Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Fiyameta
Senior Member
Posts: 19939
Joined: 02 Aug 2018, 22:59

ጄኔራል ፃድቃን ለምን አለቀሱ?

Post by Fiyameta » 29 May 2021, 16:32


በኮሎኔልነት ማዕረግ የወያኔ መርሰነሪ ጦርን ሲያገለግል የነበረው የጂማ ተወላጅ የሆነው ኮሎኔል አበበ ገረሱ: ህወሃት በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ እየተፈጸመ ያለውን አረመኔያዊ ጭፍጨፋ: ጭቆና እስርና ሞት አንገፍግፎት ይኼን ዘረኛ የወያኔ አገዛዝ በሕብረት ከትከሻው ላይ አሽቀንጥሮ እንዲጥል የወያኔን መርሰነሪ ጦር ከድቶ ወደ የትጥቅ ትግሉን ከተቀላቀለ በኋላ የሰጠው ቃለ-መጠይቅ ነው።



ኦሮማይ II ...
ማን ያውራ? የነበረ! ……. ማን ያርዳ? የቀበረ!


ፃድቃንና ፆረና



TPLF General Tsadqan Gebre-Tensae providing the general scope of the invasion campaign



"እንደምን አደርክ ኮሎኔል?"

"ሰላም ላንተ ይሁን ጋዜጠኛው።"

"ቀጠሮ በማክበርህ አመሰግናለሁ።"

"ወታደር አይደለሁ መቸስ!"

"... እንግዲህ ወደ ጉዳያችን እንዝለቅ። ጄኔራል ፃድቃንና የፆረና ውጊያን በተመለከተ አጫውትሃለሁ ብለኸን ነበር። ከየት ብንጀምረው ይሻል ይሆን?"

"ከመሃሉ መጀመር ሳይሻል አይቀርም። ያየሁትና የሰማሁት እንደወረደ ላውጋህ። ጸሃፊው አንተ ነህና እንደሚሆን ታደርገዋለህ።"

"መልካም ወንድሜ። አንተ እንደመጣልህ ተናገር። እኔ ያንን ወስጄ ለታሪክ ተረካቢው ትውልድ አደርስልሃለሁ።"



"... ወያኔ ወደ ኤርትራ ጦርነት የገባው 10 ክፍለጦሮች ይዞ ነበር" ሲል ጀመረ። እናም ቀጠለ፦

"... ከዚህ ዉስጥ አንዱ ሜካናይዝድ ክፍለ ጦር ሲሆን፤ አንድ ተጨማሪ ኮማንዶ ብርጌድም ነበር። በ1991 ጦርነቱ ሲጀመርም ይህ የሰራዊት ሃይል በአራት ግንባሮች ነበር ለማጥቃት የተዘጋጀው። ቡሬ፣ ዛላንበሳ፣ ፆረና እና ባድመ ግንባሮች ላይ ማለት ነው።

በ1991 ላይ የተደረገው የመጀመሪያው ዉግያ የተበላሸና በጣም ኣሰቃቂ ነበር። የጦር መኰነን ሆነህ እንደ ባለ ሙያ ስታየው ዉግያው በጥቅሉ የሙያ ብቃት ያልታየበት ኣሳፋሪ ጦርነት ነበር ማለት ይቻላል።

ያ ሁሉ ዜጋ ያለቀበትና ያ ሁሉ የአገር ሃብት የወደመበት ጦርነት ከጦርነት አመራር ችግር መሆኑ በግልጽ እየታወቀ አንድም የጦርነቱ መሪ ተጠያቂ ሳይሆን እንዲሁ መቅረቱ በጣም ያሳዝነኛል። ይልቁን በምርጫ 97 "ቅንጅትን ኣልተዋጋችሁም!"... "የኣመለካከት ችግር ኣለባችሁ!" በሚል ከጦርነቱ በላይ ትኩረት ተሰጥቶ ነበር። ከጄኔራል መኮንን እስከ ተራ ወታደር 20,000 የመገመት መለዮ ለባሽ ያለሃጢኣቱ ታስሮ ተባሮአል። ከሃላፊነት እንዲወገድ ተደርጎአል።

በጃንሆይና በደርግ ዘመን ኤርትራ ላይ ዉጊያ ተደርጎ የተሰዋው ዜጋችን ቁጥር ከ250 ሺህ እስከ 300 ሺህ ይደርሳል። ከዚህ ኣንጻር ወያኔ በአንድ አመት ዉስጥ ኤርትራ ላይ ያስፈጀው የወታደር ቁጥር በጣም አሳፋሪ ነው። ከመከላከያ የሰው ሃይል አስተዳደር ልማት መምሪያ ሰነዶች ያገኘሁት መረጃ እንደሚያሳየው፣ በጠቅላላ በኢትዮ-ኤርትራ ዉግያ 98,700 ወታደር ሲሞትብን፣ 194,300 ቁስለኛ ተረክበናል። ከኦርዲናንስ እዝ ያገኘሁት መረጃ ደግሞ መጀመሪያ ለዉጊያ ከተዘጋጀው ከባድ መሳርያ ⅔ኛው መውደሙን ነግረዉኛል። ይህንን ትርጉም አልባ ጦርነት የመሩት መሪዎች ሰኣረ መኮንን፣ ሳሞራ የኑስ፣ ዮሃንስ ገብረመስቀል፣ ታደሰ ወረደ፣ ኳርተር (አብርሃ ወልደማሪያም)፣ ብርሃነ ነጋሽ፣ የተባሉት ጄኔራሎች ናቸው። የጦርነቱ የማእከላዊ እዝ አባላት ደግሞ መለስ ዜናዊ፣ ስዬ አብርሃ፣ ተወልደ ወልደማርያም፣ ኣለምሰገድ ገብረኣምላክ፣ ተፈራ ዋልዋ፣ ፃድቃን ገብረትንሳኤ እና ክንፈ ገብረመድህን ነበሩ።

የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ሰነድና መረጃ ገና ታሪክ ጸሃፊዎች እጅ አልገባም። ወደፊት ብዙ ኣስገራሚ ታሪኮችን ልንሰማ እንችል ይሆናል። በ1991 የተካሄደውን የመጀመሪያ ዙር ጦርነት እንኳ ብናይ በጣም መሰረታዊ የሆኑ ወታደራዊ ስህተቶች በቀላሉ ማውጣት እንችላለን።

የቡሬ ግንባር ላይ ታደሰ ወረደ ተመደበ።

የተሰጠው ትእዛዝ አሰብን ከያዘ በሁዋላ የቀይ ባህርን ዳርቻዎች እያጠቃ፣ ምፅዋን እንዲቆጣጠርና እዚያው ሆኖ ቀጣዩን ግዳጅ እንዲጠባበቅ ነበር።

ፆረና ላይ አብርሃ ወልደገብርኤል፣ (በቅርብ ፃድቃን እየተከታተለው)፣ ዛላንበሳ ደግሞ ብርሃነ ነጋሽ ነበሩ።

ሁለቱም በየአቅጣጫው አጥቅተው ሰገነይቲ ላይ በመገናኘነት አንድ ግንባር እንዲፈጥሩና በአንድ ኮማንድ ስር በመደራጀት አስመራ እንዲገቡ ታዘዙ።

ባድመ ላይ ሰአረ መኮንንና ዮሃንስ ገብረመስቀል፣ እንዲሁም አበባው ታደሰ (በቅርብ ሳሞራ እየተከታተላቸው) ተሰየሙና ቆላማውን የኤርትራ ክፍል ሙሉ በሙሉ እንዲቆጣጠሩ ተነገራቸው።

ለዚህ እቅድ የአሸዋ ገበታ በየአካባቢው ተዘጋጅቶ ያን መሰረት ያደረገ ሰፋፊ ልምምዶች ተደርገዋል። የጦርነቱ እቅድም በየደረጃው ተነግሮኣል። በእቅዱ ላይ ታዲያ ብዙ ኣከራካሪ ጉዳዮች ተነስተው ነበር። ለምሳሌ አዲግራት ላይ በተዘጋጀው የአሸዋ ገበታ ልምምድ ላይ የ23ኛ ክፍለ ጦር ኣዛዥ የነበረው ኮሎኔል በርሄ ገብረማርያም፥
  • "ኤርትራን የመውረር እቅድ ፖለቲካዊ ኪሳራ አያስከትልብንም ወይ? ሰራዊታችንስ የመዋጋት ፍላጎት እንዴት ይኖረዋል? እንዴትስ ማሳመን ይቻላል? በትክክልስ ዉጊያውን በተባለው መሰረት ማካሄድ እንችላለን ወይ? እቅዱን እንደገና ብታዩት ጥሩ ነው።" የሚል አስተያየትና ጥያቄ አነሳ።

