Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 42902
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

የአቢይ አህመድ ከተማ እቅድ ፍልስፍና፤ ከተማ እንደ ቱሪስት ትዕይንት ሸቀጥ!

Post by Horus » 22 Aug 2022, 02:28

በአቢይ አህመድ የሚመራው ያዳነች አቤቤ አዲስ አበባ በ4 አይነት ከተማዎች ይከፈላል!

አዲስ አበባ 1፤ የአቢይ አህመድ እጅግ ተወዳጅ የሆነው እና የእድገት ብቻ ሳይሆን የስልጣኔ መለኪያ የሆነው የፓርክና መነፈሻ የላንቲካ ከተማ ነው። የላንቲካ አዲስ አበባ ከቸርችል ጎዳና በድሮ አፍሪካ አዳራሽ እስከ ቦሌ ማረፊያ ያለው ለፈረንጅ እይታ ንግድና ለመንግስት ግጽታ የሚደረገው ብልጭልጭ ነው ። ምስራቅ አዲስ አበባ እንዳንል ይህ ባበባ የማስዋብ ፍልስፍና ካሳን ጂስ እንኳ አይደርስም! ይህ የአቢይ አህመድ አዲስ አበባ ነው። ድሮ ጣሊያኖች ለራሳቸው የሰሩት አዲሱ ፒያሳ ማለት ነው።

አዲስ አበባ 2፡ ዛሬ ያዲስ አበባ ዳውን ታውን የሆነው የድሮ ሰንጋ ተራ ሲሆን ዛሬ ይህ የግዙፍ ረጃጅም የባንክ ህንጻዎች ጫካ ሲሆን ይህን ጫካ አዲስ አበቤ የሚያየው በቲቪና በቪዲዮ ነው፤ ልክ እንደ ዱባይ ማለት ነው ። ይህ ሁለተኛው አዲሳባ ነው ።

አዲስ አበባ 3፡ ከኮልፌ ቀራን ዮ በምራብ ዞሮ በቦሌ ቡልቡላ ዞሮ እስከ ብስራተ ወንጌል በፕላንና በፕላስቲክ የተከተሙት አስቀያሚ ቅርጽ አልባ በረት የሚመስሉ አስቀያሚ ኮንዶሚኒየም ፎቅ ተብዬ ክምችቶች ናቸው ። ብቻ ያዲሳባ ሰበርብ እነበለው። አቢይ ስለነዚህ የሚሊዮኖች መታጎሪያ ጌቶ ፕሮጅክት ሃውሶች አንድም ያለውና የሚለው ነገር የለም ። ምን አይነት ኧርባን ፕላኒግ ይህን መሰል አስቀያሚ የሰዎች መታጎሪያ እንደ ጸንሰ ወደፊት ልሂቃን ይጽፉበታል።

አዲስ አበባ 4፡ እና የከተማው የልብ ትርታ፣ ሸገር ኢኮኖሚ እስትንፋስ መርካቶ ኢንዲጂኖ ነው ። ይህ የውነተኛው አዲስ አበቤ ከተማ በሌሎች አገር ከተሞች እንደ ፓሪስ፣ ሎንዶን፣ ኢስታንቡል፣ ማራኬሽ፣ ካይሮ፣ ባንኮክ፣ ጃኒፑር ህንድ፣ እና ቶኪዮ ያገሪቱ፣ የከተማው እስትንፋስና የመንግስት ሁሉ ትኩረት ማዕከል ነው ።

አቢይ አህመድ ላለፉት 4 አመታት ነጋ ጠባ እንደ አሻንጉሊት ስለ ቸርችል ጎዳና ማስታወቂያ ሲሰራ አንድም ቀን ታላቁን መርካቶ የአፍሪካ ታላቁ ገበያና ከጣሊያን ወረራ ጀምሮ የምር ኢትዮጵያዊያን መገለጫ የትም ተወለድ መርካቶ እደግ ስለተባለው ያዲስ አበባ ኤሰንስ መርካቶ አንድ ቃል እንኳን ተናግሮ አያቅም ።

ይህን መሰል ፕላስቲክ፣ ፎኒ፣ የሲሊማ ኤረክላም የሚመስሉ የማስታወቂያ ቢል ቦርድ መሪዎች ናቸው የዘመናችን ከተሜነት ፍላስፋዎች! ያሳዝናል! ያሳፍራል! እነአቤቤን እስቲ ጠይቋቸው? መርካቶን እንዴት አድርገው ባለም ከታወቁት ዝነኛ የከተማ ገበያ ሊያደርጓት እንዳሰቡ!!

መርካቶ የሌለባት አዲስ አበባ፣ ልክ እንደ ጣሊያን ዘመን የቱሪስት ፎቶ መነሻ ትርጉም አልባ ከወነተኛው የህዝብ ሕይወትና ካልቸር ውጭ የተፈበረከች አርቲፊሻል ፕላስቲክ ማለት ነው።

መርካቶ የሚለው ቃል ከአቢይ አህመድ አፍ ወጥቶ አያውቅም! አዳነች አቤቤም እንዲሁ! ይህን ሳይኮሎጂ በጥልቀት አስቡት! ያስገርማ

በነገራችን ላይ ዛሬ ቸርችል ጎዳና የሚባለው አዲስ አበባ ጫካ በነበረበት 1900 ከአራዳ ጎርጊስ በቀጥታ ባቡር ጣቢያ ይወስድ የነበረው ጭቃ የግር መንገድ ነው በዘመኑ ባቡር መንገድ ይባል የነበረው ። ለዚህም ነው ዛሬ ማንኛውም መንገድ ባቡር መንገድ ብለን የምንጠራ !!!! ይህን ታሪካዊ ስሙን እንኳን ሳይለውጥ ነው አቢይ ቸርችል ጎዳና እያለ የሚያደነቁረን ።

ቢያንስ ቢያንስ ችርችል ጎዳናን ወደ መጀመሪያ ስሙ ባቡር መንገድ ቢልወጥ ምን ያህል ባከበርነው!! አቢይ ምን ያህል አዲሳባን እንደ ሚያውቅ ይህ ምስክሩ ነው !!


Horus
Senior Member+
Posts: 42902
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የአቢይ አህመድ ከተማ እቅድ ፍልስፍና፤ ከተማ እንደ ቱሪስት ትዕይንት ሸቀጥ!

Post by Horus » 22 Aug 2022, 03:20

አጌ ጉበኛው አልወለድም ከሚለው ምጽሃፉ ቀጥሎ በደረሰው ሰይፈ ነበልባል፣ ይህ የከብት እረኛ የሕዝብ መሪ መሆን አይገባውም ብሎ ነበር !!!!


Post Reply