Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 42914
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

በMarch 2022 ለeden የመለስኩት መልስ

Post by Horus » 30 Jul 2022, 11:49

አንዳንዴ በሲቃ የምንጽፈው ነገር መልሰን ማድረግ አንችልም ። ከዚህ በታች ያለው መነባንብ ዛሬ መልሼ ልጽፈው አልችልም። የጎሳ ፖለቲካ ዘመናዊ የፖለቲካ ሲስተም ሊሆን አይችልም እያልክ ትደጋግማለህ ላለኝን መልስ ...

"ኤደን፣
ኢሳቅ ኒውተን መሰረታዊ የፊዚክስ ሕጎችን ካሳወቀ መቶዎች አመታት አልፈዋል። እነዚያ የፊዚክስ ሕጎች በየቀኑ ለአዲስ ተማሪ ይደገማሉ፣ ይሰበካሉ ። ሕጉን አውቀው፣ ትምረው፣ ተቀብለው ስራ ላይ ያዋሉት የኢንዱስትሪ አብዮት አይደለም የኢንፎሜዝሽን አብዮት አይደለም ሰው ሰራሽ ሰው ሮቦት ፈጥረውበታል። አንተ ዛሬም ሁለት በሬ በጠማማ እንጨት አስረህ ፣ዛሬም ቆሻሻ ዉሃ እየጠጣህ በጭለማ ውስጥ አለህ።

ደደቦች ማንም የማይሰብረው፣ ማንም የማይበግረው የሰሩት እስር ቤት እራሳቸው ለራሳቸው በራሳቸው አንጎል ውስጥ የገነቡት ድንቁርናና እምነት ነው ። እኔ ለኢትዮጵያ ችግር ያለኝ ሃሳብ ምን እንደ ሆነ ማወቅ ካሻህ እዚህ ፎረም ላይ ካ10 አመት በላይ የጻፍኳቸውን ሃሳቦት አንብብ። ጎሳ ያንተ የማይበገር ያንጎልህ እስር ቤት ነው ። ደሞ እዚያ እድሜ ልክ ታስረህ ከሱ ጋር እስከነ ድንቁርናህ ድህንትህ፣ እና ስቃይህ ይዘህ መሞት መብትህ ነው ።

አንተ የማህበራዊ ሳይንስ ሕግጋት አልቀበልም ስላልክ፣ አንተ የፖለቲካ ሳይንስ ሕግ አምቢ ስላልክ እነዚህ በታሪክና በፕራክቲስ የተረጋገጡ ሕጎችን መደጋገም አንተውም አልተውም! ሳይስን እውነት ስለሆነ ይደገማል፣ ይደጋገማል ። በፖለቲካ ሳይንስ ሕግ ዘር፣ ጎሳ፣ ዘውግ ዘመናዊ የመንግስት ስርዓት ማቆሚያ ንድፈ ሃሳብ አይደለም፣ የፖለቲካ ማደራጃ ዘዴ አይደለም። ያን የሚከተሉ አላዋቂ የፖለቲካ መሃይሞች ወይም በዉሸት የሕዝብ ገዢ ሆነው የሚነግሱ መሳፍንት ናቸው ። አንድ መስፍንኮ የገዢነት መብትና ሃይል የተሰጠኝ ከፈጣሪ ነው ሲል ተቀብለህ ስትገዛ ነበር፣ ዛሬም አንድ መስፍን ተነስቶ የገዚነት መብትና ሃይል የተሰጠኝ ይህን ዘር ያንን ዘር ስለሆንኩኝ እያለ ነው! ያንን ድንቁርና ነው ስርዓት ብለህ የምትገዛው ።

ዘመናዊ ነጻ፣ ፍትሃዊ፣ አበልጻጊ፣ የፖለቲካ ስርዓትና መንግስት የሚያቆሙ ነጻና ልዑል የሆኑ ግለሰቦች በነጻ ፈቃዳቸው የሚያቆሙት እንጂ ፣ በጎሳና በዘር እስር ቤት እንደ ከብት ታጉረው እንደ ከብት እየተነዱ የታዘዙትን እንደ ባሪያ እሺ እያሉ የሚዘፍኑት የደንቆሮችና የመሪዎቻቸው የሌቦች ድራማ አይደለም ። እናም ደግሜ ልንገርህ እኔና እኔን መሰል ነጻ ዜጋ ምን ማለት እንደ ሆነ የምናውቅ ገና የዚህን የጎሳ ጫጫታ ድድብና ያለ ማቋረጥ ደጋግመን እናሳውቃለን!

ሂድ ዞር ዞር ብለህ አስተውል ትግሬ ሲራብ ልጅ ነበርኩ! ዛሬም ትግሬ ረሃብ ውስጥ ነው! ዛሬም የዘር እስር ቤት ተቆልፎበት ያለቅሳል! ቦረና ዛሬም ይራባል! በቃ። ሳይንስን ልትክድ ትችላለህ! ከመከራህ ግን መውጣት አትችልም! ከራስህ የጎሳ ከርቸሌ ማንም አያላቅቅህም !"