Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 11594
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

"የማክሮ ኢኮኖሚውን መዛባት የማስተካከልና የዕዳ ክፍያን ለማቃለል ሲባል በ2015 አዳዲስ ፕሮጀክቶችን የመጀመር እቅድ የለም" የፕላን እና ልማት ሚኒስትሯ ዶ/ር ፍጹም አሰፋ

Post by sarcasm » 30 Jul 2022, 10:01

"የማክሮ ኢኮኖሚውን መዛባት የማስተካከልና የዕዳ ክፍያን ለማቃለል ሲባል በ2015 አዳዲስ ፕሮጀክቶችን የመጀመር እቅድ የለም" የፕላን እና ልማት ሚኒስትሯ ዶ/ር ፍጹም አሰፋ

በጦርነቱ የወደሙ አካባቢዎች መልሶ ግንባታ ተጠያቂነትን እና ዓለም አቀፍ መርሕን በጠበቀ አግባብ ይከናወናል”፦ ዶ/ር ፍጹም አሰፋ
*********************

በሰሜኑ ጦርነት የወደሙ አካባቢዎችን የመልሶ ግንባታ እና ማቋቋም ሥራ ተጠያቂነትንና ዓለም አቀፍ መርሕን በጠበቀ አግባብ የሚከናወን መሆኑን የፕላን እና ልማት ሚኒስትሯ ዶ/ር ፍጹም አሰፋ ተናገሩ።

በሰሜን ኢትዮጵያ በነበረው ጦርነት በተለይም በአማራና አፋር ክልሎች በርካታ መሰረተ ልማቶች ላይ ከፍተኛ ውድመት መድረሱ ይታወቃል።
በዚሁ ጉዳይ ላይ ከኢዜአ ጋር ቆይታ ያደረጉት የፕላን እና ልማት ሚኒስትሯ ዶ/ር ፍጹም አሰፋ፤ በጦርነቱ የወደሙ መሰረተ ልማቶችን መልሶ ለመገንባት መንግሥት የአምስት ዓመታት ዕቅድ ይዞ እየሠራ መሆኑን ገልጸዋል።
Sarcasm's comment: Does that mean for the next 5 years, Ethiopia will working to reach where it was 7 years ago?

በልማት ድርጅቶች ከሚከናወነው የመልሶ ግንባታ በተጨማሪ መንግሥት የራሱን በጀት መድቦ በመንቀሳቀስ ላይ መሆኑን ተናግረዋል።

በ2015 በጀት ዓመት ብቻ ለመልሶ ግንባታው በመንግሥት በኩል 15 ቢሊየን ብር ስለመመደቡም ሚኒስትሯ ጠቅሰዋል።

የመልሶ ግንባታው በተለይም በትምህርት እና የጤና ተቋማት ላይ ቀደም ብሎ መጀመሩን አስታውሰው በተያዘው በጀት ዓመት የመንግሥት የትኩረት አቅጣጫ የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን ማስቀጠል እና የወደሙትን መልሶ መገንባት መሆኑን አብራርተዋል።

በአጠቃላይ የማክሮ ኢኮኖሚውን መዛባት የማስተካከልና የዕዳ ክፍያን ለማቃለል ሲባል በበጀት ዓመቱ አዳዲስ ፕሮጀክቶችን የመጀመር እቅድ የለም ብለዋል።

ለመልሶ ግንባታው ከዓለም ባንክ የተገኘው 300 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ከደረሰው ውድመት አኳያ በቂ እንዳልሆነ ገልጸው የልማት አጋሮችን ቀጣይነት ያለው ድጋፍ ይሻል ብለዋል።

ከባንኩ የተገኘው ድጋፍ በአማራና አፋር ክልሎች በመንግሥት በኩል ገቢራዊ የሚደረግ ሲሆን በትግራይ ክልል ግን በሶስተኛ ወገን ጣልቃ ገብነት ይከናወናል ነው ያሉት።

መልሶ ማቋቋሙን የሚያከናውነው ሶስተኛ ወገን ለዓለም አቀፍ መርሕና ተጠያቂነትን ታሳቢ ባደረገ አግባብ ተፈጻሚ እንደሚሆን ስምምነት መደረጉንም አስረድተዋል።

