Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 42893
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

የጉራጌ ቤት አርኪቴክቸር !!

Post by Horus » 20 Sep 2022, 14:15

በአማካይ የጉራጌ ቤት 100 አመት እንዲቆም ነው የሚሰራው! መሃል የቆመው ተሸካሚ ፒላር 'ችባን' ይባላል ። በታላቅ አያት ይመሰላል ። የቤተሰቡ ጽናት ምልክት ነው ። የደመራ ችቦ በችባን ላይ ሶስት ግዜ ወግቶ ነው አባት እሳት ወደ ደመራ የሚያወጣ! ከችባኑ አናት ያለው ኮን መሰል እስትራክቸር 'ዋጋ' ይባላል ። የቤቱ ሲሊንግ በጢስ እንዳቆሽሽ እልፍኝ ውስጥ እንጀራ መጋገር ምናምን ክልክል ነው ። ውጭ በቆርቆሮ የሚሰራ ሞላሌ የሚባል ማድቤት አለ!