የኮንደሚኒየም ቤት ሌቦች አያያዝ
መንግስት በታሰሩ የኮንደሚኒየም ሌቦችና ግነኙነት ያላቸው ግለሰቦች ላይ ከፍተኛ ክትትል ማረግ ይኖርበታል :: ለምን ? እንደሚገመተው እነዚህ ሌቦች ከዕስር ለመውጣት የማያደርጉት ጥረት አይኖርም :: ለዚህም የህግ አስከባሪውንና አስፈፃሚውን የመንግሥት አካል ፣ ፖሊስ፣ ዳኞችንና ሌሎች ተፅኖ ይፈጥራሉ የሚባሉ ግለሰቦችን ጉቦና ሌላ መደለያ ዘዴዎችን በመጠቀም ነው:: እነዚህ ሌቦች ከህግ አግባብ ውጭ በሆነ መንገድ ከዕስር ከተለቀቁ የመንግስት የህግ አስከባሪና አሰፈፃሚ አካላት ተአማኝነት ያጣሉ :: መንግስትም እንደዚሁ ተዐማኝነቱ እየተሸረሸረ ፣ "ያብይ መንግስት አልቻለም " የሚሉ በቀቀኖች ይበራከታሉ ማለት ነው :: በተለይ እንደዚህ ባደባባይ በወጣ የህዝብን ቀልብ በሳበ ጉዳይ ላይ የህግ አግባብነት ያለው ስራ መሰራት ለህዝብና መንግስት ትልቅ ፋይዳ አለው::