Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Wedi
Member+
Posts: 8649
Joined: 29 Jan 2020, 21:44

በኦሮሙማ የታፈነው ክፍለ-ሀገር .....!! ጉራጌ ክፍለ ሀገር!!

Post by Wedi » 23 Jul 2022, 00:57

በኦሮሙማ የታፈነው ክፍለ-ሀገር .....!! ጉራጌ ክፍለ ሀገር!!

♦ “ የታፈነው ክፍለ-ሀገር .....!! ”

📌 ታሪክን የኃሊት የጉራጌ ህዝብ እና የህወሓት ክርክር 1987 ዓ.ም

`` የጉራጌ ህዝብ አዲስ ክልል አልጠየቀም የተወሰደበትን ክልል ግን ይመለስለት``

“ የጉ.ክ.ሀ.መ.ሥ.ድ ..! የጉራጌ ክፍለ ሀገር መንገዶች ሥራ ድርጅት የሚያስታውስ አለወይ.? እንዲሁም ጉ.ራ.ል.ድ የጉራጌ ራስ አገዝ ልማት ድርጅት ..!! ጉራጌ ቀድሞውንም ክልል እንደነበር በቂ ማረጋገጫ አለ ፤ የጉራጌ ህዝብ አዲስ ክልል አልጠየቀም የተወሰደበትን ግን ይመለስለት ፡፡ “

በመላኩ ቢረዳ Melaku Bireda MB

⇣ ጉራጌ ዘረኛም ሆነ ብሔርተኛ አይደለም አልነበርምም አይሆንምም!! ከማንም ብሔር እና ብሔረሰብ ጋር ተስማምቶ እና ተግባብቶ ሊኖር የሚችል ሀገሩን (ኢትዮጵያን) የሚወድ ኩሩ እና ታታሪ ህዝብ ነው! በክልሎች አወቃቀር ወቅት የጉራጌ ዞን መጀመሪያ በክልሎች አወቃቀር ወቅት በክልል ሰባት በሁለት ዞኖች ( ምዕራብ ዞን ወልቂጤን ማዕከል አድርጎ እና ደቡብ ዞን ቡታጅራን ማዕከል አድርጎ) ተዋቅሮ ነበር! የደቡብ ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ክልል ሲዋቀር (ክልል 7 8 9 10 11....) የሚባሉት በአንድ ላይ ከ48 በላይ የሚሆኑ ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦችን የያዙት ክልሎች በአንድ ላይ በአንድ ክልል ስር ተዋቀሩ! በወቅቱ የህዋሃት ሰዎች በየዞኑ ተመደበው የሚያደራጁ ክልሉን የሚመሩ በየቦታው ሰለነበሩ በየዞኑና በየብሄር ብሄረሰቡ ተከታታይ የድርጅት ስብሰባዎች ፣ የህዝብ ስብሰባዎች ያደርጉም ነበር! እነዚህን ክልሎች በአንድ ላይ ቢዋቀሩ የደቡብ ህዝቦች ሁሉ ተጠቃሚ እንደሚሆኑ የባህል ተዘማጅነት ስላለ የበለጠ ባህላቸውን ቋንቋቸውን እንደሚያሳድጉም ይሰብኩ ነበር!!ሆኖም ግን አጀንዳው በወቅቱ ከፍተኛ ተቃውሞ ገጥሞት ነበር!

ብዙ ክርክሮች ነበሩ በወቅቱ እያንዳንዱ ብሄርና ብሔረሰብ የራሱን ቋንቋ ባህል ማሳደግና ልማቱንም ማሰደግ ይችላል ከተባለ፣ ኦሮሞ፣ አማራ፣ ትግሬ፣ ሱማሌ፣ ሀረሪ፣ አፋር ሌሎችም ክልሎች ሁሉም የየራሳቸው ክልሎች አዋቅረው ቋንቋና ባህላቸውን ማሰደግ ሲችሉ እንዴት ከ48 በላይ የሚሆኑት የደቡብ ብሔርና ብሔረሰቦች በአንድ ላይ ተጨፍልቀው ባህልና ቋንቋቸው በምን አይነት መልኩ ነው ሊያሳድጉ የሚችሉት የሚል ጥያቄም በወቅቱ በሰፊው በክርክርና በወይይቱ ተነስቶም ነበር !

የህዋሃት ሰዎች ግን በቂ መልስ አልነበራቸውም! የበደቡብ ህዝቦች ብላችሁ ክልሉን ማወቀር ካለባችሁ፡ የሰሜን ህዝቦች ፣ አማራን ትግሬን፣ አፋርን በአንድ ክልል ወይም በሁለት ክልል ስታዋቅሩ ከዚያ የደበቡ ህዝቦች በሚል ክልላዊ አወቃቀር እንዲዋቀር ማወቀር ትችሉ ይሆናል የሚልም ሃሳብ ቀርቦላቸው ነበር ህዋሃትና ህዋሃተኞች ግን በፍፁም አሻፋረን አሉ!