ጄኔራል ፃድቃንና ወዲ መድህን የሰጡት መልስ፣
  • "ሻእቢያን ካላጠፋን እኛ መኖር አንችልም። የሻእቢያ ሃይል ደካማ ነው። የኤርትራ ኢኰኖሚ ጦርነቱን መሸከም አይችልም። በተኩስ ሃይልም የበላይነት አለን። ይህ ዉሳኔም የመንግስት ዉሳኔ በመሆኑ ማንም ሊያደናቅፈው አይችልም!" የሚል ነበር።


በአሸዋ ገበታው ዙሪያ የነበሩት የበታች ኣዛዦች፣ "እቅዱ ሊሳካ አይችልም" የሚል ጥርጣሬ ነበራቸው። አሽዋ ላይ የምናየውን፣ በተግባር መሬት ላይ በትክክል መፈጸም የመቻላችን ጉዳይ ሚዛኑን ያልጠበቀ ነበር። ይህ የጥርጣሬ ጥያቄ በባድመና በቡሬ ግንባሮችም ተነስቶ የነበረ ሲሆን፣ እንደ አዲግራቱ ዉይይት "ዉሳኔው የመንግስት ነው!" በሚል ነበር የተዘለለው።

ጦርነቱ ተካሄደ።

በባድመ ግንባር ነበር የተጀመረው። ማጥቃቱን የጀመሩት ሶስት ክፍለ ጦሮች ከፍተኛ ጉዳት ስለደረሰባቸው፣ 20ኛው ሜካናይዝድ ክፍለ ጦርና አንድ ኰማንዶ ብርጌድ ተጨምሮ፣ ሌሎች ሁለት ክፍለ ጦሮች ታክለው በድጋሚ ተሞከረ። ከፍተኛ ሰብአዊና ማቴሪያላዊ ጉዳት ደርሶብን እቅዱ ሳይፈጸም ቀረ።

በባድመ ውጊያ በእቅዱ መሰረት መሄድ እንዳልተቻለ እየታወቀ፣ በፆረና በኩል ዉጊያው እንዲቀጥል ፃድቃን አዘዘ።

የዉጊያው እቅድ መግለጫ የተሰጠው እንፋራ በተባለ ቦታ ላይ ነበር። ፆረና ላይ ልዩ ዝግጅት ተደርጎ ነበር። 12,000 ያህል የትግራይ ሚሊሺያ፤ ከ5,000 በላይ አግላይ እንዲሁም ስንቅና ጥይት አቀባይ፤ በሺህዎች የሚቆጠሩ አህያና ፈረስም ለዚሁ ጦርነት ተሰልፈው ነበር። ለአንድ ሳምንት ያህል ከፍተኛ የጭንቀት ሙከራ ቢደረግም በዚያች ጠባብና ሙት መሬት የተሰለፈው ያ ሁሉ ንብረት፣ መሳሪያ፣ ሚሊሻና አግላይ፣ አህያና ፈረሶች ሳይቀር አንድ ላይ ረገፉ።



የ20ኛው ግዙፍ ሜካናይዝድ ሃይል እግሪ መከል ላይ አመድ ሆኖ ቀረ። ታንኰቹና ተሽከርካሪዎች በሙሉ አረሩ። ሻእቢያ በቀላሉ ከዛለንበሳ፣ ከአዲኳላና ከማይአይኒ አቅጣጫዎች በተጠመዱ መድፎች ሰራዊታችንን ተቀበለው። ይህ የጀግንነት ጉዳይ አይደለም። የኛ የጦር መሪዎች ወታደራዊ ቴክኒክ ከአለማወቅና ከብቃት ማነስ የመጣ ነበር። ሰራዊታችን እንዳለ ገብቶ ረገፈ። ከዚህ እልቂት የተረፉት ወደ ሁዋላ ሸሽተው ገርሁ ስርናይ እና እንትጮ፣ አድዋ ገቡ። ለአንድ ሳምንት የተሞከረው ዉጊያ በከፍተኛ ኪሳራ ከተደመደመ በሁዋላ የጦርነቱ ኣዛዥ የነበረው ጄኔራል ፃድቃን በወቅቱ ማዘዣ ጣብያ ከነበረችው እንፋራ ላይ ስብሰባ ጠራ።


ፃድቃን ስብሰባዉን ሊጀምር ሲል እንባው ቀድሞት ስቅስቅ ብሎ አለቀሰ። ሁሉም ተሰብሳቢ ተያይዞ መላቀስ ሆነ።

እንፋራ የለቅሶ ቦታ ሆነች።

ፃድቃን በመጨረሻ እንደምንም ራሱን ተቆጣጥሮ ከተረጋጋ በሁዋላ ተሰብሳቢውን ለማረጋጋት ሞከረ። እንዲህ ሲልም ተናገረ፤
  • "እስካሁን ብዙ ጦርነቶች መርቻለሁ። ብዙ ዉጊያዎችን ተዋግቼያለሁ። አይቻለሁ። ሰምቼያለሁ። እንዲህ አይነት መጥፎ ሁኔታ ግን ገጥሞኝ አያውቅም።"




የስብሰባው አላማ የጦርነቱን ሁኔታ ገምግሞ መፍትሄ ለመፈለግ የታሰበ ነበር። በመሆኑም ጦርነቱ ሁለት መሰረታዊ ችግሮች እንዳለበት ተሰብሳቢው ገመገመ።

"ከቦታው አስቸጋሪነት አኳያ የዉጊያ እቅዱ ስህተት ነበር። ቦታው ለመከላከል ለጠላት ምቹ ሲሆን፣ ለወገን ጦር ማጥቃት ምቹ ኣልነበረም። በቂ ዝግጅት አልነበረንም። በቂ የሰው ሃይልና የተኩስ ኣቅም አልነበረንም። በጠላት ላይ የነበረን ግምገማ የተሳሳተ ነበር። ጠላት የመሬቱን አመቺነት ተጠቅሞ ተኩስ እንደፈለገ ማዘዋወር ችሎኣል። ጠላት በቂ የሰው ሃይልና የዉግያ ቁመና ይዞ ነበር" ተባለ።

ወደ ዝርዝር ጉዳይ ሳይገባ፣ ግምገማው በዚሁ ተዘጋ። ይህን መነሻ በማድረግም ሌላ ዉሳኔ ተወሰነ።

"... በዛላንበሳና በቡሬ ተይዞ የነበረው የማጥቃት እቅድ እንዲሰረዝ። የተኩስ አቅምን ለማጠናከር ከአየር ሃይልና ከምድር ሃይል ኰሚቴ ተቋቁሞ በጄኔራል አበበ ተክለሃይማኖት መሪነት መሳርያዎች እንዲገዙ። ከፍተኛ የሰው ሃይል ምልመላ ተደርጎ በስፋት ስልጠና እንዲካሄድ። ይህን የምልመላ ስራ ደግሞ በረከት ስምኦን እንዲመራው። የስልጠና ስራውን አባዱላ እንዲከታተለው። አሁን ያሉን 12 ክፍለጦሮች በአጭር ጊዜ ወደ 30 ክፍለጦሮች እንዲያድጉ። ሰራዊቱ ማገገም እንዲችል በመከላከል ብቻ እንዲቆይ..."

እነዚህ ዉሳኔዎች ከጦርነቱ ማእከላዊ እዝ መወሰናቸውን ፃድቃን እንፋራ ላይ ከክፍለ ጦር በላይ ላለን ኣዛዦች ጠርቶ ዉሳኔዉን ነገረን።

በዚህ መመርያ መሰረት እንድንዘጋጅም ተነገረን።

በዚህ ዉሳኔ መሰረትም ለአንድ አመት ያህል ዝግጅት አደረግን። በ1992 ሚያዝያ ወር ላይም አጠቃላይ የጦርነት እቅድ ወጣ። ፃድቃን፣ ጀቤ እና አባዱላ በመቀሌ ከተማ የምክር ቤት የስብሰባ ኣዳራሽ ሰብስበው እቅዱን ገለጹልን።

  • (የ1992 እቅድ ከ1991 እቅድ የሚለየው ነገር ነበረው። በ1991 ኤርትራን ጠቅልሎ የመያዝ ፍላጎት ነበረ። በ1992 ግን "አቅማችን የፈቀደውን እንዋጋለን" የሚል ሆነ። በ1991 በነበረው እቅድ፣ "ወደ ኤርትራ መሬት ስንገባ የኤርትራን ሃብትና ንብረትን እናወድማለን። ህዝቡም የሻእቢያ ደጋፊ ስለሆነ ልናምነው አይገባም!" የሚል ነበር። በ1992 እቅድ ይህ በግልጽ አልተቀመጠም። "ህዝቡ የሻእቢያ ደጋፊ ስለሆነ ከፍተኛ ጥንቃቄ እናደርጋለን" የሚል አረፍተነገር ግን ነበረበት።)


