Finfinne Press
6 h
·
"ሰንደቅ አላማችን ሉአላዊነታችን".. 15ተኛው የሰንደቅ አላማ ቀን መፈክር ነው
አይናፋሩ ፓርላማው ስለ ኢትዮጵያ ከተነጋገረው በላይ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአውሮፓ ህብረት ስለ ኢትዮጵያ ተወያይተዋል ...
የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ከሚንቀሳቀሰው የትግራይ ድንበር በላይ የሻዕቢያ ጦር የኢትዮጵያን ድንበር አቋርጦ ተንፈላሷል። ለዛውም በጦርነት ሂደት .. ህዝብን እየገደለ ከተማ እያወደመ ..
ሱዳን ቡና መጠጣት ሲያምራት ደግሞ የኢትዮጵያን 50 ኪሎሜትር ድንበር አቋርጣ በያዘችው መሬት ነው ረከቦት የምታስቀምጠው ... በዚህ ሁሉ ችግሮች "ሰንደቅ አላማችን ሉአላዊነታችን" .. ተብሎ ማሲንቆ ይገዘገዛል።
የሻዕቢያ ወረራ በፈቃደኝነት የተደረገ ቅኝ ግዛት ስለሆነ ሉአላዊነታችን አልተጣሰም እያሉን ነው .. በዚሁ አፋቸው የተባበሩት የአለም መንግስታት ድርጅት በኢትዮጵያ ጦርነት ጉዳይ ስለተወያየ ብቻ .."ሉአላዊነታችን አትድፈሩ".. ብለው ይጮሃሉ
በጦርነት ጭምር ሉአላዊነት የተዳፈረው ሻዕቢያ ተሞግሶ .. ኢትዮጵያ በፈረመች አለምአቀፍ የስምምነት ቻርተር መሰረት የሚወያየው ተመድ ሉአላዊነት ተዳፈረ ተብሎ ይወቀሳል።
የሉአላዊነት ድንበር ፣ የሰንደቅዓላማ ክብር ፣ የህዝብ የሀገር ክብር ብልፅግና ፓርቲ ለክቶ በፕሮፖጋንዳ የሚግተው ጉዳይ አይደለም። ህወሓት ወይም ሌሎች ፓርቲዎች የሚፈጥሩት አዲስ ነገር አይደለም።
የሉአላዊነት ድንበር የሰንድቅ አላማ ክብርን ብልፅግና ፓርቲ ለሻዕቢያ ስለፈቀደ ባንዳነቱን አይፍቀውም። ሀገር አሳልፎ መሸጡን አይቀይረውም። የፈፀመውን የታሪክ ጠባሳም አይሽረውም።
የሉአላዊነት ድንበር የህዝቦች ክብር ፣ የሀገራችን መሰረት ፣ የህልውናችን ልኬት ... በደም በመስዕዋትነት የምንጠብቀው የእኛነት አስኳል ነው።
ይህ የመስዕዋትነት ድንበር ፈርሶ ፣ የህዝባችን ክብር ተዋርዶ .. ሰንደቅዓላማችን ረክሶ .. የባንዲራ ቀን ሳይሆን የባንዳነት ቀን ነበር ማክበር የነበረብን።
ሉአላዊነት ማለት ጊዜያዊ የፖለቲካ ጉዳይ ሳይሆን በአንድ ሀገር ውስጥ የሚኖሩ ህዝቦች የዘመናት የማንነታቸው ፣ የህልውናቸው ፣ የታሪካቸው ፣ የትስስራቸው ፣
የጥቅማቸው ፣ የኢኮኖሚያቸው ፣ የክብራቸው ፣ የመገኛቸው .. ከታሪክ ታሪክ ከዘመን ዘመናት የሚተላለፍ የአብሮነታቸው መገለጫ ነው።
ይህ መገለጫ ለጊዜያዊ ፍላጎት ሆነ ለፖለቲካ ጥቅም አንድ ጊዜ ከተጣሰ በኃላ ... ሉአላዊነት ብሎ ማሲንቆ መገዝገዝ ድንበር አልባነት ነው !!
Please wait, video is loading...