Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
DefendTheTruth
Senior Member
Posts: 13262
Joined: 08 Mar 2014, 16:32

Guraghe Youth Uprising in Ethiopia, Video!

Post by DefendTheTruth » 20 Aug 2022, 12:27

Horus
Senior Member+
Posts: 42903
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: Guraghe Youth Uprising in Ethiopia, Video!

Post by Horus » 20 Aug 2022, 13:01

DefendTheTruth wrote:
20 Aug 2022, 12:27
DTT
ለቪዲዮ አመሰግናለሁ! ይህ የምታየውን ሁሉ አድርጌ ነው ሶዶ ያደኩት ። ዛሬ የቡሄ ቀን የምጅር ማይ እንለዋለን። ምጅር ማለት ደመራ ማለት ሲሆን የቃሉ ትርጉም መጀመሪያ ማለት ነው። መስቀል የጸሃይ መውጣት ማለት ነው ። ቡሄ ማለት ቦ የሚለው የግዕዝ ቃል ሲሆን ጉራጌ ዬቦ የሚለው ነው፤ እሱም በራ፣ ፈካ፣ ሆነ፣ ተከሰተ ማለት ነው ። ሌላው ቀርቶ እዚህ ቪዲዮ ውስጥ ያቀረቡት የሰባ ጨዋታ ትርጉሙን ረስተውት እንጂ ቃሉ ጸባ ወይም ነጋ፣ ጸሃይ ወጣ የሚለው ቃል ነው ። በግዕዝ ጽብሃ ያልወዋል። ክስታኔ ጸጥበት ወይም ጠዋት የምንለው ነው።

የቡሄ ለት የደመራ መትከያ፣ የምጅር መትከያ ቀን ማንም ሰው ዛፉ እንዳይቆረጥበት ሊከለክል አይችልም። ቪዲዮ በትክክል እንደ ሚለው ቡሄ የመስቀል መጀመሪያ ነው ። ከዚያን ቀን ጀምሮ ማታ ማታ በደመራው ዙሪያ እንዘፍናለን። ልጃገረዶች ኢምር አሚር የሚባለ እጅግ ጥናታዊ ዘፈን ይዘፍናሉ። ኢምር እጹብ ድንቅ ብርሃን ማለት ሲሆን የኮከብ ብርሃን ማለት ነው። ያው ትርጉሙ ላዲሱ አመት፣ ላዲሱ ሰን ራይዝ ብርሃነ ጽባህ የሚደረግ ባህል ነው።

መስከረም 1 በክስታኔኛ አክራሚ ይባላል ። ደመራ በመስቀል ተቀጣጥሎ የወጣቶቹ ልዩ ልዩ በአላት እስከ ጥቅምት አቦ የቀጥላል። በጥቅምት 5 መስቀል ያበቃል ። ጉራጌ የባህል፣ የካልቸር ሙዚየም ነው!!!

ይህን ሁሉ ፈረሰ እስከ መጋለብ አድርጌው አድጌበታለሁ! ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!!

ነጆ አራጆ (ከእንቁታጣሽ ጀምሮ ያለ ጨዋታ)

DefendTheTruth
Senior Member
Posts: 13262
Joined: 08 Mar 2014, 16:32

Re: Guraghe Youth Uprising in Ethiopia, Video!

Post by DefendTheTruth » 20 Aug 2022, 13:23

Horus wrote:
20 Aug 2022, 13:01
DefendTheTruth wrote:
20 Aug 2022, 12:27
DTT
ለቪዲዮ አመሰግናለሁ! ይህ የምታየውን ሁሉ አድርጌ ነው ሶዶ ያደኩት ። ዛሬ የቡሄ ቀን የምጅር ማይ እንለዋለን። ምጅር ማለት ደመራ ማለት ሲሆን የቃሉ ትርጉም መጀመሪያ ማለት ነው። መስቀል የጸሃይ መውጣት ማለት ነው ። ቡሄ ማለት ቦ የሚለው የግዕዝ ቃል ሲሆን ጉራጌ ዬቦ የሚለው ነው፤ እሱም በራ፣ ፈካ፣ ሆነ፣ ተከሰተ ማለት ነው ። ሌላው ቀርቶ እዚህ ቪዲዮ ውስጥ ያቀረቡት የሰባ ጨዋታ ትርጉሙን ረስተውት እንጂ ቃሉ ጸባ ወይም ነጋ፣ ጸሃይ ወጣ የሚለው ቃል ነው ። በግዕዝ ጽብሃ ያልወዋል። ክስታኔ ጸጥበት ወይም ጠዋት የምንለው ነው።