በ1992 ሚያዝያ መጨረሻ ግንቦት መጀመሪያ ላይ ጦርነቱ በባድመ ግንባር ተጀመረ። በዉጊያው ከፍተኛ ጉዳት ቢደርስብንም እስከ ባረንቱ መዝለቅ ቻልን። ሻእቢያ ሰራዊቱን ይዞ ስልታዊ ማፈግፈግ እያደረገ ስለሆነ፣ የጠላት ኪሳራ አነስተኛ መሆኑን፣ ይልቁን ወደ መግደያ ወረዳ እየሳበን መሆኑን አዛዦች ሃሳባቸውንም ለፃድቃን ያቀርቡ ነበር። በአንጻሩም ወደ ኤርትራ ምድር እየዘለቅን በገባን ቁጥር ከዋና ማዘዣችን እየራቅንና የድርጅት ድጋፍ እያጣን እንሄድ ስለነበር፣ የሚያዋጣን አማራጭ ወደ ሁዋላ መመለስ ሆነ።

ከባድመ ግንባር ዉጊያ በኋላ የባድመ የዉጊያ ችግር ሳይገመገም በችኮላ በራማ፣ በፆረና እና በዛላንበሳ ግንባሮች በተመሳሳይ ጊዜ ማጥቃቱ ተጀመረ።

የነበረው ግምገማ፣
  • "በባድመ ዉጊያውን ቀድመን ስንጀምር ሻእቢያ ብዙ ሃይል ወደ ባድመ ሊያመጣ ስለሚችል ሌሎች ግንባሮች በሰው ሃይልና በመሳርያ አቅም ይሳሳሉ" የሚል ነበር።


እንደታቀደው ግን አልሆነም።

በመሆኑም በእነዚህ ሶስት ግንባሮች በተመሳሳይ ሰአት የተጀመረው ዉጊያ በእቅዱ መሰረት ሳይሳካ ሲቀር ባጭር ጊዜ ዉስጥ ሌላ የዉጊያ እቅድ ተዘጋጀ።

  • "በቡሬ ግንባር አሰብ ከተማን መያዝ ከቻልን የሞራል ግንባታ እናገኝበታለን" የሚል አሳብ መጣ።


አሰብን ለመያዝ ያደፋፈረው ዋናው ምክንያት፤

  • "ጠላት በቡሬ ግንባር እንጠቃለን ብሎ ስለማይገምት በቂ ዝግጅት አይኖረውም። ከጅቡቲ መንግስት ጋር ስለተነጋግርን ሃይላችን በቀላሉ በጅቡቲ መሬት ማስጠጋት ለዉጊያም ምቹ ሁኔታ መፍጠር እንችላለን" የሚል ነበር።


በዚሁ መነሻና ገለጻ ላይ በርካታ ጥያቄዎች ተነስተው ነበር። ለምሳሌ የ36ኛ ክፍለጦር አዛዥ ኮሎኔል መሃመድ ኢሻ፣ የ39ኛ ክፍለጦር አዛዥ ኮሎኔል ወንደሰን ተካ፣ የ14ኛ ክፍለጦር አዛዥ ኮሎኔል ወዲ አባተ ያነሱት ጥያቄ፣
  • "እስካሁን ባደረግናቸው ዉጊያዎች ሁሉ ሻእቢያን ከያዘው ምሽግ እንዲያፈገፍግ አደረግነው እንጂ፣ በእቅዳችን ያስቀመጥነውን ተግባራዊ አላደረግንም። ለዚህም ብዙ ኪሳራ ከፍለንበታል። በኪሳራው ምክንያትም የጦሩ ሞራል መጥፎ ሁኔታ ይገኛል። የቡሬ አየር ጠባይም ሆነ መሬቱ በጣም አስቸጋሪ ነው። በቂ የሎጂስቲክ ዝግጅት የለንም። ድንገተኛ ድል እናገኛለን ብለን ድንገተኛ ሽንፈትም ሊከተል ይችላልና ቢታሰብበት? ስለ ጠላት እስካሁን የተናገራችሁት ሁሉ ልክ አልሆነም። እና አሁንስ ምን ያህል ትክክል ናችሁ?" የሚል ጥያቄ አንስተው ውይይት አደረግን።


በመጨረሻ አሳማኝ ነጥቦች ባይቀርቡም፣ የማይቀየር የመንግስት ዉሳኔ ነው ተብሎ "አሰብን መያዝ!" የሚለው እቅድ ፀደቀና ዉጊያው ተካሄደ። ዉጊያው ለአምስት ተከታታይ ቀናት የተካሄደ ቢሆንም፣ እንዲያዉም ከሌሎች ዉጊያዎች ሁሉ የከፋ ዉጊያ ሆነ። ሻእቢያ በበርካታ ዉጊያዎች የሚጠቀምበትን ወደ መግደያ ቦታ እያስገባ የመምታቱን ስልት ቡሬ ላይም ስለ ደገመው ከፍተኛ እልቂት ተቀብለን አሰብን የመያዙ እቅድ ከሸፈ....



"... የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ሲነሳ ከሁሉም እንቆቅልሽ የሚሆንብኝ የፆረናው ዉጊያ ነው። እንደገለጽኩልህ ከፍተኛ መስዋእትነት ከፍለንበታል። ማነው ተጠያቂው?

በወቅቱ ግን የግድ አንድ አካል ተጠያቂ ማድረግ ስለነበረባቸው፣ አምስት ኦሮሞ መኮንኖች እንዲወነጀሉ ተደርጎአል።
"የዉጊያው እቅድ በኦነግ በኩል ለሻእቢያ አሳልፋችሁ ሰጥታችሁዋል" የሚል ክስ ቀርቦባቸው፤ ኮሎኔል ብራ የተባለች ሴት ጢጣ ካምፕ ዉስጥ ስታስገርፋቸው ሰነበተች።

ኦሮሞ መኮንኖች ድብደባው ሲበረታባቸው፣ "አድርገናል፤ ፈጽመነዋል" ብለው አመኑ።

"ግንኙነታችሁ በማን በኩል ነበር?" ተብለው ሲጠየቁ፣ "አባዱላ" ሲሉ መለሱ።

አባዱላ ግን ወያኔን እንደማይከዳ ይታወቅ ስለነበር ምርመራው እዚያው ላይ ቆመ።

በኮሎኔል ብራ ግርፍያ ከተፈጸመባቸው ከፍተኛ ኦሮሞ መኮንኖች አንዱ በድብደባ የዘርፍሬው የተኮላሸ ሲሆን፤ ሌላው ፓራላይዝድ ሆኖአል። መኮንኖቹ በህይወት ያሉ ሲሆን፤ የወያኔ ስርአት ለሚፈጽመው አሰቃቂ የመብት ጥሰት ህያው ምስክር ሆነው የተፈጸመውን ሁሉ ህግ ፊት የሚገልጹበት እለት ይመጣ ይሆናል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ። እነዚህ ኦሮሞ መኮንኖች ላይ የደረሰው አሰቃቂ ግፍ "በፆረናው እልቂት ማን ይጠየቅ?" የሚለዉን ጥያቄ ከህወሃት ዝሆኖች ሰፈር ለማውጣትና አጀንዳውን ለመዝጋት እንጂ መኮንኖቹ ንጹህ መሆናቸዉን ፃድቃን፣ ስዬ እና መለስ ያውቁ ነበር።

✄✄✄✄✄✄✄✄✄✄✄✄✄✄✄✄✄✄✄✄

".... ጦርነቱ ሲጀመር፡ የወያኔ መሪዎች "ግባ!" "ግባ!" ብለው በአማርኛ ነበር ትእዛዝ ያስተላልፉ የነበሩ። በኋላ ሲሸሹ ግን በትግርኛ "ውጻእ! "ውጻእ! (ትርጉሙ ውጣ! ውጣ!) ብለው የነሱን ቋንቋ ብቻ ለሚሰማ የራሳቸው የትግራይ ሰው እንዲሸሽና እንዲወጣ ኣደረጉ። ሌላው የኢትዮጵያ ወጣት እዛው ለሞት ተዳረገ።"




“……የኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ለጦርነቱ መሪዎች የሐብት ምንጭ ሆኖ ማገልገሉን ማየት ችያለሁ፡፡ በጦርነቱ ሰበብ በተዘረፈ ሐብት የሕወሃት ጄነራሎች ሚሊየነር ሆነዋል፡፡ ፃድቃን፣ ጀቤ፣ ብርሃነ ነጋሽ፣ ገዛኢ አበራ፣ አባዱላ ገመዳ፣ አበባው ታደሰ፣ ባጫ ደበሌ፣ ታደሰ ወረደ፣ ሰዓረ መኮንን፣ እና ሌሎችም ጄነራሎች በአዲስ አበባ በባህርዳርና በመቀሌ ያስገነቡት ቪላና ፎቅ ውበቱ አይንን ያፈዛል፡፡ የቤት እቃዎቻቸው፣ ምንጣፎቹ፣ መብራቶቻቸውና ኮርኒሶቻቸው በውድ ዋጋ ከአውሮፓ እየተጫኑ የመጡ ናቸው፡፡ የመጨረሻውን ቴክኖሎጂ እየተጠቀሙ ለቪላዎቻቸው ማሞቂያና ማቀዝቀዣ ተክለውላቸዋል፡፡ ከዚያ ሁሉ እልቂት በኋላ ጄነራሎቹ በቀጥታ ወደ ሃብት ፉክክር ነው የገቡት፡፡ የሚፈሰው ገንዘብ በጦርነቱ ወቅት የተዘረፈ ነው፡፡ …..”

