sarcasm wrote: ↑24 Jul 2022, 10:00
Kudos to Our athletes for beating the odds-persecution, discrimination worse, government imposed separation from their loved ones-to beat the rather unbelievable odd of winning medals for #Ethiopia.
"አይክፋችሁ ክብር ይገባችኃል። በብዙ ፈተናዎች አልፋችሁ በብዙ ተፅእኖ አልፋችሁ የኢትዮጵያን ሰንደቅዓላማ ከፍ ስላደረጋችሁ በጣም እናመሰግናለን።" ደራርቱ ቱሉ
♦ ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ በእንባ ተሞልታ ያቀረበችው ተማፅኖ !!!
" ... የሀገራችን ጉዳይ ያመናል ፤ ሁላችንንም የትግራይ እናቶች አባቶች ፤ እናቶቻችን አባቶቻችን ናቸው ። በእርግጠኝነት ደግሞ ነገ ሌላ ቀን ነው ።
ስለዚህ አይክፋችሁ ክብር ይገባችኃል። በብዙ ፈተናዎች አልፋችሁ በብዙ ተፅእኖ አልፋችሁ የኢትዮጵያን ሰንደቅዓላማ ከፍ ስላደረጋችሁ በጣም እናመሰግናለን።
ትግራይ ትላንትም ብትሆን ኢትዮጵያ ናት ፤ ዛሬም ኢትዮጵያ ናት ፤ ነገም ኢትዮጵያ ነች ስለዚህ እባካችሁ መሪዎቻችን እባካችሁ...እባካችሁ ... እባካችሁ ተጠቅማችሁ አይደለም ፤ ተጎድታችሁ ኢትዮጵያን አንድ አድርጓት እባካችሁ !!! ከእግዚአብሔር ጋር ትችላላችሁ። ስለዚህ መሪዎቻችን ተጎድታችሁ ለኢትዮጵያ ብላችሁ ፣ ለህዝብ ብላችሁ እናተ አንድ ካደረጋችሁ ኢትዮጵያ አንድ ትሆናለች።
... ስፖርት ወንድማማችነት ፣ ፍቅር ፣ ሰላም ነው!! ለሰላም ፣ ለፍቅር ቆመው እነዚህ ልጆች ምንም ሳይበግራቸው ለዚህ ውጤት በቅተዋልና አሁንም ቢሆን ክብር ይገባቸዋል። እናከብራችኃለን። በእርግጠኝነት ቤተሰቦቻችሁ የት እንዳሉ ታውቃላችሁ ግድ የላችሁም እንወዳችኃለን እናከብራችኃለን ፤ እንደልጆቻችን ነው አሁንም የምናያችሁ ስለሆነም ትግራይ ዛሬ ብቻዋን አይደለችም ከኢትዮጵያ ጋር ነች፤ ነገም ከኢትዮጵያ ጋር ትሆናለች።
እኔ የትግራይ ህዝብ እና የኢትዮጵያ ህዝብ ስል ምቾት አይሰማኝም እንደ ኢትዮጵያ ነው ሁላችንም የምናየው ፤ ሁሉም ብሄር ብሄረሰቦቻችን ኢትዮጵያ ናቸው ፤ ትላንትናም ተባብረውና ኢትዮጵያውያን እዚህ ያበቁትና ነገም ዛሬም እንተባበር ኢትዮጵያን አንድ እናድርጋት።
እኛ ልጆቻችሁ ከኦሮሞ የመጣ፣ ከአማራ የመጣ፣ ከትግሬ የመጣ፣ ከጉራጌ ከየትም የመጣው ለዚህ ነው አንዷን ሰንደቅዓላማ ከፍ ያደረግነው ስለሆነም ብሄር ሳንለን፣ ሃይማኖት ሳንለይ፣ ፆታ ሳንለን፤ ባንዲራችንን ያነሳነው ስለተባበርን ነው፤ በፅናት ስለቆምን ነው። ለእናተም አያቅትም የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስትም የኢትዮጵያ መንግስትም እባካችሁ ...ስለነገዋ ኢትዮጵያ አንድነት፣ ስለብልፅግናዋ ፣ ስለእድገቷ፣ ስለሰላሟ፣ እባካችሁ አያቅታችሁም እኛም ከጎናችሁ አለን ስፖርት ሰላም ነው ፤ ስፖርት ፍቅር ነው ብለናል ተያይዘን ኢትዮጵያን አንድ እናድርጋት። እግዚአብሔር ደግሞ አንድ ያድርግልን። "