Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Abere
Senior Member
Posts: 15468
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

አማራ ከተመልካችነት ወደ ተሳታፊነት--> የደቡብ አፍሪካው የወያኔ እና ብልጽግና -ኦነግ ቅርጫ የጉዳዩ ያገባኛል ባይ ሳይቀረጥ ቀድሞ ብቅ አለ። ጉልህ ታሪካዊ ተፅ እኖ ያለው AAA ሚና

Post by Abere » 22 Oct 2022, 15:06

አማራ ከተመልካችነት ወደ ተሳታፊነት--> የደቡብ አፍሪካው የወያኔ እና ብልጽግና -ኦነግ ቅርጫ የጉዳዩ ያገባኛል ባይ ሳይቀረጥ ቀድሞ ብቅ አለ። ጉልህ ታሪካዊ ተፅ እኖ ያለው AAA ሚና


የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ከአማራ ወኪል ድርጅቶች ከፍተኛ የቤት ስራ ገጥሞታል። እንደ ጥንቱ የወያኔ፤ኦነግ እና ሻዕብያ የግላጭ ድርድር ሳይሆን አሁን የጉዳዩ ቀጥተኛ ባለቤት የሆነው የአማራ ህዝብ እኔም አለሁበት የሚል ህጋዊ ጥያቄ አቅርቧል። ይህ ጥያቄ ለኦነድ እና ወያኔ ደጋፊዎች የጭንቀት እና የስጋት መርዶ ሲሆን ፤ የአማራ ህዝብ ህጋዊ ጥያቄውን በአግባቡ በማቅረቡ ማንኛውም በወያኔ (የትግሬ ህዝብ ወኪል ነኝ) በሚለው እና በብልጽግና (የኦሮሙ ህዝብ ወኪል ነኝ) በሚለው በሚካሄድ የውይይት ውጤት ዜር እና ህገ-ወጥ ያደርገዋል። ይህም ግጭቱን እድሜ ያስቀጥለዋል - አለመረጋጋት ባህል እና ዕድል ሆኖ ለትግሬ እና ለአማራ ህዝብ ይዘልቃል። ዘላቂ ሰላም ለማምጣት የግደታ የአማራ ህዝብ በወኪሎቹ ከዚህ ውይይት ላይ ሊሳተፍ አስገዳጅ ነው።

በመጨረሻ ይህን ያህል ትግል እና ቁጥጠኝነት እና መስዋዕትነት በመክፈል የአማራ ህዝብ ወኪሎች ሁነው ለአፍሪካ አንድነት አደራዳሪ ቡድን ጥያቄያቸውን በህጋዊ መንገድ ላቀረቡ ወንድሞች ከፍያለ ምስጋና ይድረሳችሁ። ታሪካዊ አስተዋጽ ኦ ማድረጋችሁ የሚመሰገን ነው።

You built a road block against the injustices pretreated Amhara people. Congrats and God bless you.

Abere
Senior Member
Posts: 15468
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: አማራ ከተመልካችነት ወደ ተሳታፊነት--> የደቡብ አፍሪካው የወያኔ እና ብልጽግና -ኦነግ ቅርጫ የጉዳዩ ያገባኛል ባይ ሳይቀረጥ ቀድሞ ብቅ አለ። ጉልህ ታሪካዊ ተፅ እኖ ያለው AAA ሚና

Post by Abere » 22 Oct 2022, 20:47

የአማራ ጥያቄ አሁን በሚገባ ቅርጽ ብቻ ሳይሆን በአለም ዐቀፍ አካላት እና በህግ ፊት የዝሆን ያህል ገዝፎ ለመቅረብ ችሏል። በደቡብ አፍሪካ አማራ እራሱን ወክሎ ለመቅረብ ያቀረበው ጥያቄ አፍሪካ ዩንዬን ሊያልፈው የማይችል ለመተው ቢችልም አጠቃላይ ሂደቱን ይሁን ውጤቱ ህገ-ወጥ እና የማይጸና ያደርገዋል። አለባብሰው ቢያርሱ በአረም ይመለሱ እንዳይሆን ከወድሁ አማራ እራሱን ወክሎ የመቅረብ ጥያቄው የግደታ ተቀባይነት ያስፈለገዋል። ከዚህ ውጭ የወያኔ እና የብልጽግና-ኦነግ ቅርጫ ለአማራ ከውጫሌ ውል ለይቶ አያየውም። officially and practically, the AU effort to negotiate TPLF and PP-OLF has already hit a snag.


Abere
Senior Member
Posts: 15468
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: አማራ ከተመልካችነት ወደ ተሳታፊነት--> የደቡብ አፍሪካው የወያኔ እና ብልጽግና -ኦነግ ቅርጫ የጉዳዩ ያገባኛል ባይ ሳይቀረጥ ቀድሞ ብቅ አለ። ጉልህ ታሪካዊ ተፅ እኖ ያለው AAA ሚና

Post by Abere » 23 Oct 2022, 12:19

Axumኪሳራ,

አሁንስ ቅዠትሽ ሰከን አላለልሽም? አክሱም በአማራ ፋኖዎች እጅ እየተጠበቀ ነው። እንኳን ደስ ያለን!ቀደም ብየ ጦርነቱ ሲጀምር እንዳልኩት ይህ ጦርነት በአማራ እና በወያኔ-ትግሬ መካከል የሚደረግ እንጅ አንድም ከብልጽግና ጋር የሚያገናኘው ነገር የለም። ወያኔ ከአዲስ አበባ ተባራ መቀሌ እንድትደበቅ ያደረጋትም የ 27 አመታት የአማራ ህዝብ የማያቋርጥ ትግል ነው - ወልድያ፥ ጎንደር እና ባህር ዳር የወያኔን ሃሞት ያፈሰሰ ነው። ወያኔ ተስፋ የቆረጠው ወልድያ እና ራያ ሲገርፈው ነው - ከዚያ በኋላ የወደቀ ዛፍ ግንድ ይበዛበታል እንድሉ የአዲስ አበባ ዙሪያ ወጣቶች የባህር ዛፍ ሽመል ይዘው ዳውን ዳውን :mrgreen: ብለው ሸኙት። ታዲያ በዚህ የረጅም ትግል ወቅት ያሳለፈው አማራን ማን ይወክለው?


Axumezana wrote:
22 Oct 2022, 22:23
Isaias boy,

ሳይጠሩ፥ አብዬት፥ ሳይላኩ፥ ወዴት፥

ሻእብያም፥ በአማራ፥ እንደተወከለ፥ሰምተናል።



Post Reply