Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
tarik
Senior Member+
Posts: 37268
Joined: 26 Feb 2016, 13:04

^^^(((JUST IN)))^^^Videos Of:ከአማራ ክልላዊ መንግስት በወቅታዊ ጉዳይ ላይ የተሰጠ መግለጫ!!! WEEY GUUD !!!

Post by tarik » 27 Aug 2022, 16:29



Ethiopian Press Agency /የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት/

ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በወቅታዊ ጉዳይ ላይ የተሰጠ መግለጫ‼️

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ባለፉት አራት ዓመታት የክልሉ ሕዝብ በኢትዮጵያ ኅብረ ብሔራዊ አንድነት ሥር ተጠቃሚ የሚሆንበትን ወሳኝ ተግባራት አከናውኗል።

ይህን ሁኔታ የተረዳው አሸባሪው የህወሃት ቡድን የአማራ ሕዝብና መንግሥት የራሱን የመልማት ዐቅም ተጠቅሞ የራሱን ዕድገት የሚያረጋግጥበትን ዕድል ለማጨናገፍ ከመነሻው ዓላማ ይዞ እንደሚንቀሳቀስ ይታወቃል።

በቀጥተኛ እና በተዘዋዋሪ መንገድ በመላ ኢትዮጵያ በሚገኘውን የአማራ ሕዝብን ላይ የተጠኑ፣ ተከታታይነት ያላቸው፣ አሰቃቂ ዘር ተኮር ጥቃቶችን፣ ግድያዎችን፣ ዝርፊያና መፈናቀል እንዲደርስበት በማድረግ አማራን ማኅበራዊ ዕረፍት የመንሣት ስልትን ሲከተል ከርሟል፡፡

በዚህ የጥፋትና የእልቂት ድርጊቱ ያልተገታው ሽብርተኛው የህወሃት ቡድን የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት አደጋ ላይ የሚጥል ክህደት ፈጽሟል። በዚህም በሀገር መከላከያ ሠራዊት ሰሜን ዕዝ ላይ ወታደራዊ ጥቃት አድርሷል። ከዚህም አልፎ በመልከአ ምድራዊ አቀማመጡም ሆነ በባህላዊና ሃይማኖታዊ መስተጋብሮቹ ከትግራይ ሕዝብ ጋር የሺ ዓመታት የአብሮነት ታሪክ ባለው የአማራ ክልል ሕዝብ ላይ ወረራ በመፈጸም ከፍተኛ ሰብአዊ ጉዳቶችን አድርሷል።

ከ288 ቢልዮን ብር በላይ ግምት ያላቸው መሠረተ ልማቶችና ተቋማትንም አውድሟል፡፡

የክልሉ መንግሥት በአማራ ሕዝብ ላይ የህልውና አደጋ ጋርጠውበት የነበሩትን እነዚህን ሁሉ ግፎች ለመከላከል ጥረት ከማድረግ በዘለለ ወደለየለት መጠፋፋት እንዳይገባ ከፍተኛ ጥንቃቄ በማድረግ የተፈጠሩት ግጭቶች ሁሉ በሰላማዊ መንገድ የሚፈቱበትን አማራጮች በማስቀደም ከሁሉም በፊት እና ከምንም በላይ ለሰላም ቅድሚያ ሰጥቶ ቆይቷል፡፡

ይሁን እንጂ ሽብርተኛው የህወሃት ቡድን ለሰላም የተከፈተውን በር በሚፈጽማቸው የጦርነት ትንኮሳዎችና ወረራዎች ስለዘጋው የጋራ ታሪካችን እና ስለ መጪው አንድነት፣ ዕድገትና ተስፋ ስንል ቅድሚያ የሰጠነውን የሰላም ዕድል በተደጋጋሚ አምክኗል፡፡

ዛሬም ቢሆን የትግራይ ክልል አዋሳኝ በሆኑ የክልላችን አካባቢዎች ላይ ለአራተኛ ጊዜ ወረራ በመፈጸም ከወራት በፊት በክልላችን ሕዝብ ላይ የፈጸመውን ሁለንተናዊ ጥቃት ለመድገም እየተክለፈለፈ ይገኛል፡፡

ይህ ጦር ናፋቂ የሽብር ቡድን በንጹሐን ዜጎች፣ በሃይማኖት ተቋማት፣ በዓለም አቀፋዊ የሰብአዊ ድጋፍ ሰጪ ድርጅቶች ላይ የፈጸማቸው ጥቃቶች የቡድኑን እውነተኛ ማንነት አጋልጠውታል።

በመሆኑ መላው ሰላም ፈላጊ የሰው ዘር እና ዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ የሽብር ቡድኑን ሊያወግዝ እና ለፈጸመው ወንጀል ተጠያቂ እንዲሆን ግፊት ሊያደርጉ ይገባል።

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ሁሉንም ዓይነት ግጭቶች በሰላማዊ መንገድ ብቻ እንዲፈቱ የሰነቀው ልባዊ መሻት ጽኑ ነው። ነገር ግን በአሸባሪው የህወሃት ቡድን እምቢተኝነት ምክንያት የሰላም አማራጮች የተዘጉ በመሆናቸው የክልሉ መንግሥት የሕዝቡን ደኅንነት የማስጠበቅ መንግሥታዊ ግዴታውን እንዲወጣ አስገድዶታል።

ስለዚህም በአሸባሪው የህወሃት ቡድን የተቃጣበትን ወረራ ለመቀልበስ የሚያስችል አስፈላጊና ተመጣጣኝ ዝግጅት በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡

በመሆኑም መላው የአማራ ሕዝብ የክልሉ መንግሥት የሚያቀርበውን ጥሪ በንቃት እንዲጠብቅና ተገቢውን ሁሉ ዝግጅት እንዲያደርግ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ከወዲሁ ያሳስባል፡፡

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት
ነሐሴ 21 ቀን 2014 ዓ.ም.
ባሕር ዳር See less

=================================================================================================================================