መፅሀፍ: የደራሲው ማስታወሻ፣ በተስፋዬ ጋዳ ገብረአብ







✄✄✄✄✄✄✄✄✄✄✄✄✄✄✄✄✄✄✄✄

Fiyameta
Senior Member
Posts: 19939
Joined: 02 Aug 2018, 22:59

Re: ጄኔራል ፃድቃን ለምን አለቀሱ?

Post by Fiyameta » 29 May 2021, 16:56

:lol: :lol: :lol: :lol:



Digital Weyane
Member+
Posts: 9837
Joined: 19 Jun 2019, 21:45

Re: ጄኔራል ፃድቃን ለምን አለቀሱ?

Post by Digital Weyane » 29 May 2021, 19:30

ይኖር ይመስለው ነበር ሥልጣኑ ኡንዲህ ጣፍጣ
መድከም መንገዳገድ ኡርጅና ሳይሞጣ
መላጣ ራሱ ሲያብለጨልጭ ፈገግታው ሲያበራ
<<ጁንታ ኡኔ ነኝ ኡኮ ማን አለ ጠንካራ?!>>
ብሎ ሲደነፋ ቆሞ ሲንጠራራ
ቀኑ መሽቶ ነግቶ ይለፈልፋል ከተደበቀበት ተራራ
:roll: :roll:

tarik
Senior Member+
Posts: 36321
Joined: 26 Feb 2016, 13:04

Re: ጄኔራል ፃድቃን ለምን አለቀሱ?

Post by tarik » 29 May 2021, 19:37

Z big question is why is this mozefkkkker coward agame is still alive? why did abiy, bacha , abebe still let these cowards 2 live and also fat boy getachew reda??? What z fkkk is going on with ethiopia's INSA???
:evil: :x
:x

Digital Weyane
Member+
Posts: 9837
Joined: 19 Jun 2019, 21:45

Re: ጄኔራል ፃድቃን ለምን አለቀሱ?

Post by Digital Weyane » 29 May 2021, 20:20

ኻው ጀኔራልነት፣ ኻው ኢተማጆርነት ሹመት፣ ላብ አሸባሪነት። ዋይ ዋይ ዋይ ዋይ :cry: :cry:

Abdisa
Member+
Posts: 6262
Joined: 25 Apr 2010, 19:14

Re: ጄኔራል ፃድቃን ለምን አለቀሱ?

Post by Abdisa » 29 May 2021, 22:55

  • መንግስቱ ሃይለማርያም፣ ሰራዊታችን ሙሰኛ አልነበረም ያለው እውነቱን ነው። ከወያኔ ጋር የምታወዳድረው አይደለም። እዚህ ዘረፋው በግልፅ ነው የሚካሄደው። ነፍጠኛ ስልጣን ላይ በነበረ ጊዜ የጅማን ጫካ የኔ ነው ብሎ ስላመነ አልነካውም። እነዚህ ወያኔ እኮ አጭደውና ፈልጠው ለመሸሽ የመጡ ወሮበሎች ናቸው። ለሰራዊት እለታዊ ካምፕና ለሽሮ መቀቀያ 500 አመት እድሜ ያለውን የቀረሮ ዛፍ ያስቆርጣሉ። አንድ የቀረሮ ዛፍ የአራት የደለቡ በሬዎች ዋጋ ነው። እነሱ ሽሮ ያበስሉበታል።

    አዋሳ ከመግባትህ በፊት ከመንገዱ ግራና ቀኝ የነበረው ዛፍ ትዝ ይልሃል? ዛሬ አንድ ዛፍ ለአይንህ አታይም። ከምርጫ 97 በሁዋላማ ለይቶላቸዋል። ገንዘብ የሚያስገኝ ከሆነ ማነኛውንም ወንጀል ይፈፅማሉ። ዛፉንም መሬቱንም በቁሙ እየቸበቸቡት ነው። የሽሽት ጣቢያ የሚሉት አሜሪካና ትግራይ ናቸው። "ሳትቀደም ቅደም! ዘርፈህ አምልጥ!" ይባባላሉ። በውግያ ወቅት "አንድ እግር በመሬት" የሚባል ነገር አለ። እስከ ኮሎኔል ያሉት ትግሬዎች በአብዛኛው ቤተሰባቸውን ወደ አሜሪካ አሸሽተዋል። በስደት ያሉ የባለስልጣን ቤተሰቦች ዶላር የሚላክላቸው ከሃገር ዉስጥ ነው። ተገላቢጦሽ። ሽመልባ የሚባል የስደተኞች ካምፕ አለ፣ ትግራይ ውስጥ። ትግሬዎቹ፣ ኤርትራውያን ነን እያሉ በብዛት ወደ ውጭ ሃገር ይሄዱበታል።

    ስለ ትውልድ መንደሬ ላጫውትህ።

    ጅማ በአንድ ብር ጠግበህ የምታድርበት ሃገር ነው። ሽልጦና ድንች በልተህ በስሙኒ ጠጅ ጠጥተህ ቤትህ ትገባለህ። ሃገራችን በወራሪዎች መዳፍ ስር የወደቀች ሆኖ ይሰማኛል። ወደ ቴፒ፡ ወደ ሚዛን፡ ሄደህ ታውቃለህ? ሳምንቱን ሙሉ በመኪና ስትዘዋወር ሽፍታ የሚባል አይገጥምህም። የኦሮሚያ ምድር ከደቡብ ህዝቦች ክልል ጋር ይጋጠማል። የወያኔ ሰዎችና አዲስ በቀል ነጋዴዎቻቸው ይህን ሁሉ መሬት ተቆጣጥረው እየዘረፉት ነው። ስብሃት ነጋ "ኩባንያችን ቢሊዬኔር ሆኖአል!" ሲል ተናገረ። መላ ሃገሪቱን በብቸኛነት ተቆጣጥረው እየዘረፉ፣ ቢሊዬኔር መሆን ይነሳቸው እንዴ?

    አሳባቸው ያው ዘርፎ ለመሸሽ ነው። ማምለጥ ግን አይችሉም። ራያ ድረስ የኛ ምድር ነው። የበቀል እሳት ሊለኰስ እንደሚችል ካላሰቡ እነዚህ ሰዎች የዋሆች ናቸው። ዘርፎ ማምለጥ የሚባል ቁማር የለም። በዚህ እስካፍንጫቸው እየዘረፉ፣ መልሰው ደግሞ ፟ሃገሪቱ ድሃ ናት፟ እያሉ ይናገራሉ። ኢትዮጵያ ድሃ ሆና አታውቅም። ድህነት ያለው የመሪዎቻችን አስተሳሰብ ዉስጥ ነው።



    አንድ ጊዜ የሆነውን ላጫውትህ? የሽራሮ ልጆች ከሆኑ ሁለት የህወሃት ከፍተኛ መኮንኖች ጋር ወደ ጅማ እየተጓዝን ነበር። ትግሬዎቹ አከባቢው ገና ማየታቸው ነበር። ኰረሪማና ዝንጅብል፤ ዘይቱንና አገዳ በየሜዳው በቅሎና ወድቆ ሲያዩ ማመን ተቸገሩና፣

    ፟፟"ይህ ገነት ነው!፟ ይሄ መንግስተ ሰማያት ነው!" ማለት አበዙ። ቢቸግረኝ እንዲህ ኣልኳቸው፣

    በስልጣን ዘመናችሁ በጎ ከሰራችሁ ስትሞቱ ነፍሳችሁ እዚህ ትመጣለች። ካልሆነ ግን ነፍሳችሁ ሽራሮ ትቀራለች!

