የጎጎት ጉርዳ ቃል ኪዳን አይጣስም! ጉራጌ ክልል ነው!
ጎጌቲ፣ የጎጎት ቃል ኪዳን የተፈጸመበት፣ ታላቁ ጀግና ደስታ ድምጠው ጣሊያን የተፋለመበት የመስቃን ከተማ !! የኬር መስቀል ይሁንልን! የጉራጌ ወጣት ተደራጅ!! በጥንታዊ ጉራጌ ባህል አንድ ሕግ፣ ስምምነት ወይም አዋጅ ለዚያ ውሳኔ ያገር ሸንጎ በተደረገበት ቦታ ይሰየም ነበር ። ለምሳሌ የሰባት ቤት ቅጫ ሴራ ዬጆካ ሴራ ይባላል ። ዬጆካ የቦታ ስም ነው ። በክስታኔ የጎርጢ ሴራ፣ የእንጀሪ ሴራ ወዘተ ይባላሉ ። የጎጎት ስምምነትም እንዲሁ ! የሰው ስም በተመለከተ አባት በመጀመሪያ ልጁ ስም ለምሳሌ የልጁ ስም ሲማ ከሆነ አባቱ አባሲማ ይባል ነበር። ልጁ ደሞ ባባቱ ስም የሲማ አርዴ (ሴት ከሆነች የሲማ አርደት) ትባል ነበር ። ለምሳሌ የምሁር ተወላጇ ጀ ግ ና የቃቄ ወርድወት (የቃቄ አርደት) ትባል ነበር ። ቃቄ ያባቷ ስም ነው። እሷ የቃቄ ልጅ ትባላላለች ማለት ነው ። አሁን ያ ሁሉ ተረስቷል! አርዴ/አርደት ግዕዝ ሲሆን ወልድ፣ ልጅ ማለት ነው! ወልዴ ማለት አልዴ፣ አርዴ ማለት ነው።
Last edited by Horus on 21 Sep 2022, 14:49, edited 1 time in total.