በየብሄረሰቡ የሚደረጉ ስብሰባዎች ከተደረጉ በኋላ በጉራጌ ብሄረሰብ በወቅቱ የነበሩት የህዝብ ተመራጭ የሆኑት የኢሀዴግ ዓላማን የሚያራምደው የጉራጌው ድርጅት (ጉህአዴን) የጉራጌ ህዝብ አንድነትና ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ በወቅቱ የድርጅቱና በከፊልም የህዝቡ ተወካዮችና የድርጅቱም ምሁራን ሽንጣቸውን ገትረው ጉራጌ ክልል ያስፈልገዋል፣ ከ48 ብሄሮች ብሔረሰቦች ጋር በአንድ መጨፍለቅ የጉራጌ ህዝብ የለበትም ፣ ይህ ከሆነ ደግሞ ቋንቋችን፣ ባህላችንን እንዲሁም ልማታችን እንዴት አድርጎ ነው የጉራጌ ህዝብ ማሰዳግ የሚችለው ፡፡ ብሄረሰቡ ቀድሞም የልማትን ጥቅም የሚያውቅ እና ወደፊት የተራመደ ስለሆነ ወደ ኋላ መጎተት የለበትም የሚል ጥያቄ በየስብሰባው እና በየ ውይይቱ ይቀርብ ነበር ! ክልሉ ለማዋቀር አዋሳ ላይ ከሁሉም ብሄረሰቦች የተወጣጡ የህዝብ ተመራጮች የመጀመሪያው ጉባኤ ሲያደርጉ ከሁሉም ብሄሮች ከመጡት ተወካዮች የጉራጌው ዞን ሽንጥን ገትሮ ያደርገው የነበረው ክርክር ጎልቶ የወጣ ነበር!

የጉራጌ ህብ በወቅቱ ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉት ብሄሮች በህዝብ ቁጥር ቢያንስ በ3ኛ ወይም በ4ኛ ደረጃ የሚገኝ ህዝብ ነው! ራሱ በራሱ ማስተዳደር የሚችል በሰው ሃይልም ሆነ በሃብት በቂ Resources ያለው ህዝብ ነው ከትግራይ፣ ከጋንቤላ፣ ከሱማሌ፣ ከአፋር፣ ሌላው ቢቀር በዚያን ወቅት 100 000 ( አንድ መቶ ሺ) ህዝብ ከማይሞላው ከሀረሪ ህዝብና ክልል እንዴት አንሶ ነው የራሱ ክልል የማይስጠው በልማት እረገድም ቢሆን ህዝቡ መንግስትን ሳይጠብቅ በራሱ ተባብሮና ተረባርቦ ሊሰራ የሚችል ወደፊት እንዲራመድ ሊደረገ ሲገባው እንዴት ወደ ኋላ ይጎታታል የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ ተደርጎ ነበር !!

በወቅቱ ክልል ካልተሰጠን ሁለት ዞኖች ሊሰጠን ይገባል እነዚህንም ሁለቱ ዞኖች ቡታጀራ እና ወልቂጤ መሆን አለባቸው የሚል ሌላም አማራጭ በጥያቄና በክርክሩ ወቅትና በዛን ዘመን ቀረቦ ነበር ! በወቅቱ የነበሩት አብዛኞቹ የጉራጌ ህዝብ ተወካዮች ከጥቂት ሆድ አደር እና አስመሳይ ካድሬዎች በስተቀር ሁሉም አንድ አይነት አቋም ይዞ ወደ የሀዋሳው የክልል ጉባኤ ገባ! የሚያሳዝነው የጉራጌ ህዝብ ተወካዮች በዛንም ወቅት ቢሆን ባይተዋር እና ገለልተኛ ተደርገው ነበር !!


:oops:
Please wait, video is loading...
:oops:

:oops:

:oops:

Please wait, video is loading...

TGAA
Member+
Posts: 5747
Joined: 07 Apr 2019, 20:34

Re: በኦሮሙማ የታፈነው ክፍለ-ሀገር .....!! ጉራጌ ክፍለ ሀገር!!

Post by TGAA » 23 Jul 2022, 01:16

The iconic Ethiopians, the beautiful Garage people. They are too beautiful to smart to be swallowed by moggasa gobblers.

Horus
Senior Member+
Posts: 42918
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: በኦሮሙማ የታፈነው ክፍለ-ሀገር .....!! ጉራጌ ክፍለ ሀገር!!

Post by Horus » 23 Jul 2022, 01:20

በትክክል! እኔ ሱሪ ያልታጠቀ ህጻን ሆኜ አባቴ ከ5 ልጆቹ ጋር የተተመነበት መዋጮ ለ 'ካለምገና እስከ ወላሞ ሶዶ የመንገድ ስራ ድርጅት' ገንዘብ ሰጥቶ ጠቅላይ ቢሮ ይልከን ነበር ። ጠቅላይ ቢሮ (የመርካቶ ማዘጋጃ ቤት) ማለት ነው ፣ ዛሬ የንግድ ባንክ ቅርንጫፍና ምራብ ሆቴል የተሰሩበት ላይ ነበር። የኦሮሞች ሜጫና ቱለማ መረዳጃ ማህበር ሞዴል የወሰዱት ከዚህ የክስታኔ (የሶዶች) ድርጅት ነው ። ዛሬ ጉራጌ ተገፍቶ ተገፍቶ እንደ ጋፋት እንዲጠፋ እየተደረገ ነው ። ግን አይሳካም !

Wedi
Member+
Posts: 8649
Joined: 29 Jan 2020, 21:44

Re: በኦሮሙማ የታፈነው ክፍለ-ሀገር .....!! ጉራጌ ክፍለ ሀገር!!

Post by Wedi » 23 Jul 2022, 01:43

Please wait, video is loading...

Post Reply