    በክፉ አልያዙብኝም።

    ደኑ መስጧቸው ስቀው ብቻ አለፉኝ። አነጋገሬ በክፉ ባይዙብኝም ለካስ ያን የመሰጣቸውን ደን በክፉ አይን አይተውት ኖሮአል። መጥረቢያ ተመኙለት። የመጥረቢያ እራት ያደርጉት ገቡ። እኔም ሆንኩ የጅማ ሰው የ500 አመት እድሜ ያላቸው የቀረሮ ዛፎች ሲታጨዱ ቆመን ተመልክተናል። እነዚህ የትግራይ ተወላጅ የሆኑ ነጋዴዎች ዛፎቹን እየቆረጡ፤ በቀን ከሃያ እስከ ሰላሳ ኤነትሬ እየጫኑ ወደ ሳውዲ አረቢያ ይሸጡታል።

    ቀረሮ ለኛ ህይወታችን ነው። ቀረሮ ተመንጥሮ ካለቀ ጅማ በረሃ ትሆናለች። ቀረሮ በጣም ግዙፍና የጥንት ዛፎች ናቸው። ቁመታቸው ሰማይ ጠቀስ ነው። አንዱን የቀረሮ ዛፍ ወያኔ እስከ 15 ሺህ ብር በቁሙ እየቸበቸበ ነው። ይህን አይቼ ካልተቆጣሁና ካላመፅኩ ታድያ መቼ ነው ልቆጣና ላምፅ የምችለው? ቡናውን እንደፈለጉ ይዝረፉ። ዛፉ ግን መንካት አልነበረባቸውም። ዛፎቹ ከሌሉ ቡናው አይኖርም። ቡና ቀጥተኛ ጸሃይ መቋቋም ስለማይችል የዛፎቹን ጥላ ይፈልጋል። የትግራይ ተወላጆቹ ስለዚህ ጉዳይ ግንዛቤ የላቸውም ብቻ ሳይሆን ደንታም የላቸውም። ወደፊት ፟ትግራይ ትገነጠላለች፟ የሚል ነገር ጭንቅላታቸው ውስጥ ስላለ፣ ስለ ገንዘብ ብቻ ነው የሚያስቡት።




    ከወያኔ እብሪትና የአለማወቅ ታሪኮች መካከል የኮሎኔል ሺሻይ አሟሟት ተጠቃሽ ሊሆን የሚችል ነው። ከህወሃት የኣመራር አባላት የአንዱ ወንድም (ቢተው በላይ) የነበረው ኮሎኔል ሺሻይ በትግሉ ወቅት የጉና ክፍለሰራዊት አዛዥ ነበር። ከደርግ ውድቀት በሁዋላ ኮሎኔል ሺሻይ የኢትዮጵያ አየር ሃይል መስርያ ቤት ዉስጥ የሄሊኮፕተር ኦፐሬሽን አዛዥ ሆኖ ተመደበ። ይህ ስልጣን ሲስጠው ግን ኮሎኔል ሺሻይ ሄሊኮፕተር ተሳፍሮ ያውቃል እንጂ ስለ ሄሊኮፕተር አንዳችም እውቀት አልነበረውም። :lol:

    ታሪኩ እንዲህ ነበር.......

    ኮሎኔል ሺሻይ የዉግያ ሄሊኮፕተር ኣዛዥ መሆኑ ካልቀረ ተብሎ ሄሊኮፕተር የማብረር ትምህርት መከታተል ይጀምራል። አሰልጣኞቹ የደርግ ተሸናፊ መኮንኖች ነበሩ። ሰልጣኞች ደግሞ አሸናፊዎች። መምህራን ከልብ ሊያስተምሩ አልቻሉም። ተማሪዎች ደግሞ በመምህሩ ላይ የበላይነት ካላሳየሁ ይላሉ። አስተማሪ ደፍሮ ተማሪውን አይናገረውም። ከሺሻይ መምህራን አንዱ ሻምበል እሸቱ ገመቹ ይባላል። ሺሻይ የዚህ ሰው አለቃ ሆኖአል። ....... በዚያን ወቅት ግን መምህራን ሺሻይን "አልቻልክም! ወድቀሃል! ቻው!" ሊሉት አይችሉም ነበር። ሻምበል እሸቱ ገመቹኡ ይህን ቢያደርግ "ኦነግ ነህ!" እንዳይባል ይሰጋ ነበር። ስለዚህ መምህራን ሁሉ ሺሻይን እሹሩሩ እያሉ የሄሊኮፕተር ተዋጊ ለማድረግ መከራቸውን እያዩ ነበር።

    ይህ በእንዲህ እያለ የኤርትራ ጦርነት ተከሰተ። ከእለታት አንድ ማለዳ ወደ ቡሬ ግምባር ሄሊኮፕተር እንዲላክ ትእዛዝ ይመጣል። ኮሎኔል ሺሻይ ባስቸኳይ ሻምበል እሸቱን ያስጠራል። ሻምበል እሸቱ ገመቹ ግን በአከባቢው ሳይገኝ ቀረ። ምናልባት ሻይ ለመጠጣት ወደ ክበብ ጎራ ብሎ ሊሆን ይችላል። ወዴያ ወዲህ በማለት እሸቱን ማፈላለግ በተቻለ። ሺሻይ ግን ይህን አላደረገም። እራሱ ወደ ሄሊኮፕተሯ ገብቶ ቀሰቀሳት። በህጉ መሰረት ሽሻይ የበረራ ትምህርቱን ያልጨረሰ እንደመሆኑ ሄሊኮፕተር ብቻዉን ይዞ መሄድ የሚፈቀድለት አልነበረም። ልክ እንደ ሚኒ ባስ ሄሊኮፕተሯን አስነስቶ ወደ ቡሬ ጭልጥ አለ። :lol:

    ሄሊኮፕተር እየነዱ መሄድና፣ እየነዱ መዋጋት ግን ለየቅል ነበሩ። ገና ቡሬ ከመድረሱ የሻእቢያ ፀረ አይሮፕላን ሚሳይሎች "እንኳን ደህና መጣህ!" ሲሉ የሞቀ አቀባበል አደረጉለት። ሺሻይና ጓደኞቹ ከነሄሊኮፕተራቸው አየር ላይ ጋዩ። ወርደዉም አሰብ ላይ ተከሰከሱ።
    :oops: የኤርትራ ወታደሮች ሄሊኮፕተሯን ሲፈትሹ ሰዎቹ በመቃጠላቸው ማንነታቸው ለመለየት የሚቻላቸው አልነበረም። የጦር አይሮፕላን አብራሪዎች ግን ከብረት የተሰራች መታወቅያ አላቸው። ያንን የብረት መታወቅያ ሲፈልጉ "ሻምበል እሸቱ ገመቹ" የሚለው ያገኛሉ። ምክንያቱም እሸቱ ለበረራ ዝግጁ ስለነበር የብረት መታወቅያዉን እዚያው ትቶአት ኖሮአል። በነጋታው የኤርትራ ሬድዮ ሻምበል እሸቱ ገመቹ የተባለ ፓይለት ከነሄሊኮፕተሩ ተመቶ መውደቁን ዜና ሲያውጅ ሻምበል እሸቱ በሞቀ ኣልጋ ዉስጥ ነበር።
    :lol: :lol: :lol: :lol:

    መፅሀፍ: የደራሲው ማስታወሻ፣ በተስፋዬ ጋዳ ገብረአብ

Abe Abraham
Senior Member
Posts: 14414
Joined: 05 Jun 2013, 13:00

Re: ጄኔራል ፃድቃን ለምን አለቀሱ?

Post by Abe Abraham » 29 May 2021, 23:12

ቸበቸበ


1_እሳትን ባፈር በቅጠል አጠፋ።
2_በርካሽ ሼጠ።
3_ዐረደ ቈረጠ።


Abdisa
Member+
Posts: 6262
Joined: 25 Apr 2010, 19:14

Re: ጄኔራል ፃድቃን ለምን አለቀሱ?

Post by Abdisa » 30 May 2021, 03:50

The game was over when terrorist Tsadkan cried in front of his troops on the battlefield. :lol: :lol:

Fiyameta
Senior Member
Posts: 19939
Joined: 02 Aug 2018, 22:59

Re: ጄኔራል ፃድቃን ለምን አለቀሱ?

Post by Fiyameta » 30 May 2021, 22:04

😩😩😩😩😩

Fiyameta
Senior Member
Posts: 19939
Joined: 02 Aug 2018, 22:59

Re: ጄኔራል ፃድቃን ለምን አለቀሱ?

Post by Fiyameta » 28 Aug 2022, 17:46

:arrow: *** ይህንን ቃለ-መጠይቅ ወያኔ በሥልጣን ላይ በነበረበት በ2008 የተደረገ ነው። ***

የኤርትራዉ ጀነራል ስብሓት ኤፍሬም “ከሃይለሥላሴ እና ከደርግ ሠራዊት ጋር ሲንጻጸር የወያኔዉ ጦር እጅግ በጣም ደካማ ነዉ” አለዉ።


( ጀኔራል ስብሓት ኤፍሬም)


  • “ወዲ ኤፍሬም” በመባል የሚታወቀው የኤርትራ መከላከያ ሚኒስትርና በጀኔራልነት ማዕረግ የሚያገልገል ከፍተኛ ባለስልጣን “ታዓጠቕ” (ታጠቅ) ተብሎ በተሰየመው አሥመራ ውስጥ የታተመዉ የኤርትራ የትግርኛ መጽሄት ባወጣዉ ልዩ እትሙ ላይ ለቃለ-መጠይቅ ቀርቦ የሰጠዉ 64 ገጽ ሙሉዉን ባላቀርበዉም አለፍ አለፍ ብየ ጠቃሚ ጉዳዮችን ወደ አማርኛ ተርጉሜ ላንባቢያን አቀርባለሁ።

