Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Abere
Senior Member
Posts: 15482
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

ውድ ሆረስ! እንኳን ለአዲሱ አመት በሰላም አደረሰህ!!! የዓመት በዐል ጥያቄ አለችኝ - ከቻልክ አብራራልኝ። እንቁጣጣሽ እና Rosh Hashanah የJew አድስ አመት ለምን በመስከረም ወር

Post by Abere » 11 Sep 2022, 15:25

ውድ ሆረስ! እንኳን ለአዲሱ አመት በሰላም አደረሰህ!!! የዓመት በዐል ጥያቄ አለችኝ - ከቻልክ አብራራልኝ። እንቁጣጣሽ እና Rosh Hashanah የJew አድስ አመት ለምን በመስከረም ወር ሆኑ?

Horus
Senior Member+
Posts: 42893
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ውድ ሆረስ! እንኳን ለአዲሱ አመት በሰላም አደረሰህ!!! የዓመት በዐል ጥያቄ አለችኝ - ከቻልክ አብራራልኝ። እንቁጣጣሽ እና Rosh Hashanah የJew አድስ አመት ለምን በመስከረም

Post by Horus » 11 Sep 2022, 16:59

ውድ ወንድሜ አበረ! ደኧም እንኳም ለአክራሚ በኬር አሰላነኧ! አንተንም እንኳን ለአዲሱ አመት በደህና አደረሰህ!

ኢትዮጵያ ከጁሊየስ ቄሳር (ጁሊያን) የሮማዊያን ዘመን ጠጋ የሚል የዘመን አቆጣጠር ስላላት እንቁጣጣሽ (የእንኩታታ ቀን)፣ የአዲስ አመት መጀመሪያ ቀን መስከረም 1 (ሴፕቴምበር 11) ሆነ እንጂ ይህ የአዲስ አመት ቀን በቅድመ ክርስትና መስከረም 15 (ሴፕቴምበር 25 እስከ 27) ባሉት ቀናት ነበር የሚከበረው ። ይህ ከዘመነ ቀምጥ (ኮፕት/ግብጽ) የነበረ ነው ።

በነገራችን ላይ እንቁጣጣሽ እንኩታታ፣ እንኩ እንኩ ፣ የስጦታ መለዋወጥ ማለት ነው። ከሴቶች እንቁ ጋር የሚያያዝነው ነገር የለም! ያዲስ አመት ስጦጣ የአደይ አበባ ነበር!

ሮሽ ሃ ሻና የአይሁዶች አዲስ አመት ነው። ቀኑም የሚውለው በኢትዮጵያ መስቀል ቀን ነው (መስከረም 15 እስከ 17) ባሉት ቀናት ! ሮሽ ሃ ሻን ማለት የአመት መጀምሪያ ማለት ነው ። ሌላ ስሙ The Festival of Lights ልክ እኛ ደመራና ችቦ በማቃጠል የብርሃን መምጣትን በመስቀል እንደ ምናከብረው ነው።

ጉራጌ ትልቁ መስቀል የሚለው መስከረም 17 ይሁዲዎቹ ዮም ኪፑር (ክቡር ቀን ወይም Holy Day) ይሉታል ። እኛ የቅዱስ ዮሃንስ ቀን (በኦርቶዶክስ) አክራሚ/የኬርማይ የምንለው ነው ። ማይ (ዮም) ቀን ማለት ነው ። ግን ይህ ቀን ዛሬ ላይ መስከረም 1 ነው፣ ከኦርቶዶክስ ክርስትና በተያያዘ ማለት ነው ።

ስለዚህ ባጭሩ ከክርስትና በፊት አዲስ አመት የሚውለው በመስቀል ቀን ነበር! የሚመለከው የብርሃን አምላክ ጸሃይ ስለነበር መስቀል ማለት Sun Rise or Rising Sun ማለት ነው ። የቃላቱ ኢቲሞሎጂ ከፈለግ ሌላ ግዜ በዝርዝር ልነግርህ እችላለሁ። እነዚህ የመስቀል ሕዝቦች የምንላቸው ከኦርቶዶክስን መስቀል (የግማደ መስቀሉ መገኛ) ቀን በተለየ መንገድ የሚያከብሩት ለዘመናት መስቀል የአዲስ አመት እለታቸው ስለነበር ነው ።

