Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 42875
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

TGAA - ያልከው ደረሰ ( ፈተና ጥለው ወጡ)

Post by Horus » 11 Oct 2022, 13:23

ትላንት ይህን ብለህ ነበር ...

"However, you've got to expect an uproar when the exam result comes back in from those who hoped to wear a graduation gown to pretend their position in the government is earned rather than ethnically stamped."

ትላንት ይህን ብዬህ ነበር ...

"ጦርነትና ሁከት አካባቢ ያሉ ተማሪዎች ሲወድቁ ጭቅጭቅ ማስነሳታቸው የሚጠበቅ ነው። አንዳንድ ብሄረሰቦችና ጎሳዎች ከርቀትም ከት/ቤቱ ድክመትም የተነሳ ተማሪዎቻቸው ከትላልቅ ከተማ፣ ከህብታም ቤተሰብ እና ከተማረ ቤተሰብ ከሚመጡ ተማሪዎች ጋር እኩል ውጤት ሳያመጡ ሲቀሩ ጭቅጭቅ መነሳቱ አይቀርም ። ለምሳሌ ወጣቱ በጣም ፖለቲካል በሆነበት አማራአን ኦሮሞ የሚመጡ ተማሪዎች ብዙ ወዳቂ ቢኖራቸው ጭቅጭቅ መነሳቱ አይቀሬ ነው።

ግ ን ለዚህ የተማሪ ትግጅት አለመኖር ምክኛት የሆኑትን ነገሮች ማረም እንጂ ወለጋ አመጽ ስላለ የወለጋ ተማሪዎች በትንሽ ውጤት ኮሌጅ ይግቡ የሚል ሎጂክ አይኖርም! ደግሞ ካመት በኋላ ደግሞ መፈተን የመሳሰሉ ማረሚያዎች ማድረግ ያስፈላል ።"

ይህን ስማ

TGAA
Member+
Posts: 5747
Joined: 07 Apr 2019, 20:34

Re: TGAA - ያልከው ደረሰ ( ፈተና ጥለው ወጡ)

Post by TGAA » 11 Oct 2022, 21:42

በደርግ ግዜ ዩኒቨርሲቲ መግቢያው በሜሪት ላይ የተመሰረተ ቢሆንም የአዲስ አባባ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ መግብያ ነጥቡ ከክፍለ ሀገር ከሚመጡ ተማሪዎች ከፍ ያለ ነበር ፤ ዋናው ምክንያትም ከተማ የሚማሩ ተማሪዎች የተሻለ የትምህርት አቅርቦት አላቸው በሚል ምክንያት ነበር ፤ በወቅቱ ይህ አቀራረብ ፍትሀዊ ነው የሚል አስተሳሰብ ነበረኝ ፤ ወያኔ ከመጣ ግን ከዩኒቨርሲት ፊልድ እዳላ ጀምሮ እሰከ ሁለተኛ ደረጃ መልቀቅያ ፈተና ጨምሮ ፤ ይሰረቃል ፤ወይ አስተማሪዎች እንዲያሳልፉ ይገዳዳሉ ፤ የተማሪ ግምገማ በሚል ፈልጥ አስተማሪዎችን ተማሪዎች እንዲቆጣጠሩ ተደርጓል፤ እርግጥ መንግስት በጦርነት ምክንያት ትምርህታቸው ለተጓጎለ ተማሪዎች ትምህርታቸውን እንደገና ደግመው የሚማሩበትና ፈተናውን የሚወስዱበትን መንገድ ማመቻችትና ሁለተኛ እደል መስጠት አለበት ፤ ነገሩ ግን የማለፍያ ነጥብ ማደል ፤ ተማሪዎቹንም ይሁን ሀገሪቱን አይጠቅምም፤ መረዳት ግን አለባቸው ፤ ዋናው ነጥብ ግን ፖለቲካውን ትምህርቱ ተነጣጥለው መሄድ አለባቸው ያንን ነው ብርሀኑ እያደረገ ያለው በጣም መበረታታ ያለበት ነው ፤ ፈተናውን ረግጠው ወጡ የተባሉት ተማሪዎች ቢፈተኑም ረግጠው ከወጡበት የተለየ ነጥብ ማምጣት እንደማይችሉ ስለሚያውቁ ነው ፤

Post Reply