    << …የኤርትራ ትልቁ ስጋታችን ነዉ ብልን የምንሰጋዉ ‘ኢትዮጵያ ለወደፊቱ የኢርትራ ትለቁ ሸክም እንዳትሆንብን ነዉ የምንሰጋዉ። ምክንያቱም ኢትዮጵያ በቀጣይ የዉስጥ ሽኩቻና ቀዉስ ከመወጠርዋ በላይ፤ አገሪቷ ድሃ በመሆኗ ያለ የዉጭ ዕርዳታ መኖር ይቸግራታል፤ አትችልም። ተያይዞም ወያኔ ጦርነት እንደ ዓላማ ስለያዙት በድህነትና በረሃብ በቀጣይ ይሰቃያሉ። በረሃብና በድህነት የሚሰቃይ ጎረቤት ደግሞ መጨረሻዉ ሸክሙ ለጎረቤት ነዉ። ይህ ሁኔታ አሁን ባሉበት የዉስጥ የፖለቲካ ፍትግያና ድህነት አንዲሁም መራቡን ከቀጠሉበት፤ ሸክማቸዉ ሊከብደን ነዉ።……።>> በማለት ስጋቱን የገለጸበት ረዥሙ ቃለ፡መጠይቅ አንብቡ እነሆ።

    ወያኔን እንዴት ትመለከተዋለህ ለሚለዉ ኣጠቃላይ ጥያቄ ጀኔራል ስብሓት ኤፍሬም ሲመልስ:
    <<አንደሚታወቀዉ አሁን እያየነዉ ያለዉን አዲሱ የዓለማችን ስርዓት ሲታይ ወያኔ በዚህ መነጽር ዉስጥ እስገብተህ የአሜሪካኖች አገልጋይ መሆኑን ነዉ ምትደመድመዉ።…….>>

    ወታደራዊ ሚዛኑ -- ወያኔ’ና የደርግ እንዲሁም ከሱ በፊት የነበረዉ ጦር ስታነጻጽራቸዉ -- ወያኔ በየትኛዉ መመዘኛ ታስቀምጠዋለህ? ለሚለዉ ጥያቄ ሰፋ ያለ መግለጫ ሰጥቶበታል።

    << የወያነ ጦር ከዚህም ከዛም የተጠረቃቀመ ጦር ከመሆኑ ባሻገር፤ ተዋጊዉና አዋጊዎቹ ካለፉት ማለትም የደርግና ከሱ በፊት የነበሩ የኢትዮጵያ ሰራዊቶች ሲታዩ ወያኔ ደካማ ነዉ።…>>


    ኢትዮጵያና ኤርትራ ስታወዳድራቸዉ አሁን ሁለቱም አገሮች በምን ላይ ታስቀምጣቸዋለህ ? ለተባለዉም አንዲሁ አስገራሚ በሆነ መልስ መልሶታል።

    << ኤርትራና ኢትዮጵያ ስታነጻጽራቸዉ፤ - ኤርትራ ከጥዋቱ 5፡00 A.M. ሰዓት በንጋት ላይ ስትገኝ፤-ኢትዮጵያ ከምሽቱ 5፡00 P.M. ሰዓት ላይ ሆና የጨለማዉ ጉዞ መጛዙን የጀመረችዉ አሁን ነዉ። ንጋት ላይ ለመድረስ ረዥሙ የጨለማዉ ጉዞ መጛዝ ሊኖርባት ነዉ። >>

    • ጥያቄ :
      በደርግ ጊዜ በአንድ ወቅት ድሮ ከረን/ናቅፋን ለማስለቀቅ 6 ወር የፈጀ እልክ አስጨራሽ ዉግያዎች ተካሂደዉ አንተ በተካፈልክበት በ3ኛዉ ባታልዮን (607 እና 301- ባታልዮን) ስንመለከት፤ አንዴት አንድ ስፍራ ለማስለቀቅ ያን ያህል ረዥም ዉግያ ሊካሄድ ቻለ?


    << ሁለት ነገር እናያለን። እዛ የነበረዉ የደርግ ጦር በጣም በጣም ሃይለኛ ነበር። እኛ የደረስነዉ ከተዳከመ በጣም ከደከመ በሗላ ነዉ። እዛ የገጠመን የጠላት ጦር ብርቱ ነበር ለማለት ምትደፍርበት ምክንያት ብዙ ነዉ። አንደኛ የጠላት ጦር ለ6 ወር ሙሉ ያለ ምንም ረዳት ተከቦ ሌሊት ሌሊት ጦርነት ገጥሞ ቦታውን ሳይለቅ መጋተሩ በጣም አስገራሚ የሆነ አዋጊና ተዋጊ ጦር መኖሩን ታያለህ። በጣም ከባድ ነዉ። ቀላል አይደለም። የጠላት ጦር ያሳየዉ ቁመናም ይሄንን ነበር። የ607 እና 301 ባታልዮን ሰራዊት በጠላት ላይ ያደረገዉ ከበባ እና ቦታን የማስለቀቅ ዉግያ፤ በጣም ፈታኝ ነበር። ለ6 ወር ያክል ዙርያዉ በከበባ ገብቶ ሲዋጋ እሱን ለመርዳት በሄልኮፕተር የመጡት አየር- ወለዶች በፓራሹት ሲወርዱ ህዋ ላይ እንዳሉ ብዙዎቹ ተጎድተዋል። ሁለታችንም ረዥም ዉግያ አካሂደናል። እዛ የነበረዉ የጠላት ጦር ኮማንዶ፤ ምርጥ ከሚባሉት አንዱ ነበር። እንደነዚያ አይነቶቹ ምርጥ የጠላት ተዋጊዎች ከኛ ባታልዮን ጋር በተለያዩ የዉግያ አዉድማዎች ላይ፤ ሁለት ሦስቴ ያክል ገጥሞናል። በተለይም “ሃብረንጋቓ’ የነበሩ የጠላት የክብር ዘበኛ ተዋጊ ሃይሎች አስደናቂ የመዋጋት ብቃት ነበራቸዉ። እንደነዚህ አይነቶቹ ብርቱ የጠላት ሃይል ለማዳከም በተለይም ዙርያዉ ፈንጅ በታጠረ ምሽግ በኛ በኩል መከፈል የነበረበት እዳም ያን ያህል መሆኑ አትዘንጋ። በጣም ፈታኝ ነበር። እንደሚታወቀዉ የናቅፋ ተራሮች እርስ በርስ በትይዩ የቆሙ ናቸዉ። ያንን በፈንጅ የታጠረዉ ወረዳ ጥሶ ለመግባት በጣም ክፉ ነዉ። እዛ የነበረዉ ጠላት አዋጊ “ማሞ” ይሉታል፡- “ማሞ” ብርቱ የጦር አዋጊ ነበር። የቦታ አያያዝና የጦሩ አስገራሚ አሰላለፍ ሞያተኛ ነበር።>>

    <….ለረዥም ጊዜ ተከቦ ተዋግቷል። በሄሊኮፕተር አየር ወለዶች ሊረዱት ሞከሩ፤ ግን ለረዥም ጊዜ ተከቦ ስለተዋጋ መጨረሻ ተዳከመ። እኛም የማጥቃት ስልታችን ከሌሊት ወደ ቀን አዙረን በቀን ይዋጉናል የሚል ጥርጣሬ ስላልነበራቸዉና አድርገነዉም ስላማናዉቅ፤ ጦሩ ጥበቃዉን አላልቶ፤ ተዝናንቶ በነበረበት ሰዓት ገብተን ዉግያ ከፍተን መጨረሻ ሊደመሰስ በቃ…..።>>

    <<ስለዚህ ወያኔ በዚህ እኩል ልታየዉ አትችልም። መሰረታዊ ባህሪዉ የአዲስ ዓለም ስርዓት አገልጋይ ነዉና። ወያነ ማለት “በግ” ማለት ነዉ። በግ ትንሽ ሳር ከጣልክለት፤ ሳሯን ተደፍቶ ሲጎራርድ፤ ከሗላዉ ምን እየተዘረፈ እና እየተደረገ እንዳለም አያዉቅም። ለወያነ ግን ትንሽ ሲጥሉለት ይጠቅመዋል። ወያነ የሕዝቡን ንብረት ሲነጥቅ፤ እየጣሉለት ያሉት ጌቶቹ ደግሞ አገሪቷን ያራቁታሉ። ለሱ ብሔራዊ ጥቅም/ልማት ..የሚለዉ የዘረፋዉ መንገድ ነዉ። የስነ-አእምሮ ዉግያ እያካሄድኩ ነዉ ሚለዉም ቢሆን የአዲሱ ዓለም ስርዓት አገልጋይነቱ ለመግለጽ ነዉ። አጼ ሃይለስላሴ የመገነኛ ብዙሃን፤ ራዲዮ አላስፈለጋቸዉም ነበር፤ ምክንያቱም ስራዉ የሚከናወነዉ በቤተ-ክህነቱ በኩል ነበርና። አንደዚያ ዓይነት የቅስቃሳ ክንዋኔ ለወያኔ የሚያካሂዱለት ደግሞ አሜሪካኖች ናቸዉ። ምክንያቱም፤የአዲሱ ዓለም ስርዓት የማገልገል ስራ በአንጻሩ ለወያኔ ስለተሰጠዉ። ስራዉ ያን ተልእኮ ማገልገል ነዉ። ይህ አዲስ ስርዓት እየተባለ ያለዉ የዓለም ህዝብ ተቃዉሞታል። ያሜሪካን ሕዝብ ሳይቀር ተቃዉሞታል። ወያኔ ብቻ ነዉ ባገልጋይነት የቆመዉ። የስነ-ኣእምሮ ትግል የማካሄዱ ስራ በደረግ ጊዜም የነበረ ነዉ። ወያኔ አሁን እየደገመዉ ያለዉ ያንኑ ነዉ። “ዉግያ” እያለ የሚጠራዉ ያነን ነዉ። >>