የመልሶ ማቋቋም ሥራዎች በታለመላቸው መልኩ እንዲፈጸሙ እንደማንኛውም የልማት ፕሮግራም ተጠያቂነት ባለው አግባብ እንደሚፈፀም በገንዘብ ሚኒስቴር፣ ፕላን እና ልማት ሚኒስቴር እና ሌሎች ተቋማትን ያካተተ አደረጃጀት መዋቀሩንም ተናግረዋል።

የገንዘብ ፍሰቱን የሚመለከት በገንዘብ ሚኒስቴር ስር ጽህፈት ቤት መቋቋሙንና የፕሮግራም አፈጻጸሙም በፕላንና ልማት ሚኒስቴር እየተገመገመ እንደሚፈጸም ነው ያብራሩት።

Please wait, video is loading...

sarcasm
Senior Member
Posts: 11594
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

Re: "የማክሮ ኢኮኖሚውን መዛባት የማስተካከልና የዕዳ ክፍያን ለማቃለል ሲባል በ2015 አዳዲስ ፕሮጀክቶችን የመጀመር እቅድ የለም" የፕላን እና ልማት ሚኒስትሯ ዶ/ር ፍጹም አሰፋ

Post by sarcasm » 30 Jul 2022, 12:12


This was in 2011 - the year after PM Abiy came to power - አዳዲስ የልማት ፕሮጀክቶች አለመጀመር አባዜ ለካ ቆየት ብሏል። በብልጽግና ሟሟ እናዝግም እየተባለ ነው።



ኢትዮጵያ በቀጣዩ በጀት ዓመት በ2011 አዳዲስ የልማት ፕሮጀክቶች አትጀምርም


አዲስ አበባ ሰኔ 29/2010 ኢትዮጵያ በ2011 በጀት ዓመት አዳዲስ የልማት ፕሮጀክቶች እንደማትጀምር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ተናገሩ።

ቀደም ሲል የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን ለመጨረስ 7 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ያስፈልጋል ብለዋል።

ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለቀረበላቸው ጥያቄዎች ምላሽ እየሰጡ የሚገኙት ጠቅላይ ሚኒሰትሩ፤ በቀጣዩ በጀት ዓመት ኢትዮጵያ ቀደም ብላ የጀመረቻቸውን ፕሮጀክቶች ለመጨረስ ትኩረት ታደርጋለች ብለዋል።

አሁን ባለው የፕሮጀክቶች አፈጻጸም አገሪቱ አዳዲስ ፕሮጀክቶችን ለመጀመር ከውጭ ምንዛሪ አኳያ አዋጭ አለመሆኑን የገለጹት፤ የፕሮጀክቶችን ፍትሃዊነትን ለማረጋገጥ መጀመሪያ በዕውቀትና በፋይናንስ አመራር ፕሮጀክቶችን መፈጸም እንደሚገባ ተናግረዋል።

የመንግስት የልማት ድርጅቶች 400 ቢሊዮን ብር ከተለያዩ ባንኮች እንደተበደሩ የገለጹ ሲሆን፤ ነገር ግን በርካታ ፕሮጀክቶች በታቀደላቸው ጊዜ እየተጠናቀቁ አይደለም።

በዚህም አንዳንድ የልማት ድርጅቶች ካላቸው አጠቃላይ ሀብት የሚስተካከል አልያም ከሃብታቸው የሚልቅ ዕዳ እንዳለባቸው ያብራሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ “ከንግድ መርህ አንጻር ይህ አዋጭነት የለውም” ነው ያሉት።

በተለይም በስኳርና በማዳበሪያ ፋብሪካ ፕሮጀክቶች በኩል ጊዜው ስኳር ተመርቶ ለገበያ ቀርቦ ገቢ የሚደረግበት ወቅት ነበር ብለዋል።

ስለሆነም ተጨማሪ ጊዜና ሀብት እየወጣባቸው የሚገኙ ፕሮጀክቶች ግብረ ኃይል ተቋቁሞ፣ የልማት ድርጅቶቹ መስራት የሚችሉት እንዲሰሩ፣ የማይችሉትን ደግሞ ወደግል ዘርፍ እንዲያሸጋግሩ በማድረግ በሚቀጥለው ዓመት አብዛኞቹን ለማጠናቀቅና ወደ ስራ ለማስገባት ታስቧል ነው ያሉት።

ከዚህ በኋላ ከሚገኘው ሀብት ጨምረን በተሟላ ዕውቀት አዳዲስ ፕሮጀክቶችን ወደ መገንባት እንሸጋገራለን ብለዋል።

https://www.ena.et/?p=9057


Post Reply