባባሪነት ጭምር የሚያደርገው ግድያ በኢትዮጵያ ላይ ከሚታየው ችግር ሁሉ ገዝፎ እንዲታይ አድርጎታል።የፕሮፖጋንዳ ክንፉ ይህንን በደንብ በመጠቀም " ወያኔ በ27 ዓመት ይህንን ያህል ግፍ አልፈፀመም" የሚል የመሰባሰቢያ አጀንዳ እንዲኖር አስችሎታል።
የሆነው ሁኖ የዚህ ሁሉ ዋና ጦስ ወያኔና የእርሱ ግርፍ ኦነግ መሆኑን ጠንከር አድርጎ የሚናገር ከተገኘ "የብልፅግና ፈረስ፣ ተከፋይ ወዘተ" በማለት አጀንዳቸውን ለማስረፅ ብዙ ተጉዘዋል።
ወደ መጨረሻ ግን መንግስት ህግ ማስከበር በሚል የተወሰነውን ኔትወርክ አስጨንግፎባቸዋል።ሆኖም ሙሉ በሙሉ ስላልተነካ ከፊሉ የወያኔን መመታት ተከትሎ በድርድር ስም ብቅ ብሏል። ይህ በድርድር ስም ብቅ ያለው አካል ለወራት ለሌላ ዓላማ ሲሰባሰብ የነበረና አጋጣሚውን ተጠቅሞ ራሱን ለማስተዋወቅ የመጣ የብልጣብልጥ አካሄድ እንጅ የሞኝ አካሄድ ብቻ አይደለም።በፌስቡክ ተፅዕኖ ያላቸው ሰዎች ስብስቡን የሞኝ ስብስብ ቢሉትም የሞኝ ስብስብ ግን አይደለም።
ይህ አይነት ስብስብ ከሶስት ዓመት በፊት ዋሽንግተን ዲሲ ላይ በኢትዮጵያ ውስጥ መንግስት የመገልበጥ እቅድ በሚል ሰነድ ያዘጋጅ እና ተከታታይ ውይይት ያደርግ የነበረ ነው።
እና ይህ ስብስብ ከትናንት መግለጫው ማግስት ዛሬ የትዊተር ውይይት አዘጋጅቶ ነበር።
የውይይቱ አዘጋጅ የሰሜን አሜሪካ የአማራ ማህበር የህዝብ ግንኙነት የነበረው/የሆነው እና ተቋሙን ከጀርባ የሚያሾረው ተመስገን መንግስቱ ነበር።የአማራ ማህበር በሰሜን አሜሪካ በተለይ HR-128 ላይ የሰራው ስራ መልካም ነበር።የብዙ ኢትዮጵያዊ ማህበራት ስብስብን በሰብሳቢነት ይመራው የነበረው አቶ ቴዋድሮስ ትርፌ ነበር።ከHR-128 እና ከወያኔ መውደቅ በኃላ ግን ይህ ስብስብ አጀንዳው በመንግስታዊ ሀይሉና በአገር ቤት ነዋሪው ስለተቀማ እዚህ ግባ የሚባል ስራ አልሰራም።ትኩረቱንም ወደ ሰብአዊ መብትና የፖለቲካ ሎቢ በማድረግ ነው የቆየው።ወያኔን በመጣል ሂደት ውስጥ ከፊት የሚሰለፉትን እነ ኮሎኔል ደመቀን የሚያሳስረውን የአሜሪካ ሴናተሮች ረቂቅ ደግፎ ከወያኔ ጋር ቆሞ ሰንብቷል። እርግጥ ብዙዎቹ ወያኔን ይወዳሉ ማለት አይደለም።ሆኖም የአጀንዳ መገጣጠም ገጥሟቸው መሃል መንገድ ላይ ከወያኔ ጋር ተገናኝተው በወገናቸው ላይ ቀውስ ይዘው ብቅ ብለው ነበርም
በዚህም ያላቆሙት እነዚህ ሰዎች አማርኛ የማይችለውን "በጎንደር ስም ቴዎድሮስ ትርፌን ካመጣንለት ይቀበላል" በሚል ቴዲን ጭራሽ የፊት መስመር ላይ አስቀምጦ ብቅ ብሏል።
ለዚህ ያመቸው ዘንድም የተለያዩ ፕላትፎርሞችን በመጠቀም ውይይት ያደርጋል።ማገር ሚዲያ የሚባል በዋና የተንኮል ተዋናዩ ተመስገን መንግስቱ የሚመራ ዩትዩብ አለው። ዛሬም የትዊተር ውይይት ነበራቸው።በዛሬው ውይይት ላይ ከተሳተፉት ውስጥ፦
ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ
አክቲቪስት መስከረም አበራ
አክቲቪስት በላይ ማናየ እና መሰሎቹ የተመስገን የፊት መስመር ጉዳይ አስፈፃሚዎችና እቅድ አውጭዎች የተገኙ ሲሆን
በወያኔ በኩል
አሉላ ሰለሞን
የኦነጓ ፀዳለ ለማና ሌሎችም በውይይቱ ተሳተፈዋል።
ባለፈው በነበራቸው የዙም ውይይት እነ ፃድቃን ከኢትዮጵያ ገብተው ማብራሪያ ሲሰጡ ነበር።ቴዎድሮስ ትርፌም ፃድቃንን ጥያቄ ሲጠይቅ ነበር። ይህ ስብስብ ድርድሩን እየተጠቀመበት ያለው ራሱን ለማስተዋወቅና ወደፊት ለሚያስበው እቅድ እንጅ ለድርድሩ ብቁ እንዳልሆነ በደንብ ያውቀዋል።