    <<…..በወታደራዊ መልኩ ግን የደረግ ሰራዊትና የወያነ ይለያያል። የደረግ ሰራዊት በወታደራዊ ስነምግባረና በሙያዉ የተለየ ነዉ። ሌላ ስራዉን ትተህ፤ በጣም እልከኛ ተዋጊ ሰራዊት ነበር። የደረግ የጦር አለቆች በሰራዊቶቻቸዉ አድናቆትንና ተወዳጅነት ያተረፉ ነበሩ። አዋጊዎቹን ስትመለከት፤ በጣም ጎበዞች ፤ ሃይለኞች ነበሩ። እነ ረጋሳ ጅማ እነ ታሪኩ ላይኔ….ወዘተ .ወዘተ .. የሚባሉ አዋጊዎቻቸዉን ስትመለከት ከፍተኛና ልዩ ችሎታ ያላቸዉ አዋጊዎች ነበሩ። በጣም ልዩ ነበሩ። እልከኞች ነበሩ።

    <<... የኛ ሰራዊት ከእነደዚያ ዓይነቱ ምርጥ አዋጊና ተዋጊ ጦር መግጠማችን ያኮራናል። የጠላት አዋጊዎችም በኛ ሰራዊት አድናቆትን አትርፎላቸዋል። በእንደዚህ ዓይነት ሃየለኛ ሰራዊት እና አዋጊዎች ባየነበት ዓይናችን የወያኔን ጦር ስንመለከት አንደነዚያ ዓይነት አዋጊዎችና ባለሞያተኞች የሉትም። ለሽታ ፈልገህ አታገኝባቸዉም
    ……….። >>

    << ….ወያኔን ከአዲሱ የዓለማችን ስርዓት ጋር አያይዘህ ነዉ ማየት ያለብህ። አዲሱ የዓለማችን ስርዓት ዓለምን በኢኮኖሚና በዲፕሎማሲ አንቆ ሊይዝህ የሚፈልግ ነዉ። ከዚም ከዚህም እየዘረፈ ወደ ሌላ መጓዝ። ያለንበት ዓለም በዚህ እየተመራ ስላለ በዓለም ዉስጥ ያሉት የብዙሃን የመገናኛ ጋዜጦች ሁሉ ተቆጣጥሮ ሁሉም ጋዜጦች በአንድ ርዕስ አንዲዘጋጁ ያደረግጋል። ከሚተነተነዉ ርዕስም አብሮ ትንሽ ወታደራዊ ነክ ጉራ ይጨመርበታል።



    ከሚተነተነዉ የስነ ዓእምሮ ትነተና ዉስጥ የወያኔ ሃይል ትነሽ ነጥብ ነች። የወያኔ ጦርነት የስነ-ዓእምሮ ጦርነት ነዉ። ሌላዉ ነገር ዉስጡ ባዶ ነዉ። ያ የስነ-ዓእመሮ ጦርነት ነጥለህ ብትለየዉ የወያኔ አቅም ኢሚንት ነዉ። ምን ዉግያ አለዉ? የለዉም! ወታደራዊ ስልቱ ስፍር ቁጥር የሌለዉ የሰዉ ሃይል ሰብሰቦ መዋጋት ብቻ ነዉ። ትንሽ ቦታ ለማግኘት በብዙ ሺህ የሚቆጠር የሰው ሕይወት ያስፈጃል። ኤርትራ 19,000 ሺህ ሰዉ ሲሰዋባት ዉያኔ 170,000 ሺህ ሰዉ ነዉ ያስፈጀዉ። የከፈለዉ ሕይወት በጣም ብዙ ነዉ። ታሞ በህመም የሞተ ሳይጨምር ማለት ነዉ። የደርግ ሰራዊት እኮ ልክ አንደፊተኛዉ ሰራዊት በስለቱም በጥንካሬዉም እያደገ የመጣ ሰራዊት ነበር። የወያኔ ሰራዊት ጥርቃሞ ነዉ። ከዚህም ከዚያም ለቃቅሞ ያቆመዉ ነዉ።
    ከወያኔ በፊት የነበረዉ ጦር በፍጹም ታወዳዳሪ አይገኝላቸዉም። ወያኔ አቅሙን መጥኖ ስለማያዉቅ፡ አቅምም ስለሌለዉ፤ የኢኮኖሚ ረዳት የሌላትን ኤርትራን በኢኮኖኖሚ እናንቃታልን እያለ ነዉ የስነ እምሮ ዉግያዉን እየነዛ ያለዉ።

    <<……..የስነ-ዓእምሮ ጦርነቱን አብረዉ የሚያጫፈሩት አንዳንድ ኤርትራዊያን ቅጥረኞቹን ድሮ የተረሱ፤ የበሰበሱ፤ የሞቱ በድን ድርጅቶችን አፈላልጎ እያስባሰባቸዉ ነዉ። እነዚህም በነገርኩህ በዛዉ በስነ-ዓእምሮዊ ዉግያዉ ዉስጥ እንደ ፓኬጅ ጨምራቸዉና ገምግመዉ። ግልጽ ነዉ! ዉግያዉ ከዚያ አያልፍም። ወያኔ ሊያደረጋት የሚችላት አቅሙ ያች ብቻ ነች። በዚህ መለኪያ ስትመዝነዉ የወያኔ አቅም ለመገመት የሚያሳስት ነገር አይደለም።>>



    • ጥያቄ :
      የወያኔ ሰራዊት ገፍቶ ወደ ዉስጥ ኤርትራ በመዝለቁ እንደ ወታደራዊ የበላይነት ተደርጎ ይታያል። የሄንን እንዴት ትመለከተዋለህ?


    << ወያኔ በወታደራዊ ሃይል የበላይነት ለማግኘት ሦስት ጊዜ ሞከረ። መጀመሪያ፤ ሁለተኛ…..ሦስተኛ ጊዜ የባሰ መጣበት። ከዚያ ወዲያ መቀጠል ስላልቻለ አቅም ስላልነበረዉ ወደ አልጄርስ ለመሄድ ተገደደ። እዛም በሽንፈት ተከናንቦ የውርደት ዉርደቱን አገኘ። በሽንፈት ላይ ሽንፈት ኪሳራ ደረሰበት። ያካሄደዉ ዉግያ የስነ-ዓእምሮ ዉግያ ነበር፡ በሺዎቹ የሰዉ ሕይወት ታስፈጅና በምትኩ፤ ትንሽ ቦታ ይዘህ ከየአቅጣጫዉ ጋዜጠኞችን ሰብስበህ “ኑ እዩልኝ፤ ዘግቡልኝ” ይላል። የኛ ጦር በኤርትራ ምድር በየአቅጣጫዉ በስፋት ስለዘረጋነዉ፤ ወያኔ በሺዎቹ የሰዉ ሃይል ሰባስቦ በአንድ አቅጣጫ መጣ። ያ ዕድል ነበር ለወያነ የሰጠነዉ። እኛ በአቅማችን እንተማመናለን። ይሄ የሚያስጨንቀን አይደለም። የዉግያ ሙያ የሚያዉቅ ያዉቀዋል። ቀስ እያልን እንደምንጠርገዉ ያዉቅ ነበር። ለዚያም ነበር ያቆመዉ። እስኪ እንደዉ በእዉነቱ ወያነ ከጸሮና ዉግያ ወዲያ ዉግያ መቀጠልና ማሰብ ነበረበት? ያ የታየዉ የሬሳ ክምር፤ የዉትድርና ብቃት ምልክት አይደለም። በዓለም ጋዜጦች የተዘረጋዉ በቲቪ የታየዉ የሬሳ ክምር እኮ ሙሉዉን አልታየም። በዓይን ስታየዉ እኮ የክምሩ ብዛት በእዉነቱ “በፍሊት” መርዝ የተፈጁ ነበር የሚመስሉት። በፍሊት የተገደሉም እንደዚያ ዓይነት የሰዉ ሬሳ “ክምር፤ በክምር ላይ ተደራርቦ” ማየት ያስቸግራል። 170,000 ሰራዊት አስፈጅቶ አንዴት ድል በድል ሆንን ይላል? አቅም ኖሮት ወያኔ ቢችል ኖሮ ነበር 10 ጊዜ ወደ ፍርድ ቤት እየሄደ ዉሸትና መለማመጥ የመረጠዉ? ያ ሊያደርገዉ የሚችለዉ አቅሙ ያኔ አብቅቷል። ጊዜዉ አልቋል። አሁን የቀረዉ ፕሮፖጋንዳ የስነ ዓእምሮ፤ ጉራና መዋሸት ብቻ ነዉ።

