Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
MINILIK SALSAWI
Senior Member
Posts: 11713
Joined: 24 Aug 2012, 12:02
Contact:

Eritrea is deploying its entire army as well as reservists. በ6 ግንባሮች ጦርነት ተከፈብን - Getachew Reda Mourns

Post by MINILIK SALSAWI » 20 Sep 2022, 11:53

"Eritrea is deploying its entire army as well as reservists. Our forces are heroically defending their positions," Getachew Reda, a spokesman for the Tigray People's Liberation Front (TPLF), said on Twitter.

Eritrean Information Minister Yemane Gebremeskel did not immediately respond to requests for comment.

Getachew said Ethiopian troops and special forces from the Amhara region to the south had also joined the offensive.

አቶ ጌታቸው በቲውተር ገፃቸው በ6 ግንባሮች ጦርነት ተከፈብን ሲሉ ጣታቸውን ወደ ኤርትራ ጠቁመዋል።የኤርትራ ጦር ከተከዜ እስከ ኢሮብ ባሉት በማይ ኩህሊ፥ዝባን ገደና፤አዲ አዋላ፤ራማ፤ ፀሮና እና ዛላንበሳ በሙሉ ኃይል ጥቃት ተሰንዝሮብናል ሲሉ አመልክተዋል።

Read Full Article - https://minilik-salsawi.blogspot.com/20 ... my-as.html



=

MINILIK SALSAWI
Senior Member
Posts: 11713
Joined: 24 Aug 2012, 12:02
Contact:

Re: Eritrea is deploying its entire army as well as reservists. በ6 ግንባሮች ጦርነት ተከፈብን - Getachew Reda Mourns

Post by MINILIK SALSAWI » 20 Sep 2022, 15:05

ኤርትራ ወረረችኝ ብለህ ማማረር አትችልም! ጌታቸው ሽፈራው

የአማራና የኤርትራ ፀጥታ ኃይል ወደ ትግራይ አልገባም። ግን....ግን... ግብፅ አሰልጥናህ፣ ሱዳን አግዛህ አንዴ በመተማ፣ ሌላ ጊዜ በበረከት፣ ቆይተህ በቤንሻንጉል የውጭ ቅጥረኛ ሰራዊት ይዘህ እየመጣህ የኢትዮጵያን ሉአላዊነት እየጣስክ ወደ ትግራይ ያልገባችውን ኤርትራን የመውቀስ ሞራል የለህም።

ኧረ ቆይ! ሰተት ብላ ወደ ትግራይ ብትገባስ? በሮኬት ከተማዎቿን የመታኸው ስትጫወት አምልጦህ ነው? ግቢህ ውስጥ ኳስ ስትጫወት ሳታስበው ሌላ ግቢ የገባብህ አደረኸው? በቃ ኤርትራ አምጥታ ልትሰጥህ ስለሆነ አትድከም። ጠብቃት።

በሰነድ ኤርትራን እመታለሁ ብለህ አስቀምጠሃል። ከምዕራባውያኑ ቀብድ በልተህ ኢሳያስን የማወርድላችሁ እኔ ነኝ ብለሃል። አሰብና አስመራን እይዛለሁ ብለሃል። ስትተነኩሳት ከርመሃል።

ደግሞኮ ቀልድህ አይጠገብም! የኢትዮጵያን ሉአላዊ ግዛት ጥሳለች ትላለህ። ጉድ ነው መቸው። የት የምታውቀውን ሉአላዊነት? አንተ ለሱዳን አሳልፈህ የሰጠኸውን? ከውጭ ኃይል ጋር ሆነህ ልትጥሰው የምትሰራበትን? አሁን አንተ ስለ ኢትዮጵያ ሉአላዊነት የመናገር ሞራል አለህ? ሉአላዊነት የሚያስከብር ሰራዊቷን መትተህ? በኢትዮጵያ ስር አልሆንም ብለህ? ኢትዮጵያን እየወረርክ? ገሃነም ገብቸ አፈርሳታለሁ እያልክ?

አንተ የአገው ሸንጎ፣ የአፋር ፌደራሊስት፣ ኦነግ ሸኔ፣ የጉምዝና የቅማንት ታጣቂ ወዘተ ጋር ሆኘ እየታገልኩ ነው ብለህ መግለጫ ትሰጣለህ። በኩራት። አንዳንዶቹን ይዘህ ሌላ ክልል ወርረሃል። የኤርትራም ሆነ የአማራ፣ የአፋርም ሆነ የኦሮሚያ ኃይል ወደ ትግራይ ቢገባስ? አንተ አሸባሪው ተገንጣይ ሰብስበህ ስትመጣ ትክክል፣ አገር የራሷን ክልል ፀጥታ ስታሰማራ ስህተት? አንተ ለምን ክልሎችን ወረርክ ስትባል ህልውናዬን የማስጠብቀው ጠላቶቸ ያሉበት ድረስ ሄጀ በመምታት ነው አላልክም? እነሱ ህልውናቸውን ለማስጠበቅ አንተ ድረስ መጥተው ቢያቀምሱህ ምን ይመስልሃል? እንዴት ነው ያዋጣል?

Post Reply