ዛሬ ላይ ከርስትናም ባንድ በኩል ፈጣሪ ብርሃን ነው ብሎ እያስተማረ የብርሃን (የጸሃይ) ፈጣሪነት ለመሸፋፈን ሌሎችም ዶግማዎችና ቀኖናዎች ስላለበሱት አዲስ አመት (ዉሃ ሁሉ ጠበል ይሆናል የሚባልበትን ቀን) ቅዱስ ዮሃንስ ብለነዋል። መስቀል የብርሃን መወለጃ መውጫ፣ ያዲስ ወራት መጀመሪያ የነበረው ቀን የግማደ መስቀል መገኛ ቀን ብለነዋል። በነዚህ ምክኛቶች ለምሳሌ ገና የክርስቶስ ልደት ቀን (ንጋት ወይም ጽብሃ ብርሃን ማለት ነው) ሄዶ ካውሮፓዊያን የጥንት ክሪስማስ ጋር እንዲጠጋ ተደርጓል ። በመሰረቱ ግን ገና እራሱ የጸሃይ ልደት ወይም ያዲስ አመት በዓል ነው ።

ታሪኩ ብዙ ስለሆነ አላሰለችህም! ይህ የሕዝባችን ነጻነት፣ የነጻነት መውጫ አመት ይሁንልን !!!
Last edited by Horus on 11 Sep 2022, 17:43, edited 1 time in total.

Horus
Senior Member+
Posts: 42893
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ውድ ሆረስ! እንኳን ለአዲሱ አመት በሰላም አደረሰህ!!! የዓመት በዐል ጥያቄ አለችኝ - ከቻልክ አብራራልኝ። እንቁጣጣሽ እና Rosh Hashanah የJew አድስ አመት ለምን በመስከረም

Post by Horus » 11 Sep 2022, 17:24

አበረር፣
የረሳሁን! ለምን በመስከረም ወር ላልከው፤ በኛ በኩል ግልጽ ነው ። የክረምት (የልማት ወራትማለት ነው) ወራት አልፎ ጸደይ (የጸዳ፣ ብራ የሆነ የአደይ) ወራት እምንጀምርበት ወር መስከረም ነው ። ትርጉም ከላይ እንዳልኩት የጸሃይ መውጫ ወር ማለት ነው ። ጸዳይ ማለት አደይ ማለት ነው ። ጸአዳ ብርሃን ማለት ነው ።

አይሁዶች ከኛ በተለየ የክላይሜት ዞነ እየኖሩ ከኛ ጋር አንድ የሆኑት ይህ የዘመን አቆጣጠር የጥንታዊት ግብጽ ስለሆነ ከዚያ የወሰዱት ነው ። በነገራችን ላይ 12 የኢትዮጵያ ካላንደር ወራት ስሞች ከሞላ ጎደል ሁሉም ኮፕቲክ ናቸው ። ስለዚያ በሌላ ግዜ! ኬር!

Abere
Senior Member
Posts: 15482
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: ውድ ሆረስ! እንኳን ለአዲሱ አመት በሰላም አደረሰህ!!! የዓመት በዐል ጥያቄ አለችኝ - ከቻልክ አብራራልኝ። እንቁጣጣሽ እና Rosh Hashanah የJew አድስ አመት ለምን በመስከረም

Post by Abere » 11 Sep 2022, 18:32

ሆረስ፤

ጥያቄየን በተመለከተ ለሰጠኸኝ ሰፊ ዕውቀት ዐዘል ማብራርያ አመሰግናለሁ። ወርሃ መስከረም የወራቶች ንጉስ ነው። ለዚህ ይመስላል ብዙ ሰዎች መስከረም በሚል ስም የሚጠሩት። ጅኦግራፊይዊ ብቻ ሳይሆን የስነ-ፈለግ እና መለኮትዊ ምስጢር ያዘለ ቁም ነገር።

Horus wrote:
11 Sep 2022, 17:24

Post Reply