Yes, I love it! This is ድፊት exactly! እጅ ማስገቢያው ቀዳዳ አይታየኝም። ይህ በሳጤራ በደምብ የተሰራ ነው ። እኛ በጨፈቃና ሃረግ በቁጥቋጦ እዚያው እንሰራዋለን ።

ደሞ አንድ የትግሬ ተወላጅ ሽሬ አትበሉ ስሙ ሽረ ነው ያለው ስህተት ነው ። ትክክለኛው ቃል ሽሬ ነው። እሱም ሺር የሚለው ግስ ቅጽል ሲሆን ነው ሽሬ የሚባለው ። ትርጉሙን ከጦርነቱ በኋላ እነግራችኋለሁ
ወፎቹ ግን እነዚህ የሚበሉ ቆቅ (ቆቆች) ሳይህኑ እነዚህ እርግብ ናቸው ። እርግቦች እንኳንስ ሊበሉ እነሱን መምታት ሁሉ እጅግ ክልክል ነው ። ቡላል ይባላሉ በጉራጌኛ ። ጎጆአቸውን ማበላሸት እንቁላላቸውን መንካት ሁሉ ክልክል ነው እኛ ስናድግ ማለት ነው ። ቆቅ ማደን ግን አንድ እረኛ ልክ ጅራፍ የመትኮስ እና ፈረስ የመጋለብን ያህል የረኛ ችሎታ ነው ።