    ወያነ ደካማ መሆኑን የምታዉቀዉ ባደረጋቸዉ ሥስት ሙከራዎች ላይ ነዉ። የወያኔ የድሮ ተዋጊዎች አብዛኛዎቹ በዉግያዉ ተፈጅተዋል። ትግራይ ዉስጥ የመወያያ ርዕስ ሆኖ የሚነገረዉም ይህነኑ ነዉ። ድል አመጣሁ እያለ ወያነ የሚለፍፈዉ፤-ድሉ ከየት መጣ ቢባል- የስነ ዓእምሮ የፖለቲካ ወግያና የዲፕሎማሲ ዉግያዉ ነዉ። ያነን የስነ እምሮዉ ዉግያዉ ብትለየዉ ወታደራዊ አቅሙ 20% አይበልጥም። …ወያነ ኤርትራን ቢቆጣጠር ነብሰጡሮች ቁጥቋጦ ስር ነበር የሚወለዱት። ተመልከት ለአማራ ህዝብ እያደረጉት ያሉትን ግፍ። መልከመልካም ሚስቶቻቸዉን እየነጠቁ ያማግጧቸዋል። ልጆቻቸዉም አንደዚሁ። ባኦጋዴን፤ በሶማሊ እየፈጸመ ያለዉን ድርጊት በአልጀዚራ በቲቪ ያየነዉ ነው።>>




    • ጥያቄ :
      ወያነ የያዛቸዉን ሉአላዊ መሬታችን አልሰጥም ብሏል በዚህ የምትለዉ ነገር ካለ አስተያየትህ?


    <<ወያነ ከግዛታችን ካስነሳልን በጀ! ለሱም ይበጀዋል። ካላነሳም ማስነሳቱን የሚከብድ አይደለም።የድምበር ክርክር ጉዳይ ያበቃለት የሞተ ጉዳይ ነዉ። ኢትዮጵያን ስንመለከት አርግዛለች። ምን እንደምትወልድ ግን ሕዝቡ እየተጠባበቀ ነዉ። በእወነቱ ኢትዮጵያ ማርገዝ በተገባት ነበር? አያስፈልጋትም። ሕዝቡ ከወያኔ ማነቆ ተገላግሎ ወደ ሌላ ሽግግር እያመራ መሆኑን እያታዘብን ነዉ። ይህ ከድምበር ጋር የተያያዘ ይሁን አይሁን ሌላ ጉዳይ ነዉ። በኛ በኩል ፤የድምበር ጉዳይ አልቆለታል። የተባበሩት መንግሥታት ከዚህ ተባሯል። የቀረ ነገር ካለ፤ “የተባበሩት መንግሥታት” ስሙን አንዴት ያስመልስ/ያ’ሳድስ ነዉ። ስሙን በእንዴት መልክ ማሳመር እንዳለበት የራሱ የግሉ ጉዳይ ነዉ። ለራሱ ችግር ሲል። የኤርትራ ጉዳይ አንደሆነ ያለቀለት ነዉ። የኛ የተሰጠዉ መሬት በፈለግንበት ሰዓት መልስን መዉሰዳችን የማይቀር ነዉ። ዓለምም ብትሆን ወዳ ሳትሆን በግዷ የኛዉን ትቀበላለች። ኤርትራንም እኮ ወዶ የሰጠን ሃይል የለም። የተባበሩት መንግሥታት እኮ በ50ዎቹ ወደ ኤርትራ መጥቶ ነገር አበላሽቶ ሄደ። ነጻ ስናወጣት ተመልሶ መጣ። አሁንም መሬታችን ካስመለስን በሗላ፤ ያ ሲሆን- ተመልሶ እንደገና ይመጣል። ይሄ እኮ ነዉ የተባበሩት መንግሥታት ማለት። ሌላ የተባበሩት መንግሥታት የለም። የማናዉቀዉ ሌላ የተባበሩት መንግሥታት የለም። ሄልኮፕተራችሁ ከዚህ አስነሱ፤ ልቀቁ ብለን ስናስነሳቸዉ አዉቀዉታል፡ ያኔ ያለቀ መሆኑን ያቃሉ።>>

    …….ኤርትራ ወያኔን ለማጥቃት ህጋዊም ሆነ ወታደራዊ መብት አላት። የተባበሩት መንግሥታት ኖረ አልኖረ፤ የተባበሩት መንግሥታት ሄደ አልሄደ ጦርነት ሊያስቆም አይችልም። ለዚህ ነዉ ኤርትራ ዉስጥ ሲነጋ በነሱ ምሽት ሆኖ ጨለማዉ ገና መያያዝ የጀመሩት። ገና አልነጋላቸዉም። ኢትዮጵያ ሰላም አንድታገኝ ብልን ድሃ ስለሆነች በዉስጣዊ ዉጥረት ስለተወጠረች ሰላም እንድታገኝ ብለን፤ ለኛም ሸክሙ አንዲቀለን፤ ሸክማቸዉ የኛ እንዳይሆን፤ ብለን እጃችን አስገብተናል። ኤርትራ አንደ መዓከላዊ ስበት ሆና መታየትዋ የማይቀር ነዉ።

    ……እሳቱ እየነደደ ነዉ። እኛ ከእሳቱ አጠገብ ነን፡ ያለነዉ። እሳቱ ነዶ ወደ አመድ ለመለወጥ ሊቀረዉ በቁጥር ስንት ያክል የማገዶ እንጨቶች እንደቀሩ የሚያዉቀዉ ከእሳቱ አጠገብ ላይ ያለዉ ሰዉ ነዉ የሚያዉቀዉ። ከእሳቱ አጠገቡ ላይ ያለነዉ ደግሞ እኛ ነን።……>>


    • በማለት “ተዓጠቕ”/ታጠቅ ከተባለዉ ወታደራዊ መጽሄት የሰጠዉ ቃለ መጠይቅ አንኳር አንኳር ነጥቦች እነዚህ ነበሩ።.



Fiyameta
Senior Member
Posts: 19939
Joined: 02 Aug 2018, 22:59

Re: ጄኔራል ፃድቃን ለምን አለቀሱ?

Post by Fiyameta » 28 Aug 2022, 17:57

:lol: :lol: :lol: :lol: :mrgreen:




Weyane.is.dead
Member+
Posts: 6796
Joined: 19 Oct 2017, 11:19

Re: ጄኔራል ፃድቃን ለምን አለቀሱ?

Post by Weyane.is.dead » 28 Aug 2022, 19:02

Where is shi.ntam Tsadkan hiding these days :mrgreen: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol:

Fiyameta
Senior Member
Posts: 19939
Joined: 02 Aug 2018, 22:59

Re: ጄኔራል ፃድቃን ለምን አለቀሱ?

Post by Fiyameta » 28 Aug 2022, 19:23


Weyane.is.dead
Member+
Posts: 6796
Joined: 19 Oct 2017, 11:19

Re: ጄኔራል ፃድቃን ለምን አለቀሱ?

Post by Weyane.is.dead » 28 Aug 2022, 20:03

:idea: :idea: :idea:
Fiyameta wrote:
28 Aug 2022, 19:23

Fiyameta
Senior Member
Posts: 19939
Joined: 02 Aug 2018, 22:59

Re: ጄኔራል ፃድቃን ለምን አለቀሱ?

Post by Fiyameta » 28 Aug 2022, 21:11






Fiyameta
Senior Member
Posts: 19939
Joined: 02 Aug 2018, 22:59

Re: ጄኔራል ፃድቃን ለምን አለቀሱ?

Post by Fiyameta » 29 Aug 2022, 14:33

:| :| :| :|


Abdisa
Member+
Posts: 6262
Joined: 25 Apr 2010, 19:14

Re: ጄኔራል ፃድቃን ለምን አለቀሱ?

Post by Abdisa » 29 Aug 2022, 16:18

They made General Tsadkan cry "Joe Biden Uuuuuye!" :lol: :lol: :lol: :mrgreen:

Fiyameta
Senior Member
Posts: 19939
Joined: 02 Aug 2018, 22:59

Re: ጄኔራል ፃድቃን ለምን አለቀሱ?

Post by Fiyameta » 04 Sep 2022, 06:49


Fiyameta
Senior Member
Posts: 19939
Joined: 02 Aug 2018, 22:59

Re: ጄኔራል ፃድቃን ለምን አለቀሱ?

Post by Fiyameta » 16 Jun 2023, 21:05

:lol: :lol: :lol: :lol: :mrgreen:


Fiyameta
Senior Member
Posts: 19939
Joined: 02 Aug 2018, 22:59

Re: ጄኔራል ፃድቃን ለምን አለቀሱ?

Post by Fiyameta » 16 Jun 2023, 22:19

:P :P :P :P


Post Reply