Re: Must Watch: ዜና እረፍት : የ FM ሬድዮ የዓብይ አህመድን እረፍት አበሰረ
በእውቀቱ ሥዩም ዓብይ አህመድ ሞቷል እያለን ነው ?
ንጉሱ ድንገት ወራሹን ሳያሳውቅ በጦር ሜዳ ይገደላል እንበል፥ አንዱ የቤተመንግስት መኮንን ብድግ ይልና አንዱን ልኡል ከማጎርያ ቤት አውርዶ ዙፋን ላይ ያወጣዋል፤ ሌላው የጦር አዝማች ደግሞ የኔን ምርጫ ካላነገስኩ ሞቼ እገኛለሁ ብሎ ይነሳል፤ ባንጋሾች መካከል የሚደረገው ፉክክር መዲናይቱን ባንዴ ወደ ፍርስራሽ እና ያስከሬን ክምር ይቀይራታል::
የቀድሞ ሰዎች እንዲህ አይነቱን ብሄራዊ አደጋ ለመቀነስ የፈጠሩት “ዘዴ “ የንጉስን ሞት መሰወር ነበር ፤ የንጉስ ሞት ቀርቶ ህመሙ እንኳ ለህዘብ ይፋ አይደረግም፤ በዘመነ መሳፍነት ጊዜ ፥ የየጁው ራስ አሊ ሲሞት ፤ አንድ አሳባቂ ( የዘመኑ ፓፓራዚ) ወሬውን አሾለከው፤ ወድያው የረጋው አገር መላወስ ጀመረ፤ ጉዳዩ ያሳሰባት አንዲት አልቃሽ እንዲህ ብላ ገጠመች፥
“ እሻ እሻ ነው እንጂ የእስራኤልን ሞት
እንዲያልቅሰው አሊን ለምን ቀበሩት “
“ እሻ እሻ “ ማለት ዝም በሉ ጸጥ በሉ ማለት ነው ፤ በዘመኑ የንጉስ ወገን ነን የሚሉ ሰዎች ዘራቸውን ከሰለሞን ስለሚመዝዙ “ እስራኤል “ በሚል የወል ስም ይታወቃሉ፤
በግጥሙ መስመር ላይ ያለው ህብረቃል “ እንዲያልቅሰው “ የሚል ነው፤ ሰሙ “ እንዲህ አልቅሰው “ ሲሆን ወርቁ “ ሰው እንዲተላለቅ” የሚል ትርጉም አለው ፤
ባጭሩ አልቃሺቱ፥
“ ህዘብ እንዳይተላለቅ
የንጉስ ሞት ይደበቅ “ ማለት ነው የፈለገችው ፤[/size]
Source: https://www.facebook.com/bewketu.seyoum.3

Funeral March