የቡሄ ለት የደመራ መትከያ፣ የምጅር መትከያ ቀን ማንም ሰው ዛፉ እንዳይቆረጥበት ሊከለክል አይችልም። ቪዲዮ በትክክል እንደ ሚለው ቡሄ የመስቀል መጀመሪያ ነው ። ከዚያን ቀን ጀምሮ ማታ ማታ በደመራው ዙሪያ እንዘፍናለን። ልጃገረዶች ኢምር አሚር የሚባለ እጅግ ጥናታዊ ዘፈን ይዘፍናሉ። ኢምር እጹብ ድንቅ ብርሃን ማለት ሲሆን የኮከብ ብርሃን ማለት ነው። ያው ትርጉሙ ላዲሱ አመት፣ ላዲሱ ሰን ራይዝ ብርሃነ ጽባህ የሚደረግ ባህል ነው።

መስከረም 1 በክስታኔኛ አክራሚ ይባላል ። ደመራ በመስቀል ተቀጣጥሎ የወጣቶቹ ልዩ ልዩ በአላት እስከ ጥቅምት አቦ የቀጥላል። በጥቅምት 5 መስቀል ያበቃል ። ጉራጌ የባህል፣ የካልቸር ሙዚየም ነው!!!

ይህን ሁሉ ፈረሰ እስከ መጋለብ አድርጌው አድጌበታለሁ! ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!!

ነጆ አራጆ (ከእንቁታጣሽ ጀምሮ ያለ ጨዋታ)
Horus,

Amen, awo ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!!.

Sorry, I don't have Geez font on this computer, so I have to reply in my poorer english than in Amharic, which is also not so good but still better.

The cultural practice you described in here is by no means exotic to me, I too lived in a society that celebrated Buhe and considered it the beginning of the spring, when the weather will get drier and more sun will be shinning, the beginning of a new year, after the old and darker rainy season goes to end.

In my family we also alighted a Bonfire, a smaller one than the one to Meskel, we children were given a piece of Mulmul bread, a smaller bread but the whole of it. It was specifically made for boys, I remember, and we were allowed to go for Buhe celebration, during the day, if you are younger, in the evening or at the night if you are old enough, we tour the villages and collect gifts, in kind or cash and then share it among ourselves.

No one will say "I don't have, else we will curse in our songs of Hoya Hoye, Hoy....

That was back then, today I sit here on someone else's computer and scribble something, unaware of the Holiday...

Melkam Beal!

Horus
Senior Member+
Posts: 42903
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: Guraghe Youth Uprising in Ethiopia, Video!

Post by Horus » 20 Aug 2022, 13:33

ጉራጌን በመከፋፈል ላይ ያለው የብልጽግና ሴራ ይህን ቪዲዮ እንኳን የጉራጌ ባህል ብሎ ለጠራው አይፈልግም፤ ክስታኔን ከጉራጌ የመገንጠል ሴራ አይሰራም ክስታኔ የጉራጌ ግንድ ነው ። EBC ETV የጉራጌ ሕዝብ ምክር ቤት ስብሰባ አንድ ግዜ እንኳን ረፖርት ሳያደርግ፣ የክለሰተር ተከፋዮች ስብሰባ ቀጥታ ያስተላለፈ ጸረ ጉራጌ ኢዜአ ፣ሙሉ የዜና እቀባ በጉራጌ ላይ ጥሎ ሲያበቃ ETV የተባለ የመግስት ጡሩምባ ለ30 አመት ያላነሳውን የክስታኔ ባህል ዛሬ ለምን ሽር ጉድ ። ጉራጌ ከክስታኔ እስከ አበሽጌ እስከ መስቃን ይህን ሴራ ልብ እንድትሉ ። በዚህ የመስቀል ወር ከ1 ሚሊዮን ሕዝብ በላይ ወዳገርቤት ይገባል ። የጉራጌ ወጣት ሁሉ በአዳብና ይገናኛል!! በዚህ ዘላለማዊ ባህል ላይ ፕሮፓጋንዳ ለመስራትና የዘር ፖለቲካ ለመነገድ ነው ብልጽግናዎች ላይ ታች የሚሮጡት !!

Horus
Senior Member+
Posts: 42903
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: Guraghe Youth Uprising in Ethiopia, Video!

Post by Horus » 20 Aug 2022, 13:57

Post Reply