Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 42907
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

ልጓዝ በውድቀት ጎዳና በወያኔ ትግሬ ፋና (ያቢይ መከራ)

Post by Horus » 30 Jul 2022, 00:36

የትግሬ ወያኔዎች ከምዕራብ ቅኝ ገዦች የኮረጁትን የዘር አፓርታይድ ናዕት ስርዓት ለማስመሰል ሲባክኑ መለሰ ዜናዌም ያን የጎሳ ናዕት አምባሻ ነው ብሎ ለማሳመን ሲታክት እንደ ሰም ቀልጦ አለእድሜው አለፈ ።

አቢይ አህመድም "ለውጡ" ኢህአዴጋዊ ነው ብሎ አወጀና ተረኛ የኦሮሞ ጎሳ ከበርቴም 'ልጓዝ በውድቀት ጎዳና በወያኔ ትግሬ ፋና' ብሎ ዘመረ! ልክ እንደ መለሰ ዜናዌ አቢይም ይህን የቅኝ ገዦች ናዕት ጨጨብሳ ነው ብሎ ሊያሳምነን ሲታክት አለእድሜው ሊያልፍ ነው።

የጎሳ ሰርዓት የፖለቲካ ሲስተም አይደለም! መደመር ቢባል፣ ማካፈል ቢባል፣ ማባዛት ቢባል ያው ስልቻ ያው ቀልቀሎ ነው! አይሰራም ! ትግሬዎች ለ50 አመት ሞክረውት አሁንም ረሃብ ላይ ናቸው! ኦሮሞች ለሌላ 50 አመት ሊባክኑበት ይችላሉ! አይሰራም።

በከንቱ አትልፉ! በከንቱ አትሙቱ! ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር !!